ልጥፎች

ከጃንዋሪ 10, 2026 ልጥፎች በማሳየት ላይ

እቴጌ ጎንደር ሰላምሽ #በመዳፍሽ ነው። የውስጤ ሆይ! እንደ ውርስሽ #አደብ ላይ ከትሚ።

ምስል
  እቴጌ ጎንደር ሰላምሽ #በመዳፍሽ ነው። የውስጤ ሆይ! እንደ ውርስሽ #አደብ ላይ ከትሚ።   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።     እቴጌ ጎንደር ሰላምሽ #በመዳፍሽ ነው። የውስጤ ሆይ! እንደ ውርስሽ #አደብ ላይ ከትሚ።   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።   #ምዕራፍ ፲፰   እቴጌዋ ዘመነ -አስተርዬ #ምችት ይለው ዘንድ ሰላምሽን ሰንቂ። ከፈጣሪሽ ጋር የሚኖርሽ ሃዲድ የሚዋብበት ሆነ የሚለመልምበት ዘመነ - አስተርዬን እንደ አባት አደሩ #ስቀሽ ለመቀበል ተሰናጂ። መገበርሽን ለማን? ማገዶነትሽን ስለምን ብለሽ እሰቢው? መገበርሽን ለማስቆም ቁልፋ ከእጅሽ ከመዳፍሽ ነው። "ወልቃይት ብረሳሽ ብለሽ" ስትነሺ ከጎንሽ የነበረ #የቅኔው ጎጃም ሙሉ ህዝብ ብቻ ነው። ግብርነቱም መኖሩን ፈቅዶ እና ወዶ ለሰማዕትነት የሰጠ ድንቅ ህዝብ ነው ቅኔው ጎጃም። በሙሉ መረጃው ከእጄ ይገኛል። ልዩዬ ስለሆነ።   ስለወልቃይት ጠገዴ ካነሳሁ ዘንድ ሰላማችሁን ላስከበራችሁ የማስተዋል ባለክህሎት ጀግኖቼ ምስጋናዬ በክብር ይድረሳችሁ። #ለእኛ የህሊናችን ቁልፍ ጉዳይ የመካከለኛው ምስራቅ እና የአፍሪካ ቀንድ ቁልፍ የፖለቲካ አናታዊ ጉዳይ ነገረ ወልቃይት ጠገዴ የወገራ እና የስሜን አውራጃ ጉዳይ ብቻ እና ብቻ ነው።    #ስሚኝማ ወለላዬ ጎንደሪና።    ማን ይሁን? ምን? ከአንቺ ጋር አሳሩን ያልተጋራ ስለአንቺ ሊበይን፤ ከተውንም ልትፈቅጂለት አይገባም። ዘመነ ህወሃት እንደሆን የቀራንዮ የድቅድቅ ጨለማ፥ መተንፈሻሽ ፈተና ላይ የነበረበት ዘመንሽ ነበረ። የአንድ አውራጃ ያህል ክብር አልነበረሽም። ይህን በጥልቀት እሰቢው። ስለክብርሽ፤ ስለዝናሽ፤ ስለልቅናሽ፤ ስለልዕልናሽ፤ ስለ ...

የባህር በር ጥያቄ 100% #የእኔም ነው። የወደብ ጥያቄ 100% #የኔም ነው። ጥያቄው #የሚሊዮኖችም ነው።

ምስል
      የባህር በር ጥያቄ 100% #የእኔም ነው። የወደብ ጥያቄ 100% #የኔም ነው። ጥያቄው #የሚሊዮኖችም ነው።   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።   #ምዕራፍ ፲፰   ሰሞኑን ከኤርትራ መንግሥት በሚሰጡ መግለጫወች ዕድምታቸውን ሳጠና የባህር በር ጥያቄ፤ የወደብ ጥያቄ የኢትዮጵያ ተፈላጊ እና የህልውና ጥያቄ ሊሆን የማይችል፤ የኢትዮጵያ ዜጎች ጥያቄም እንዳልሆነ፤ የአብይዝም ሰብዕና ሌጋሲ አስቀጣይ እንደሆነም የሚገልጽ ዓይነት ነው። እንደዚህ የኤርትራ መንግሥት ባያስብ ጥሩ ነው። የአንድን የነፃነት የፊደል ገበታ የሆነችን አገር ብሄራዊ ጥያቄ ከደረጃ በታች ባያወርዱት ጥሩ ነው፤ የኤርትራ መንግሥት ሊቃናት እና ደጋፊ ወገኖች። በኢትዮጵያ ሥም ያሉ፤ ለኤርትራ መንግሥት የበለጠ የሚሳሱ ሰብዕናወችን ሳይ በውነት አዝንላቸዋለሁኝ።    በዘመነ ህወሃት የወልቃይት፤ ጠገዴ ጥያቄ ሲነሳ አንድነት ፓርቲን የተቀላቀሉ የአማርኛ ቋንቋ ሊቅ ተጋሩ ይህ "የገብያ ግርግር ነው። 100% "የአማራ ሊቃናትም የማይገዙት ነው" ብለው በሰጡት መግለጫ ማንነት በገብያ ህግ የማይተደደር ነው፤ ምክንያት ማንነት ሸቅጥ ስላልሆነ በሚል ሞግቻቸው ነበር። ዛሬ ላይ ሆነው ሲዩት የወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ ከኢትዮጵያም አልፎ #ቀጠናዊ ዘውድ ደፍቷል።    ደክሜበታለሁኝ። ተመስገንም ብያለሁኝ። ዛሬ ያ ቀጠና ሰላሙ ተረጋግቶ እፎይ ብሏል። " አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁኝ" ስንት ነፍስ የተገበረበት፤ ስንት መዋዕለ ንዋይ የፈሰሰበት የቀይ ባህር ወሳኝ ቀንድነታችን ጉዳይ፤ #ተዘግቶ የቆዬን አጀንዳ ይለፍልህ ብለው // ይለፍ የሰጡት ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ናቸው። በፋኖ ጠንካራ ንቅናቄ ጋር ተያይዞ የመጣ ውሳ...