እስኪ ልጅ ጋሻው መርሻ ይሞገት። በምን የመረጃ ጥናት 95% የአማራ ክልል ሰላም ነው እንዳለ አልገባኝም።
እስኪ ልጅ ጋሻው መርሻ ይሞገት። በምን የመረጃ ጥናት 95% የአማራ ክልል ሰላም ነው እንዳለ አልገባኝም። "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን። #እፍታ ። አብን ነፍሱ ስለመኖሩ አላወቅኩም። ስለዚህ ሙግቴ በግለሰባዊ ዕይታ ብቻ ቢሆን እፈልጋለሁኝ። ግን ብዕሬ ከፈቀደች እና ካሰኛት ሳይለንት ዲስክርምኔሽን አልፈጽምባትም። እንዳሰኛ ትሰጥስጠው። #ጠብታ ። ልጅ ጋሻው መርሻ አንዳቤቴ ነው ሲባል ሰምቻለሁኝ። አንዳቤት ለእናት አገሩ ለኢትዮጵያ በየዘመኑ አርበኛ ማፍራት፤ የቤተክህነት ሊቀ - ሊቃውንትን ለእናታችን ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ማበርከት ተመክሮው ቢሆንም፤ እንደ ልጅ ጋሻው መርሻ #ፈንገጥ ያለ ሃሳብ አቅራባ ግን ሰምቼ አላውቅም። ስለሆነም አቶ ጋሻው መርሻን ሳዳምጠው ሁልጊዜ "የአንድአቤት" ሥያሜ ይገርመኛል። አንድአቤትን በአካል አውቀዋለሁኝ። ብዙውን የጎንደርን ቀበሌ መንደሮች በእግሬ እየተጓዝኩ አውቃቸዋለሁ። የአንዳቤት የማይረሳኝ እርጎው ነው። ዛሬ የቅኒት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች ቄራ የሆነው አርሲ ጢቾ አውራጃ አምኛ ወረዳ በተመሳሳይ የተመገብኩትን እርጎ አንዳቤት ላይ አግኝቸዋለሁ። እርጎ ከምለው አንጠልጥዬ በክብር የቅቤ እርጎ ብለው ዕውነቱን ያደረጀዋል። የአንደቤትን ገበሬወች፤ የሴቶች ማህበር እና የወጣቶች ማህበርን አመራር ሳወያያቸው አንድአቤት እንደ ሥሙ ሆኖ ነበር ያገኜሁትኝ። እናቴን የእሽታ ልዕልቴን ለምን አንድአቤት ተባለ ብዬ ከሥራ ወደ ጎንደር ስመለስ ጠዬቅኳት። እሷም ከቤተሰብ የሰማችውን ነገረችኝ። በጥንት ጊዜ ገዢወች እየተዘዋወሩ ነበር ፍርድ የሚሰጡት። አንድአቤትም እንደሌሎቹ ባድማወች የተጉላላ ፍትህ በማጣት የተቸገረ፤ ፍርድ የጎ...