ድንቡልቡሏ #ኳሲዝም ተናፋቂዋ የፍቅር ተፈጥሮ ዓርማዋ #ሙሽሪት እየመጣች ነው።
ድንቡልቡሏ #ኳሲዝም ተናፋቂዋ የፍቅር ተፈጥሮ ዓርማዋ #ሙሽሪት እየመጣች ነው። እግር ኳስን የሥነ - ጹሁፍ ያህል የምወደው አርት ነው። "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን። #ምዕራፍ ፲፱። ደም ግባቷ ከሩቁ ይስባል። ጠረኗ ዓራቱን ማዕዘን በጹዑም ዝባድ #ማዕዛ ያውዳል። ድለቃ ናፍቋተኛዋ፤ በግራ ቀኝ እና በማህል ዳኛ ሰበር ችሎት የምትዳኜው፤ የመረብ ግርማ ሞገስን ከዙፋኗ ላይ በክብር ጉብ ብላ ፍንደቃ የምታስፈነድቅ፤ ስቃ ሲቃ የምትፈጥር፤ ዕንባ ፈጥራ ተስፋን የምታቆላምጥ፤ መሸነፍን እና ማሸነፍን እጀቡኝ ብላ፤ ሙሽራው ከነሚዚወቹ ተንቆጥቁጣ የምትጠበቃዋ የፊፋ ሙሽራ እንሆ …… የጸሐይ ብርሃን ፏፏቴ ያህል የምትናፈቀው ወይዘሪት ድንቡልቡልሻ #ኳሲዝም በሦስት አገራት ላይ ዘንድሮ ትደምቃለች፤ ታብባለች፤ ትፍለቀለቃለች። ሳቅን በድል ኩላ ፋክክሩን አህዱ ለማለት ሱባዬ ላይም ባጅታለች። የሚሊዮኖች ፍቅረኛ፤ የብሄራዊነት መጽደቂያ፤ የሉዓላዊነት መከበሪያ እና ማስከበሪያ ከሊቅ እስከ ደቂቅ አሰልፋ ስትደለቅ - ስታስደልቅ፤ ስትደለቅም፤ ስታፈነገጥ ስታሯሩጥም፤ ከመረብ ጋር ስትጋባ ትዕይንቷ ልብን አንጠልጥሎ ሐሤትን በምዕላት #ይናኛል ። ተናኜ እኮ ናት። ቢሯዋ አጤ ፊፋ መሰናዶውን በተሟላ ንቃት እና አቅም ማጠናቀቁን ዓውጇል። አያይዞም ህገ - መንግሥቱን ይፋ አድርጓል። የህገ - መንግስቱ መንፈስ ሰብዓዊ ተኮር ሆኖ ወደ #የሰብዓዊ መብት ተሟጋችነት ያዘነበለ ነው። በሌላ በኩል ስሜትን ለመቆጣጠር የሄደበት እርቀትም አንቱ ያሰኜዋል። የአጤ ፊፋ የክፋ ሃሳብ አቀንቃኝ ድርጊቶችን ለመቋቋም፤ የመብት ጥሰት አደጋ እንዳይገጥመው ቅድመ ጥንቃቄው ...