ዛሬ አብያዊ መንፈስ ከሱባኤ ማግስት በመነኩሲት ባዕት!

ትርጉም ገብ ማዕልት።
„እግዚአብሄርን መፍራት ውደ ህይወት ይመራል፤
የሚፈራውም ጠግቦ ይኖራል፤ ክፉ ነገርም አያገኘውም።“
ምሳሌ ምዕራፍ ፲፱ ቁጥር ፳፫
  
ከሥርጉተ ©ሥላሴ
26.08.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ

ይህ የዶር አብይ አህመድ ፍላጎት የዛሬ አይደለም የቀደመ ነው። 

እንዴት ናችሁ የኔዎቹ ደህና ናችሁ ወይ። ትናንትና ጠ/ ሚር አብይ አህመድ በርከት ላሉ አገር ውስጥ ለሚገኙ ጋዜጠኞች የመጀመሪያውን የጋዜጠኞች እና የጠ/ሚሩን የመጠይቅ እና የመልስ ሂደት ሁላችንም ተከታትለናል። 

በጤናቸው ዙሪያ ለተነሳው ጥያቄ ምንም አልደረሰብኝም፤ ታምሜም አላውቅም ሲሉ ቅልብጭ ያለ መልስ ሰጥተዋል። ያም ቢሆን እንደ እኔ መሰል የቀደመውን አብይ ፍለጋ ለነበርን ሰዎች ብዙም አጥጋቢ አልነበረም። 

ይህ ሲባል ደህንነታቸውን መስማት አያስደስትም ማለት ግን አይደለም። የአብይ መንፈስን ባወቅነው ልክ አለመግኘታችን ነበር ጭንቀታችን። በሌላ በኩል ተራ ወሬ ብቻ ተደርጎ መወሰዱም ብዙም ያልተመቸኝ ነበር። ሰዉ ልዩ ፍቅር፤ ልዩ አክብሮት፤ ልዩ ተስፋ ስላለው ነው ጭንቁ መጠበቡ የነበረው። ዕንባ አልቃሽ በገንዘብ የተገዛበትም ታሪክ እኮ እናውቃለን።

ከሚዲያ መጥፋት ብቻ ሳይሆን የሚዲያዎች ሂደት እና አቀራረባቸው፤ ምስል ቀረጻው እና ሁኔታው በፍጹም ወደ ውስጥ ሊገባ የሚቸል አልነበረም። ዛሬ ሳይሆን ቀደም ባለው ጊዜም ጭምር በጥልቀት ጉዳያችን ብለን አብያዊ መንፈስን ለምንከታተለው ሰዎች ወሬው ከመወራቱ ቀድሞም ያሉትን ክንዋኔዎች በባለቤትን ስንከታተል መቆዬታችን ለኢትዮጵያ ተስፋ ካለን ቀናዕይነት ነበር። 

ልብ አምላክ ዳዊት „የቤትህ ቅናት በላኝ“ እንዳለው ማለት ነው። በዚህ ዘርፍ የጠላት እና የወረኞች ወይንም በጎ የማያስቡ እና ቅን ያልሆኑ ዜጎች የሚመኙት ጉዳይ ብቻ አድርጎ መወሰዱ እኔ እንደ ሥርጉተ ሥላሴ አልተመቸኝም። ባገኛቸውም እሞግታቸዋለሁኝ እኔ።
የሆነ ሆኖ ዛሬ አሁን አንድ ዜና አገኘሁ። ይሄ ዜና ይልቅ ያ እጠብቀው የነበረውን የአብይን መንፈስ ሙሉውን ውስጥነት ሰጥቶኛል። ስለዚህም ደስ ብሎኛል።

https://www.youtube.com/watch?v=yk2SbV8H-mY

Ethiopia:/ ዐብይ አህመድ እና ጓዶቹ በእሁድ ቀንም ሥራ ላይ ናቸው


በዚህም ቪዲዮ ላይ ሌላ ጸጉር ስንጠቃ እንደሚመጣ አውቃለሁኝ። አንድ ጊዜ „ሰው ሰው የሚሸት መሪ“ ነው የሚያስፈልገን ሲሉ ጸሐፊ አቶ ስዩም ተሾመ የቀድመዎን የአሜሪካ ፕ/ ባራክ ኦባማ ህጻን ልጅን ወለል ላይ ተንጋለው ሲያጫውቱ የሚያሰይ ፎቶ ተለጥፎበት አይቼ ነበር። ያ መቼም ለእኔ ጎርባጣ ነገር ነበር። „በእጅ የያዙትን ወርቅም“ ካለማወቅ የመነጨ ነበር። ዋላ ደግሞ የ የአብይ መንፈስ ደጋፊ ሰልፍ አስተባባሪ ሆነዋል ጦማሪው። እንኳንም ለዚህ አበቃቸው ብያለሁኝ።  

ይህም ምን ማለት ነው አንድን ሰብዕ ወደ መሪነት ሲመጣ ወደ ኋዋላ ተመልሶ መነሻውን ማጥናት ይጠቅማል። መነሻውን ወደ ኋዋላ ሳብ አድርጎ ፍሬ ነገሩን፤ ስብዕናውን ማዳመጥ ጊዜ ወስዶ ለማጥናት መሞኮር፤ ከውስጥ መፍቀድም በፍጹም ሁኔታ ይገባል። ስለሆነም እኔ ጸሐፊውን በተለያዩ ጹሁፎች መሳረጃዎቼን እያቀርብኩኝ ሞግቻቸው ነበር።

ዛሬም ይህ ዜና ሲመጣ አሁን ጠ/ ሚኒስተርነታቸውን ለማዋደድ ነው ሊባል እንደሚችል ስለማውቅ ገፋ አድርጌ ከቀደመው ስብዕናቸው የተቀዳ ስለመሆኑ ማገናዘቢያዎችን ማቅረብ ግድ አለኝ።

እኔ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ24.12.2017 አብይ ብቸኛው የጎንደር ጌጥ በሚል ይህን ጽፌ ነበር።

ያን ጊዜ ዶር አብይ አህመድ ኦህዴድ ውስጥ ምንም ሥማቸው ብዙም የማይነሳ በዶር ለማ መገርሳ ፍቅር ምልዕቱ እኔን ጨምሮ በተመሰጥነበት ወቅት ወይንም ጊዜ ነበር። ከሥራቸው ብጡል የሆኑ ዶር አብይ አህመድ የሚባሉ ሰው አሉ በማለት ሙግት የጀመርኩት "አብይ ኬኛ!" በማለት ወደ ስድስት ክፍላት፤ ከዛም እጅግ በርካታ ጹሁፎችንም እንዲሁ በተከታታይ ሠርቻለሁኝ።

በ2009 የከተሞች ቀን በጎንደር ተከብሮ ነበር። በዚህ ቀን ተጋብዘው መግለጫ ሲሰጡ በትክክል አንድ ከንቲባ ሊያደርግ የሚገባውን አስገንዝበው ነበር። አሁን ዛሬ ሰንበት ላይ የሆነው ይሄው ነው።

/ አብይ አህመድ በጎንደር ከተማ ስለ ጎንደር እንዲህ አስገራሚ ንግግር አድርገው ነበር

በዚህ ጭብጥ „ሰው የጸሐይ ብርሃን ነው“ የሚል ፍልስፍና የተገለጠበት ነበር። በተጨማሪም የአንድ ከንቲባ ህልም እና እውንነትን በሚገባ በዝልቅት የተነተኑበት ነበር። የከንቲባዎችን ድርሻ በሚገባ ነበር የገለጹት። 

በጎ ተግባርን በሚመለከት ደግሞ ቪዲዮው ስለምን እንደተሰረዘ አላውቅም ግን ያን ጊዜ ክፍል ሁለት አብይ ኬኛን ስሰራ ሙሉውን ጽፌው ስለነበረ ይሄውና መንፈሱ …

በዛ ቪዲዮ ላይ የነበረው ጭብጥ ግን እንዲህ ይል ነበር ..."ውሃን ከጥሩ ነገርን ከሥሩ" እንዲሉ። እንዲህ ይላሉ ዶር አብይ አህመድ፤ ይህን የተናገሩት በ2009 ነው፤ በጎንደር ከተማ። 

የዛሬ 23 / 24 ዓመት ገደማ አጋጣሚ እዚህ ጎንደር ነበርኩኝ። ይሄ ቦታ አዳራሽ አልነበረም። በጣም የሚገርማችሁ ጎንደር ኢትዮጵያ ሆቴል፣ ፎገራ ሆቴል፣ ጎሃና ቋራ የሚባሉ ትላልቅ ሆቴሎች ነበሩት።ገብያ ማዕከሉም በጊዜው ትንሽ ሞደርንየሚባል ነበር። በጊዜው ከዚህ ወደ ርዋንዳ ዘመትኩኝ። ያኔ ሩዋንዳ 1994 ግጭት ነበርና ስዘምት ኪጋሊ ገጠር ነበረች። ከጎንደር አንጻር። አይወዳደሩም። ኪጋሊና ጎንደር በፍጹም አይወዳደሩም። ግን ኪጋሊ ባለፉት 20 ዓመታት ፕሬዚዳንቷ ማህበረሰባዊ እንቅስቃሴ ያደርግ ነበር። ካጋሜ በወሩ መጨረሻ ቀን አካባቢ እንቅስቃሴ ያደርግ ነበር። በዬወሩ ህዝብ ጋር ወጥቶ ከተማ ያጸዳል። እሚገነባ ላይብራሪ ካለ አብሮ ይገነባል። እሚሠራ ሥራ ካለ ይሳተፋል። መሪው ይሄ ስለሆነ አሁን ኪጋሊና ጎንደር ሳይሆን ኪጋሊናአዲስ አበባንልናወዳደር አንችልም። "

"ለምሳሌ ይህን ፕሮግራም ያዘጋጃችሁ ሰዎች የፕሮግራሙ መጨረሻ አንድ ቀን ሲቀረው ሁሉም ታዳሚ ዶር. አንባቸውን ጨምሮ ጥዋት 12.00 ሰዓት ተንስቶ ጎንደርን ሳያጸዳ ከሄደ መጥቶ ገንዘብ አፍስሶ ሊሆን ይቻላል፤ ድግስ ደግሶ ሊሆን ይችላል፤ ግን አንድ ነገር አስተምሮ አልሄደም ማለት ነው። የጎንደር ዩንቨርስቲ 50,000/45,000 ሺህ ማህበረሰብ አለው። በወር አንድ ቀን አንድ እሁድ ጥዋት ለአንድ ሰዓት ለሁለት ሰዓት ተከፋፍሎ ጎንደርን ማጽዳት ሃምሳ ሺው ሁለት ሁለት/ ሦስት ሦስት ዛፍ መትከል ቢለምድ ብዙ ገንዘብ የማይመለስው ሥራ ይሠራል። ሥራም ብቻም አይደለም፤ ሰው ጎንደርን ይወዳል፤ ጎንደርም ዩንቨርስቲውን ይወዳል፤ ተቋሙ ትርፍ ይሆናል ማለት ነው።" 

"በዛ መንገድ የተመረቀ (graduated) ያደረገው ሰው ደግሞ ITW ብቻ ሳይሆን ስሜታዊ የማሰብ ችሎታ (Emotional Intelligence) ያለው ይሆናል። ማገልገል የገባው ይሆናል። ለምሳሌ የዚህ ከተማ ከንቲባ (Mayor) በዚህ ዓመት ሥራ ሲቀጥር አንዱ ክራይተሪያ መሆን የሚገባው ሳትቀጠር በነጻ ስንት ጊዜ ከተማን  አጽድተሃል የሚል ሰርትፊኬት ያስፈልግዋል። በነፃ ያለገለገል ሰው ብትከፍለውም አያገለግልህም። ይህ ሰው  (this guy's) ሥራ ፈት/ አጥ ዓይነት (Unemployed) ነው የሚሆነው። "

"የተቀጠረ ግን የማይስራ ነው የሚሆነው። ሰው በነፃ ማገልገል ሲማር ነው ሲከፈለው የበለጠ የሚያገለግለው። እኛ ስትወስዱ እብዛኛው ሰው ቢሮ ይገባል። ጃኬት ያንጠለጥላል እንዳለ ይታሰባል። አቶ እከሌ ስትሉትአሁን ወጣይባላል። 11.00 ሰዓት ላይ ጃኬት የለም። ይህ ሰው (this guy's) የአገር ኢኮኖሚ የሚገድል ነው።እለተ ሰንበት 26.08.2018 የሆነውም ይሄው ነው።

የተሰረዘው ቪዲዮ ሊንክ ይሄ ነበር።"

Gonder Vs Kigali, Dr Abey explains why Gonder remained poor. / አቢያ ኪጋሊንና ጎንደርን ያወዳደሩበት።“ 

የተሰረዘበት ምክንያት ጎንደር እና ዶር አብይ አህመድን በመንፈስ ለመለያዬት የተሴረ ነው ብዬ ነው እማምነው። ዶር አብይ አህመድ እና ኮ/ ደመቀ ዘውዴ እንዲራራቁ የተፈለገበት ምክንያትም ይሄው ነው። እኔም በ እድሜ እንዲህ ጎንደርን ወስጡ ያደረገ መሪ ከጓድ ገዛህኝ ወርቄ በስተቀር አላዬሁም ነበር። ስለሆነም አስቀድሜ ሞግቼበት ስለነበር፤ አብይ ብቸኛው የጎንደር ጌጥ ብዬ ስለዚህም ይመስላል የተሰረዘው። 

ደግሞም እውነታውም ታይቷል ከዶር አብይ አህመድ ጋር እንዲገናኙ ያልተፈቀደው ኮ/ ደመቀ ዘውዱ ከ አቶ ጃዋር መሃመድ ጋር የመንፈስ መስመር እንዲፈጥሩ ተፈቅዷል። በሌላ በኩልም ዶር አብይ በጎንደር ላይ ጥርጣሬ እንዲያሰድሩ የጎንደር ህዝብ አብይ አደባባይ ንግግር እያደረገ ረግጦ ሄደ የሚልም አንድ ጹሑፍ በጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው ተጽፎ ጹሁፉን ከመጤፍ የማይቆጥሩት ሁሉ ተቀባብለው ለጥፈውለት ነበር። መቼም ያ መከረኛ ጎንደር የሁሉም ነገር ማገዶነት ለመቆስቆሻነት የተሰናዳ ነው፤ ከዛ የተፈጠሩትም ከውስጣቸው ለመሆን ስለተ - ቢሶች ናቸውና ...

በጠነከረ ሁኔታ ሊታይ የሚገባው ደግሞ እሰቡት ጎንደር ድረስ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ  ሄደው ኮ/ ደመቀ ዘውዱ ጋር እንዳይገናኙ ታግዶ ለአቶ ጃዋርን ግን ባህርዳር ድረስ አቀባበል እንዲያደርጉ ኮ/ ደመቀ ዘውዱ ተደረጉ። ፍሬ ነገሩን ከልብ ሆኖ ማዳመጥ ያስፈልጋል።    

የሆነ ሆኖ ከተሞችን በሚመለከት ያላቸውን ዕይታ የታዬበት የጎንደሩ ንግግር ነበር ጠ/ ሚር ከመሆናቸው በፊት ... ይህን የቀደመ ይመኙት የነበረውን ንጹህ መንፈስ ነው አሁን ዛሬ አዲስ አበባ ከተማ ላይ የፈጸሙት። ልክ ሦስት ማዕዘን ፊልም ላይ ሲሳተፉ ስለ ኤርትራ እና ስለ ኢትዮጵያ ያላቸውን ቅን ምናባዊ እሳቤ ድርጊት ላይ እንደ አዋሉት።

እግዚአብሄር ወዶ እና ፈቅዶ የመጀመሪያ የጠ/ ሚር የሹመት ንግግራቸው ላይም ኤርትራን በሚመለከት ንጹህ ፍቅርን እንደላኩ አዳምጠናል፤  በኋዋላም ተወዝፎ የተቀመጠውን የአልጀርሱን የውሳኔ ሃሳብ አቧራውን አራግፈው ወደ ተግባር ለማሻገር እንደደፈሩት "የባድመ እድምታ በሥርጉተ ዕይታ" ላይ ገልጨዋለሁኝ። ከዚያም ባለፈ ግንኙነቱ ተፈጥሯዊ እንዲሆን ያደረጉበት መንገድ ነው ውስጣቸውን ፍንትው አድርጎ የሚያሳዬን።

 ህልማቸውን ለማስፈጸም ሁኔታ ካጋጠማቸው ለማድረግ ደፋር መሆናቸውን በዚህ ውስጥ  እናዬልን። ንጽህናቸው የሚቀዳውም ከዚህ ነው። ዛሬም ያዬነው ይህንኑ ነው። ጎንደር ከተማ ላይ በነበረው የከተሞች ስብሰባ ላይ በእንግድነት ተጋብዘው ተገኝተው ያደረጉት ንግግር ጠ/ ሚር ሲሆኑ ትግራይ ላይ፤ አዋሳ ላይ፤ ውልቂጤ ላይ ይህንኑ ተናግረውታ፤ ለወጣቶች በአጽህኖት አሳስበዋል።  

ወደ ቀደመው ስመለስ ይህ የ እርምጃ ተግባር ገብ፤ ትርጉም ገብ አቅጣጫ ለአዲስ አባባ ብቻ ሳይሆን ለመላ የኢትዮጵያ ከተሞች እና በዬደረጃው ለሚገኙ ከንቲቦች እና ለመሪዎችም የተሰጠ የተግባር ት/ ቤት ነው። ይህም ብቻ አይደለም „የልጅ እና የጢስ መውጫው አይታወቅም“ እንደሚባለው የነገ የኢትዮጵያ መሪዎችም ይህን አብነት እንዲወስዱ ለማጠዬቅ ነው። ተቋም ነው።  

በቀጣዩ የምርጫ ሂደት አሸናፊ የሚሆኑ የአገር መሪም ይህን አብነት እንዲከተሉም ነው። ዘርፈ ብዙ አምክንዮ አለው። ነገር ግን ይህን ማድረጋቸው ጠ/ ሚር ስለሆኑ አይደለም፤ ወስጣቸው ስለዚህ መልካም ነገር ስለመፈጠሩ ነው። ዓላማቸው ኢትዮጵያን ቁም ነገር የማድረግ ዓላማ ነው ያላቸው።

 ሌላም ጠንከር ያለ የደግነት ፍልስፍና ማስረጃ ደግሞ ላቅርብ …

ይሄ ደግሞ የመሰሪያ ቤት ሃላፊ በመነበሩብት ጊዜ የሆነ ነው …

Ethiopia - Dr Abiy ከላይ ስትሆኑ በዛ መነጽር ብቻ ታች አትመልከቱ

„ግንዛቤ ፕርስፔክቲብ መልካም ነገር ነው በተለይ አለቆችን ይመለከታል፤ የበታች ያሉ ሰዎችን ላይ ሆናችሁ ስትመለከቱ ለምሳሌ ሰርቢስ አምልጦኝ ነው፤ በእግሬ ነው የመጣሁት ስትል አንዲት ምስኪን ደሃ ሠራተኛ ቢሯችን ውስጥ አለቆች አይገባንም፤ ሰርቢስ እንደሚያመልጥ ረስተነዋል፤ ቆዬን ከረሳን፤ ሰርቢስ ያመለጠን እንደሆነ ስልክ ተደውሎ እንትና ና እና ውሰደኝ ማለት ስለሚቻል ማለት ነው። ያመልጣል እንዴ ሰርቢስ? አለ እንዴ እንደዚህ ዓይነት ነገር? አረሳችሁም አለቆች?" ከዚህ ላይ ዓይናቸው እራሱ የጉድ ነው። 

"ቀጥሎ ደግሞ ሰርቢስ ሲያመልጠው አለቃ ታክሲ ኮንትራት ይዞ መሄድ ይችላል፤ የእሱ ትንሽ ሻል ያለ ነው፤ ያቺ ሴት ምን አልበት ቦርሳውን እረስታ ሊሆን ይችላል፤ ልጅ ስታበላ ቁርስ ብዙ ጣጣ አለ ገንዘብ የለም በእግር እዬኳተነች 30 ደቂቃ መጥታ ሊሆን ይችላል እባካችሁን ላይ ስትሆኑ በዛ መነጸር ታች ያለውን አትመልከቱ ታችን ዝቅ ብሎ ማዬት ያስፈልጋል የሰውን ጉስቁልና እና ኑሮ …“

 ዛሬ ዕለት ሰንበትም ያሉትም ይህንኑ ነው … ላዩን ስናይ ባጅተናል እንዲህ ታች ወረድ ብሎ ማዬት ያስፈልጋል ነው ያሉት ...አሁን ወደ ቀደመው ... 

„ለምሳሌ አለቆች ሁናችሁ አንድ ሴት መጥታ ልጄ ታሞብኛል እና ሆስፒታል ልወስደው ነው ስትላችሁ አንዳንዱ ሂጂ የሀኪም ወረቀት አምጪ፤ አንዳንዱ ኋላ ተውስጂዋለሽ አሁን ሥራ ላይ ነኝ ይላል፤ በጣም ጠጠር ያለ እንደሆነ አንዳንዱ ደግሞ ትንሽ ሻል ያለው ሂጂ ይላል፤ ሦስቱም አይረቡም። ለምን መሰላችሁ? ሰው እኮ የታመመበት ልጅ ነው፤ ታመመብሽ እንዴ? የት ነው የተኛው? መኪና አለሽ? ብርስ ይዘሻል? ላድርስሽ ካላለ አለቃ ምኑን አለቃ ሆነው?"

ለእኔ ይህ ከዴሞክራሲ በላይ ነው። ለዚህ ነው የሽግግር መንግሥት፤ የተጽዕኖ ፈጣሪዎች አንድነት መንግሥት የሚሉ ወገኖቼ መንፈስ ግጥሜ ሊሆን የማይችለው። እኔ ያለምኩት ብቻ ሳይሆን ላልመውም ከማልችለው የሃሳብም፤ የፈጠራም፤ የጥልቅነትም፤ የሰብዕነትም፤ የተፈጠሯዊነትም፤ የእኛነትም በላይ የሆነ ሙሴ ልዑል እግዚአብሄር ለአላዛሯ ኢትዮጵያ ስለሰጣት ውስጤ ለማድረግ ሲጀመር ጀምሮ የእኔ ለማለት አብይ ኬኛ! የፈቀድኩት፤ በዚሕው እድምታ ነው። ከማንም እና ከምንም ጋርም ላወዳድረው፤ ላነጻጽረው፤ ላጠጋጋውም አልችልም። ምክንያቱም ከውስጤ ነው ያጠናሁት። ሰሞናቱም ላይ አብይን ፍለጋ ላይ የከረምኩት የመሻቴን ሰቅ ስለማግኘት ነበር። 

ዶር አብይ አህመድ አሁን የሚያደርጉት ማናቸውም መልካም ነገሮች ልብጦች፤ አልርቲፊሻሎች፤ ቅቦች አይደሉም። ሲፈጠሩ ይህን ሆነው ነው የተፈጠሩት። አሁን ያለው ሁኔታ አቅማቸውን ተግባር ላይ ለማዋል ብሄራዊ ዕድል ማግኘታቸው ብቻ ነው ልዩነቱ። እንጂ ዶር አብይ አህመድ ማለት እኒህ ናቸው። አንድ ጋዜጠኛ የራሰን ታሪክ ስለመሥራት ወረፍ  ያደረገ ጥያቄ አቅርቦ ነበር አላወቃቸውም፤ አላጠናቸውም። 

ለቀደሙት ምን ያህል ክብር እንዳላቸው እኮ አቶ ሃይለማርያም ደስአለኝ ሲሸኙ ያደረጉት ተግባር ገላጭ ነው። ይሄ ብቻ አይደለም የሳይንስ እና ቴክኖለጂ አውራዎችን ሲያመሰግኑ ሲሸልሙ ላይ ሆነው ሳይሆን እቦታቸው አዬሄዱ ስለመሆኑ ይሄ ቪዲዮው ያመልክታል፤ ቀድሞ ነገር ብዙ ትርጉም ገብ ጊዜ እና ሁኔታ ስላልፈቀደው ብቻ  የማናውቃው ሰብዕና ያለው ጠ/ ሚር ነው አላዛሯ ኢትዮጵያ ያላት። የቀደሙትን ማመስገን ብቻ ሳይሆን ክብር መስጠት መሸለም የ አብይ መንፈስ ስለዚህም ተፈጠረ ማለት እችላለሁኝ በእርግጠኝነት። ጣዕሙን ለማወቅ መፍቀድ ያስፈልጋል። ለዚህ ደግሞ ከወረቀት ጥብቆ አምልኮ ወጥቶ የልዑል እግዚአብሄርን መክሊት ለማዬት ለመቀበል መሻትን ይጠይቃል።  

https://www.youtube.com/watch?v=RLBOF9AO0Aw

Ethiopia - የመወድስ ግጥም ለዶ/ር አብይ አህመድ


ጠ/ ሚር አብይ አህመድ በፊትም ዛሬም ወደፊትም በተሰጣቸው የምርቃት ሰብዕና ልክ ውስጥ የበቀሉ ናቸው። በዛም ውስጥ ያጸደዩ ናቸው። ስለሆነም ዛሬ በሙሃይቱ ቤት መገኘታቸው የምጠብቀው ነው። እሙሃይም እውነተኛው የሱባኤ የአድርሽኝ ድንግልዬን መልስ አግኝተዋል ብዬ አስባለሁኝ። ፍልስቲት እንዲህ ናት። በረከቷ፤ ቦነሷ እንዲህ ነው አይለካም፤ አይመዘነም። አንድ ቀን ደግሞ ቤተ መንግሥት ወግ ደርሶት ከመነኩሲት ጋር ታድሞ ቡና አብረው ሲጠጡ እናያለን። መልካም ነገር እናይ ዘን የተፈቀደልን ዘመን ነውና። ምን አልባትም አድዮን እንቁጢን በዚህ መልክም የደግነት፤ የቸርነት ዓውደምህረት ምርቃት ... እንጠብቃታለን። ለጨርቅ ለበሾችም እኩል ቤተመንግሥታዊ ክብር እና ፍቅር ሲለገሱ።

እውነት ለመነገር ዛሬ ሰው ቅኖች ሁሉ ጉድ እንደሚሉ ነው። ለእኔ አይደንቀኝም። ይህን ኢትዮጵያ ታገኝ ዘንድ ከምርቃቷ ጋር እንዳትተላለፍ ነበር እኔ የሃሳብ ቅንነት መሰባሰብ ስስራ የባጀሁት። ሳተናውሻም አግዞኛል። አመሰግነዋለሁኝ። 

ማናቸውም እሳቸው የሚታትሩበት ዘርፍ ሁሉ ከእውነት እና ከሃቅ ነው። ለዚህም ነው እኔ በኤርትራ እና በኢትዮጵያ ግንኙነት አንዲትም ቅንጣት ጥርጣሬ ሊኖረኝ ያልቻለው።
አሁን ለእኔ ውስጤን ደስ ያለው ነገር ቢኖር ዋንኛው ምክንያት ያ የምሳሳለት መንፈስ በሳሳሁለት ልክ ዳግም አዬው ዘንድ እግዚአብሄር ስለወደደ እና ስለፈቀደ እጅግ ደስ ብሎኛል፤ ሐሤትም አድርጌያለሁኝ። 

አዲስ አባባም ታድላለች፤ አላዛሯ ኢትዮጵያም እንዲሁ። አዲሱ የአዲስ አበባ አስተዳደርም በዚህ ቀና በሆነ፤ ቅን በሆነ ዘመን ላይ ለተወሰነ ጊዜም ቢሆን እስከ የሚቀጥለው ምርጫ ድርስ ዕድሉን በማግኘታቸው ደስ ሊላቸው ይገባል። 

አንድ ሰው ከመልካም ሰው ጋር ለመሥራት ሲታድል ፈጣሪውን ማመስገን አለበት። በዚህ ላይ አቶ ፍጹም አረጋ ከሁሉም የታደሉ ናቸው። ግን ይህን ዕድላቸውን አቶ ፍጹም አረጋ ምን ያህል እንዳከበሩት ባገኛቸው እምጠይቃቸው አመክንዮ ይሆናል?

መቼም በህይወት ልዩ ሥጦታ የሚባለው የሚያሠራ፤ የሚረዳ፤ ውስጥ የሆነ አለቃ ሲገጥም ነው። ሌላው ትርፍ ነው። ኑሮን ኖርኩኝ፤ ለትክክለኛው ድካሜ የተሰጠኝ ማሃዬ ነው ተብሎ በነፃነት ወር ላይ ተቅብሎ ሥራ ላይ ለማዋልም እንዲህ መሰል የእግዜሩ ቅን፤ የእግዜሩ ንጹህ፤ የእግዜሩ ቤተሰብ አለቃ ሲገጥም ብቻ ነው።

ጥሩ አለቃ መንፈስ ነው ለሥራ ወዳዶች ወይንም ሥራ አገራቸው ለሆነ። ሥራ አገሩ የሆነ መሪ ሙሴም ህሊናም አላዛሯ ኢትዮጵያ ስለሰጣት እንኳን ደስ አላት እላለሁኝ።

ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር!
አቤቱ ፈጣሪ ሆይ! ሙሴያችን አደራህን ጠብቅልን።

የኔዎቹ ኑሩልኝ።
ማለፊያ ጊዜ።
ተመስገን!
  


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።