#ኡራኖስ ላይ የሚኖረው የኢትዮጵያ ሴቶች ፌድሬሽን መግለጫ?

 

#ኡራኖስ ላይ የሚኖረው የኢትዮጵያ ሴቶች ፌድሬሽን መግለጫ?
 
የፌዴሬሽኑ መግለጫ 👉 ሕዝብ ያሳየው ታማኝነትና ቁርጠኝነት
 
"አቤቱ የቤትህ ቅናት በላኝ።"
 
#እንዲህ የሚባል ተቋም #ኢትዮጵያ አላትን?
 
የምር ነው በትህትና የምጠይቀው? የት የነበረ ይሆን ይህ ተቋም የሚኖረው ጁቢተር ወይንስ ኡራኖስ ማርስ ወይንስ ሜርኩሪ ላይ? የኢትዮጵያ እናቶች ሲከፋቸው፤ ሲያለቅሱ፤ በተፈጥሮ ይሁን በሰው ሠራሽ ችግር ሲገረፋ የት ነበሩ? በግፍ ሲታገቱ፤ አራስ ቤት ህይወታቸው ሲያልፍ፤ ተፈናቅለው ሲንከራተቱ? ሲርባቸው - ሲጠማቸው፤ ሲታረዙ እራፊ ሲያጡ ተቋሙ የት ነበር? ዛሬ ለሠርግ እንደምን ብቅ አለ ደፍሮ? 
 
ኢትዮጵያ ለዚህ በምንም ደረጃ ላለ ተቋም #በጀት መድባለችን? በውነት እምዬ በጣም ደልቷቷል ማለት ነው። የእናቶች ዕንባ እኮ የቧንቧ ውሃ አይደለም። በዓለም ውዱ የዕንባ ጠብታ ነው። 
 
ከኢትዮጵያ እናቶች ዕንባ መከፋት ጎን ቆሞ ፊት ለፊት ወጥቶ ያልሞገተ፤ የግንባር ስጋ መሆን ያልፈቀደ ያልተገባ ሥያሜን ይዞ ሚዲያ ላይ የሚወጣ ምን ይባል ይሆን? የወጣቶችን አይቻለሁኝ። የእነሱ ዕድሜያዊ ጉዳይ ስላለበት ዘልየዋለሁኝ።
ሴቶች ግን በጥቂቱ ………
 
1) የአገር ኃላፊነት፤
2) የትውልድ ኃላፊነት፤
3) የአደራ ኃላፊነት፤
4) የታሪክ ኃላፊነት፤
5) #የሰላም ኃላፊነት፤
6) #የፍቅር ኃላፊነት፤
7) የእናታዊነት ሁለገብ ኃላፊነት፤ እናታዊነት ከፖለቲካ ርዕዮት በላይ ነው። 
ስምንተኛ) የተፈጥሯዊነት ኃላፊነት ያለባቸው ናቸው።
 
ለእኛ ለሴቶች የተሰጠን ሰማያዊ ኃላፊነት #የሰብዐዊ መብት ተሟጋችነትን ነው። ለዛውም በጀት ተመድቦ። መሃያ እየተከፈለ። የተሟላ አገልግሎት እየተገኜ ለሴቶች መከፋት #ውስጥን አለመስጠት ፈቅዶ #መበደል ነው። #እርግማንም
 
ሴት ሊቃናትን በሚመለከት ማሄስ ላይ ቁጥብ ነኝ። ፈተናውን ስለማውቀው። ይህ ሲባል ግን ዕንባ ላይ ሳይገኙ ሠርግ ላይ ለሴቶች ሰብዕና እንደ ተቋም ያስከፋል። ኃላፊነት መቀበል ቀላል ነው። በኃላፊነቱ ልክ ዲስፕሊኑን አክብሮ በውስጡ መገኜት ግን እንዲህም ይከብዳል። አንዲት ጠብታ የሌለበት እንደዚህም ይገጥማል። ከውስጤ አዝኛለሁኝ። 
 
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ ማህበረ ቅንነት። አሜን።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
06/06/026.
 
ፍቅር ሲያልቅ፤ ትዕግስት ይሰደዳል።
ትዕግሥትም ሲያልቅ፤ ፍቅር ይሰደዳል
See less

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።