ልጥፎች

ከጁላይ 23, 2026 ልጥፎች በማሳየት ላይ

#ዋ! የዬኔታ ልቅና #ራስ #ዋሸራ! ሆይ! ሆይ!

  #ዋ ! የዬኔታ ልቅና #ራስ #ዋሸራ ! ሆይ! ሆይ!   "አቤቱ የቤትህ ቅናት በላኝ።"   #ምዕራፍ ፲፱።   "ዋሸራ (ደብረ ምዕራፍ ዋሸራ ማርያም) በኢትዮጵያ፣ አማራ ክልል ጎንጅ ቆለላ ወረዳ (ምዕራብ ጎጃም) የሚገኝ ታሪካዊና መንፈሳዊ ቦታ ነው። ከአዲስ አበባ 426 ኪሎ ሜትር እና ከባሕር ዳር 82 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው ይህ ስፍራ፣ በርካታ ሊቃውንት የተገኙበት የቅኔ መገኛ ማዕከል በመባል ይታወቃል።ቁም ነገሮች፡የቅኔ አምባ፡ ከዋሸራ የወጡ የቅኔ ሊቃውንት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ታላላቅ ገዳማትና አድባራት በማስተማር ቅኔን አስፋፍተዋል።የቅኔ ዩኒቨርሲቲ፡ የቅኔ ጥበብን ለማሳደግ "የቅኔ ዩኒቨርሲቲ" ማዕረግ የተሰጠው ሲሆን፣ ታላላቅ የበዓላት በዓላት ለምሳሌ የአስተርእዮ ማርያም በዓል እጅግ በደማቅ ሁኔታ በቦታው ይከበራል።"   #ብሎት መሆኑን አውቃለሁኝ። በዓለም ውስጥ ላለነው፣ ለኢትዮጵያ የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች። ግን እንዲህ ህሊናን የሚያፈርስ ክስተት ሲኖር ቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ጉባኤ ጠርቶ ቤተ - እግዚአብሄራችን ጋሻ፣ ጦሯ፣ ድሮኗ፣ ኒኩለሯ፣ ባሩዷ፣ ትጥቅ እና ስንቋ #ጸሎት ነው። ፆም ነው። ሱባኤ ነው። ስግደት ነው። ምህላ ነው። ልመና ነው።    እግዚአብሄርን የተረገምንበትን ከልቶ ምህረት ይልክ ዘንድ ተንበርክኮ #ድሆ መለመን አያሽላንም። ይህን ማታዊ ዜና እንዲያስታግሰው፣ እንዲያቆረው ለሁሉ ጌታ አማኑኤል በዕንባ መጠየቅ ይገባ ይመስለኛል። አልቦሽነት ነገን፣ ማግሥትን አልቦሽን #ስለሚቀልበው ።   የወል ሱባኤ ጥቅሙ የአንዱ ባይደመጥ ከብዙኃን የእኔ ቢጤ ኃጣን አንድ #ዕዮባዊ አይጠፋም እና የወል ሱባዬ መያዝ የተገባ ይመስለኛል። እኔ ቅዱ...