ልጥፎች

ከኦክቶበር, 2023 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ግሥ የሌለው መሪነት አልቦሽነት።

ግሥ የሌለው መሪነት አልቦሽነት። "ከንቱ የከንቱ ከንቱ ሁሉም ነገር ከንቱ።" ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ #ማሰሪያ #አንቀጽ የላቸውም። የድርጊቱ መነሻም መዳረሻውም ከኦዲዬንሱ ውጪ ነው። አሁን አሁን ሳስበው መሪነት ጽንሰ ሃሳቡ የገባቸው አይመስለኝም። በሌላ በኩል #የመሪነት #ስሜቱንም የተረዱት አይመስለኝም። በተጨማሪነት የመሪነት #መነሻውን ያወቁትም አይመስለኝይ። ይህም ብቻ አይደለም #የመሪነት #ቅደም ተከተሉንም የተረዱት አይመስለኝም። እርግጥ እሳቸው ያቀዱትን እዬከወኑ መሆኑን አያለሁኝ። ያ ማለት ግን የአገር መሪነቱን ሚና እዬተወጡ ነው ማለት አይደለም። መሪነት ለእሳቸው 365 ቀን መናገር፤ ለሳቸው ደስ የሚላቸውን ፕሮጀክት የድሎት አቅዶ መፈፀም፤ አስደሳች እና አዝናኝ የሆኑ ጉዳዮችን ነጥሎ ትኩረት መስጠት መሪነት መስሏቸዋል። በፍፁም የመሪነትን #ስሜቱን አልተረዱትም። በፍፁም። መጓዝ፤ ንግግር ማድረግ፤ ድንገተኛ ክንውኖች ላይ አቅምን ማፍሰስ መሪነት መስሏቸዋል። የሠፈር መሪ አይደሉም። የዓለም የሰላም አባት የሚመራውን አገር ቀጠናውን በሰላም ማስተዳደር የተሳነው፤ እወክለዋለሁ በሚለው ኦሮምያ ክልል እንኳን ከህዝቡ ጋር የተቆራረጠ። ከበሻሻ በስተቀር በዬትኛውም ሁኔታ የወጡበት ማህበረሰብ ውክላዊ ፖለቲካዊ ሂደት አብሰንት የሆኑ። የሚገርመኝ እሳቸው ከተደሰቱ፤ እሳቸው ከደለቁ ከ110 ሚሊዮን ህዝብ በላይ የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ስሜቱ ምን ይሁን ምን ጉዳያቸው አይደለም። እረፍት አልባ የሚታትሩት ለራሳቸው ፍስኃ ስለመሆኑ ነው እኔ እማስተውለው። ህዝቡ ሲከፋው አይከፋም። ሲያዝን አያዝኑም። ሲራብ አይራቡም። ሲያለቅስ አያለቅሱም። ለእኔ የቤተ መንግሥቱ #ሃውልት ወይንም ማስዋቢያ ዲኮሬሽን ሆነው ነው የሚታዩኝ። ኦሮሞ ጠቅላይ ሚር ሆነ።

ከአሰር አቮል አይመጣም፤ ከሻገታም ትኩስ እንጀራ አይታለምም እናም አይስጉ።

  ከአሰር አቮል አይመጣም፤ ከሻገታም ትኩስ እንጀራ አይታለምም እናም አይስጉ።      "ህግ ተላላፊወችን ጠላሁ።" እጅግ በተደጋጋሚ ጊዜ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ከዛው ከሻገተው የኢህዴግ መንፈስ አዲስ ኃይል ወጥቶ ይፈነቅለኛል ብለው ይሰጋሉ። መንገዱን እናውቀዋለን አትሞክሩት ሲሉ አዳምጣለሁኝ። በዚህ ቅዠት እነ ቲም አንባቸው ተመነጠሩ። የአማራ ልጆች ተጋዙ፤ ተሰወሩ፤ ታገቱ፤ ተረሸኑ፤ ተሳደዱ። ሁልጊዜ የሚያባንናቸው መፈንቅለ መንግሥት ከዛው ከዛገው ብርታቸው ውስጥ ነው። እኔ ደግሞ እላለሁ። አይስጉ። ከሽውራር የምንጠብቀው ትፍስህት የለም። ቢሞከርም ይጨነግፋል። ምክንያት ኤክስፓዬርድ ያደረገ ስለሆነ። በጣም በተደጋጋሚ በእናንተ ጥረት ብቻ ለውጥ እንደመጣ ያስባሉ። ዕሳቤው ልሙጥ ነው። ከዛ የበሰበሰ አካል ቀጣይ አካል እንዲቀጥል የተደረገው የእኛ የወል ስምምነት ስለነበረ ብቻ ነው። ኢትዮጵያዊነት ሱሴ ነው የሠራው ደባ ነው እንጂ ኢህዴግ ታምኖ በዓለም ዓቀፍ ማህበረሰቡ ይሁንታ ያገኛል ተብሎ አይታሰብም። ጠቅላይ ሚር አብይ ስላልነበሩበት ያልገባቸው ሚስጢር ይህ ነው። ሁለተኛ የሚጭበረበር የለም። ፈፅሞ። እናማ ተፈነቃቅላችሁ ኃይል ነን ብሎ የሚከሰት ማንም ይሁን ማን የሚመጣ አካል ተቀባይነት የለውም። ኢትዮጵያ ሙሉ 60 ዓመት ረግረግ የወደቀችበት የመከራ ሥረ መሠረትን የሚነቅል ሂደት ነው እኔ በግሌ የምሻው። ያ ደግሞ ሥር ነቀል ለውጥ በአዲስ ኃይል እና ተፈጥሯዊነት መንፈስ። ትራፊም፤ ቅርጥምጣሚም አያሰኜንም። በሌላውም በኩል ህልም ሊኖር ይችላል። ያም አይሆንም። ከግንቦት 7 በላይ ሚሊዮኖችን መንፈስ የተቆጣጠረ አልነበረም። ቻለ? አልቻለም። የህወሃት መሸኜት ለሁሉም ዱብ ዕዳ ነበር። ሥራ ይጠይቃል። ለዚህም ነው ሲግለበለብም፤ ሲፈላም፤ ሲንተከተክም በጥሞ

ይድረስ ለEthiopian National Dialogue Commission/የኢትዮጵያ ... EthioNDC ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን/ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

ምስል
  ይድረስ ለEthiopian National Dialogue Commission/የኢትዮጵያ ... EthioNDC ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን/ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ። "የቅኖች ፀሎት ግን በእርሱ ዘንድ የተወደደ ነው። የኅጥዕ መንገድ በእግዚአብሄር ዘንድ አፀያፊ ነው።" (መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፱፭ ቁ ፰ - ፱) የተከበርከው ብሄራዊ የምክክር ኮሚሽን ሆይ!       #ዕፍታ ። ዘለግ ያለ አቤቱታም፤ ሙግት ነክ ጉዳይ ነው። የማክበር ሰላምታዬን በቅንነት አቀርባለሁኝ። እንዴት ናችሁ? ዬተነሳችሁበት የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ፕሮጀክት ይሳካላችሁ ዘንድ ምኞቴ ነው። ዕውነት እና ፋክት ሸንጋይ ዬሚሹ ባይሆንም፤ ዕውነት እና ፋክት አጃቢ ሠራዊት የለላቸው ቢሆኑም ዕውነት አለን፤ ፋክት አለን ለዛም እንተጋለን ማለት መብት ነውና፦ ይህን ተቀብሎ ግን ሊሳኩ የማይችሉ ሎጅኮችን አቅርቦ መሞገት ደግሞ አስፈላጊ እና መሠረታዊ ጉዳይ ይሆናል። #ውስጠት ። በወፍ በረር እማዳምጣቸው ጉዳዮች አሉ። የአማራን ችግር በተለይ አሁን ያለውን የሞት የሽረት የፋኖ ዕፁብ ድንቅ ተጋድሎ እንዳኛለን፤ እናስማማለን ብላችሁ መነሳታችሁን አዳምጣለሁ። ለመሆኑ ልትታገሉበት ከተሰናዳው ሰነድ አንቀጽ ውስጥ "ፋኖ" የሚል ኃይለ ቃል አለን? የዚህን መልስ መስጠት ስትችሉ፤ እራሱ መልሱ የስኬታችሁ ወቄት መሆን ይችላል። ብዙ ተቋማት የሚወድቁት መሠረታዊ ምክንያት በማኒፌስቷቸው የፖለቲካ ድርጅት ከሆኑ፤ ማህበራት ከሆኑም አታጋይ ሰነዶቻቸው ላይ የሌሉ አቅም እና ጉልበት ሲመጣ ዘለው እንዋኝ ሲሉ አላዋቂ ሳሚ ይሆኑና ሰብዕናቸውም ተቋማቸውም አብሮ ይተናል። የትኛውም ተቋም፤ የትኛውም የፖለቲካ ድርጅት #ከሞረሽ በስተቀር አማራ የሚል ኃይለ ቃል በሌለበት የሐምሌ 5ቱ የአማራ የማንነት እና የህል

#የአማራ ማህፀን የ30 ዓመት ህማማት አቶ ደመቀ መኮነን።23/11/2023 ዬተፃፈ ነበር።

ምስል
  23/11/2023 ዬተፃፈ ነበር። #የአማራ ማህፀን የ30 ዓመት ህማማት አቶ ደመቀ መኮነን። ዕለተ ሰንበት ማዕዶተ ርትህወሰባዕዊነት በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። "ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁ።" (ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯) የአማራ እናት ማህፀን አንድነት ነኝ ሲል ለዛ ማገዶ እሷ ናት።   የዜጋ ነኝ ሲባልም እሷ የቄራ ናት። የብሄራዊ ነኝ ሲባልም የልጅ ልኳንዳ ቤት አቅራቢ እሷ ናት። አማራ ነኝ ብሎ ሲመጣም እሷ ናት። ለእሷ መገደል፣ መፈናቀል፣ ለልጇ መታገድ ግን አንድም ከጎኗ የሚቆም ድርጅት የለም። አንድም። አንድም የለም። እንደ ግለሰብ እምንቆም ብንኖርም የቆምንለት ነፍስ እኛኑ ተዋጊ ሆኖ ያርፋልዕድሉን አግኝቶ ለወግ ሲበቃ። እኔ እምለው አንድ ነገር አለኝ። ይሳካለት እና ይካደኝ። አሁንም እምለው ይህንኑ ነው። እኔው ልማገድ የቁሩት ከሞት ይትረፋ እና ይካዱኝ። መካዱ ብቻ ሳይሆን ይታገሉኝ። ችግር የለም። የእነሱን ትቼ ለባለተረኞች ባለ ካቴና አይታክቴ ደግሞ እንደ አሙሏ ትማገዳለች። ስለ አቶ እስክንድር እና ሰርኬ የዛሬ 15 ዓመትም ከጋዜጠኛ ብያንካ ጋር እታጋል ነበር ዛሬ ብቻዬን እታገላለሁኝ። ይኽው ነው ጥሪዬ። አያውቀኝ፣ አላውቀው። ሆላንድ መጥቶ ነበር። አልሄድኩም። ዙሪክ ቢመጣም አልሄድም። የሆነ ሆኖ እነኝህ ተሰውረው የቀሩ የአማራ ልጆች ናቸው። የማናውቃቸው ብዙ ናቸው። በወለጋ ብዙ በጣም ብዙ። በነገሌ ቦረናን አሁን ስለተቆጣጠሩት ብዙ ይኖራሉ። ህወኃት በያዛቸው በስሜን ወሎም እንዲሁ። የአማራ እናት ማህፀን ቄራ ነው። ይህን ለማስቆም የረባ አስተሳሰብ ያለው የፖለቲካ አቅም የለም። ትነት ብቻ። በቃ ትነት ብቻ። መጀመር እንጅ ፍፃሜ አልቦሽ ዳንኪራ።
ምስል
  23/10/2021 ዬተፃፈ። #የአቶ አባዱላ ገመዳ ቤርሙዳ ትርያንግል ምንዱባን! #መርዷችሁ ለካስ እንዲህ ይናፍቃል። ዕለተ ሰንበት ማዕዶተ ርትህወሰባዕዊነት በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁ። (ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯) የአማራ እናት መሃፀን መርዶ እንደ ናፈቀው ደረቀ እንሆ ደም እንደ አረገዘ አለ እዬማቀቀ በገዳ አፈና እንዲህም ነቀዘ ተስፋውም በረደው ሆነ ቀዘቀዘ። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 23/10/2021 የት ናችሁ? ምን አደረጓችሁ? እዮር ሆይ ፍረድእባክህን?

23/1/2021 ዬተፃፈ ነበር። አቤቶ አብን የፎቶ ሾፓችሁ ቋቅ ብሎኛል

  23/1/2021 ዬተፃፈ ነበር። አቤቶ አብን የፎቶ ሾፓችሁ ቋቅ ብሎኛል፣ ያው የቤተ መንግስቱ የቡና ቤተኝነታችሁ ለመኮንኖች መፈታት አውሉት። ቢያንስ። ዕለተ ሰንበት ማዕዶተ ርትህወሰባዕዊነት በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራ በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። "ዝም ብዬ የመከራ ቀን እጠብቃለሁ።" (ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯) 1) አርበኛ መሳንፍትጀግንነታቸውን አውቃለሁ። ግን ተንቤን ሄደን ሂሳብ እናወራርዳለን ሲሉ እረፋ ብዬ ተግሳፅ ፃፍኩኝ። ወቅንን ጠብቁ፣ ዳሽንን ጠብቁ፣ ደባርቅን ጠብቁ፣ ደባርቅን ጠብቁ አልኩ። የሆነውን አያችሁ ወቅን ጭና አጅሬ ድረስ ሄደው ያን የመሰለ ጭካኔ አስታቀፋን። ግን ትርፍ ንግግሩን አስቆምኩት። በእኔ ቤት ቀልድ የለም። አልወድም እኔ መንጠራራት። የፈለገ ቢመላ ቢተርፍ ሰው በልኩ መኖር አለበት። ከእኔ ቤት የሚደፋ ነገር የለም። ግማሽ አፍል ቢበላሽ። የተበላሸውን የአፍል ክፍል ቁርጥ አድርጌ ጥዬ ቀሪውን እጠቀምበታለሁ። እራሱ ስገዛ ባዮ ነው እምገዛው ውድ ነው በቁጥር ነው እምገዛው። ውኃ ስጠቀም። እዬከፈትኩ እዬዘጋሁ ነው። ካንፕ እያለሁ። ክፍሉን ሁሉ እዬዞርኩ አላግባብ የበሩ መብራቶችን አጠፋለሁ፣ አላግባብ የሚፈሱ ውኃወችን እዘጋለሁ። ኃላፊነት በዬትም ሁኔታ ነው ሊኖር የሚገባው። 2) አቶ ጋሻው መርሻ ደቡብ ጎንደር እንደዛ ተዝረክርኮ ሰሜን ጎንደር አሰኜው እና ደባርቅ ተከሰተ ተባለ። ፃፍኩኝ። የምታለዘው ነገር ካልኖረ አልሄድካትም አልኩ። የሆነውን አያችሁ የጀምላ መቃብር። አቅሙ ካለው ካለሙያው ገብቶ ፎቶ ከሚደረድር፣ ከሚያስደረድር የተደራጀበትም ተልዕኮ ለኮረጆ ማድረጉን ስላስተዋልን እስኪ ባለሙያወችን መኮንኖችን ያስፈታ። "አንድ አማራ ለሁሉም አማራ" ብሎን
ምስል
  23/1/2021 ዬተፃፈ #እናንተስ አዲስ አበቤ አይደላችሁንም። #ግን የማን ናችሁ? #ማን ነው ባለቤታችሁ? ግን ባልደራስ ስለአዲስአበቤ አይደለምን? ዕለተ ሰንበት ርትህወሰባዕዊነት በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። "ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁ" (ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯) እነኝህ የእኛ ናቸው። ስለ አዲስ አበባ ዝም አንልም ያሉ እንደ ሻማ የቀለጡ ባለቤት አልባወች ናቸው። አቋጥሯቸው። የተሰውም አሉ። 5 በጠራራ ፀሐይ።      ፎቷቸው ሥማቸው የለንም። ፎቷቸው ሥማቸው ያለንንም ሰማዕታትም አሉን። ካቴና ላይ ላሉት ቢያንስ ባሊህ ይባሉ። ቢያንስ። የአቶ እስክንድር ነጋ ከእስር ይፈታ ቅድሚያ ይሰጠው እል የነበረው ለዚህ ነበር። ያን ድርጅቱ አልፈለገውም ነበር። ሽሚያው ሌላ ነበር። ዕውነት እማትደፈረው ገመናው ስለታወ ነው። የዶር ገመችስ ደስታ ተልዕኮ ድል በድርብ አሳክቷል ያን የአቶ ዮናስ የኋንስን ሰርግ ክርስትያን ዩቱብ ገብቶ የህሊና ነቀላ እና ተከላው እንደምን እንደተከወነ ማዬት ነው። ሰው ማተቡንክዶ ለሆዱ ካደረ ከምኑ ምኑ ይለያል። ብላሽነት በጠራራ ጠኃይ በሁሉም ዘርፍ የታዬበት ሁሉም ገመናውን ተሸከሞ ደብቁኝ ሊል ሲገባ ገመናው ሳይወሳ የዕለቱ አንበሳ ነኝ ብሎ ሲያገሳ አለማፈሩ ይገርመኛል። በሌላው ይቻላል። በእኔ ግን አይቻልም። ፈፅሞ አይቻልም። ቅርሻን የሚያስተናግድ ሰብዕና የለኝም። ኑሮኝም አያውቅም። ከትናንት ተነስቼ ዛሬን እመዝናለሁ። ትናንትን በቅንነት ሳይ የዛሬ የተግባር ብልጫ እሻለሁ። ዛሬን እዬገደሉ ትናንት፣ ትናንትን ገድሎ ዛሬ የለም። አቶ እስክንድር ነጋ ይሁን፣ አቶ ስንታዬሁ ቸኮል፣ ወሮ ቀለብ ስዩም ትሁን ወት አስካለ ደምሌ ዕዳ የለ

23/10/2021 ዬተፃፈ ነው። ፕ. ዶር መራራ ጉዲናም የጠቅላይ ሚኒስትርነትን ቦታ ምኞተኛ ናቸው። ቢሯቸው ግን ዕብድ የዘራው አዝመራ …… መጥኔ ለኢትዮጵያ ……… #ማደራጀት።

ምስል
  23/10/2021 ዬተፃፈ ነው። ፕ. ዶር መራራ ጉዲናም የጠቅላይ ሚኒስትርነትን ቦታ ምኞተኛ ናቸው። ቢሯቸው ግን ዕብድ የዘራው አዝመራ …… መጥኔ ለኢትዮጵያ ……… #ማደራጀት ።     ማደራጀት በብዙ መልኩ ይከወናል። መስከ ብዙ ህብራዊ የሆነ የሙያ ዓይነት ነው። በማደራጀት ውስጥ ሰውን ማደራጀት ብቻ የሚመስላቸው ሊኖሩ ይችላሉ። በህክምና ውስጥ ማከም ብቻ የሚመስላቸውም ይኖራሉ። በማስተማር ውስጥም የቾክና የጠመኔ ቢበዛ የቀይ እስክርቢቶ ውሎ የሚመስላቸው ይኖራሉ። አይደለም። በመምህራን ውስጥ የወላጅነት፣ የትውልድ ግንባታ ግዙፍ ድርሻ አለ፣ በህክምና ውስጥ የሰባዕዊነት መጠነ ሰፊ ድርሻ አብሮ አለ። እያንዳንዱ ሙያ ኤቲክሱ በሚፈቅደው ውስጥ ብዙ ተፈጥሮ ተኮር መልካም ጅረቶች አሉ። በማደራጀት ውስጥ የመጀመሪያው አህዱ ጉዳይ እራስን ማደራጀት ነው። ከዚህ የሚቀጥሉት ሃሳብን፣ ራዕይን፣ ፍላጎትን፣ አቅጣጫን፣ ትልምት፣ ውሳኔን፣ አቋምን ማደራጀት ይጠይቃል። አንድ መፅሐፍ ፀሀፊ ቢጋር ይኖረዋል የተግባሩ ቅደም ተከተል የሚያወጣበት፣ ዕርዕስ፣ የፊት ሽፋን፣ የጀርባ ሽፋን፣ መቅድም፣ መግቢያ፣ ጭብጥ ማጠቃለያ፣ መፍቻ እነኝህ በምዕራፍ፣ በዋና ዕርዕሰ ጉዳይ፣ በንዑስ ርዕሰ ጉዳይ ይደራጃሉ። ከዚህ በላይ አንዳንድ ፀሐፍት ከተመክሯቸው ሊነሱ እና መዳረሻቸው ያው ሊሆን ይችላሉ፣ በጥናት መሰል ለሚያተኩሩ ጭብጡን የሚያጠብቁ ማጣቀሻዎችን ሊጨምሩ ይችላሉ። ለሁልም የተደራጀ ሃሳብ ያስፈልገዋል። አንድ ሰው ራዲዮ ፕሮግራም ቢኖረው መግቢያው፣ ሙዚቃው፣ ዕርዕሰ ጉዳዩ፣ ማጠቃለያው፣ በዛ በተሰጠው የጊዜ ማዕቀፍ አብቃቅቶ ለመከወን ቢጋር ያስፈልገዋል። ማደራጀት ሲባል ሰውን በማህበር፣ በዕድር፣ በቁቤ፣ ወይ በተቋም ማደራጀት ብቻ አይደለም። የተበተነን መንፈስ የመሰብሰብ፣ የተዝረከረከን ቤት በቅ