ከአሰር አቮል አይመጣም፤ ከሻገታም ትኩስ እንጀራ አይታለምም እናም አይስጉ።
ከአሰር አቮል አይመጣም፤ ከሻገታም ትኩስ እንጀራ አይታለምም እናም አይስጉ።
"ህግ ተላላፊወችን ጠላሁ።"
እጅግ በተደጋጋሚ ጊዜ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ከዛው ከሻገተው የኢህዴግ መንፈስ አዲስ ኃይል ወጥቶ ይፈነቅለኛል ብለው ይሰጋሉ። መንገዱን እናውቀዋለን አትሞክሩት ሲሉ አዳምጣለሁኝ። በዚህ ቅዠት እነ ቲም አንባቸው ተመነጠሩ። የአማራ ልጆች ተጋዙ፤ ተሰወሩ፤ ታገቱ፤ ተረሸኑ፤ ተሳደዱ። ሁልጊዜ የሚያባንናቸው መፈንቅለ መንግሥት ከዛው ከዛገው ብርታቸው ውስጥ ነው። እኔ ደግሞ እላለሁ። አይስጉ። ከሽውራር የምንጠብቀው ትፍስህት የለም። ቢሞከርም ይጨነግፋል። ምክንያት ኤክስፓዬርድ ያደረገ ስለሆነ።
ሁለተኛ የሚጭበረበር የለም። ፈፅሞ። እናማ ተፈነቃቅላችሁ ኃይል ነን ብሎ የሚከሰት ማንም ይሁን ማን የሚመጣ አካል ተቀባይነት የለውም። ኢትዮጵያ ሙሉ 60 ዓመት ረግረግ የወደቀችበት የመከራ ሥረ መሠረትን የሚነቅል ሂደት ነው እኔ በግሌ የምሻው። ያ ደግሞ ሥር ነቀል ለውጥ በአዲስ ኃይል እና ተፈጥሯዊነት መንፈስ። ትራፊም፤ ቅርጥምጣሚም አያሰኜንም።
በሌላውም በኩል ህልም ሊኖር ይችላል። ያም አይሆንም። ከግንቦት 7 በላይ ሚሊዮኖችን መንፈስ የተቆጣጠረ አልነበረም። ቻለ? አልቻለም። የህወሃት መሸኜት ለሁሉም ዱብ ዕዳ ነበር። ሥራ ይጠይቃል። ለዚህም ነው ሲግለበለብም፤ ሲፈላም፤ ሲንተከተክም በጥሞና እምታደመው። እንዲያውም ሞቅ ሞቅ ሲል ሥርጉትሻ አትኖርም።
በሌላ በኩል የፌድራሉ እና የህወሃት ጦርነት ተከትሎ ፈቃደ ህወሃት ምርቃት ያገኜ አዲስ አመራርም ተጠብቆ ነበር። ያም #ሬሳ ሆኗል። ስለዚህ በስሜት፤ በምኞት፤ በፍላጎት፤ በድረስ ድረስ፤ በተወሰኑ አካላት ቅርበት እና ርቀት የኢትዮጵያ የመሪነት ዕጣ ፈንታ አይወሰንም። ጥበብን የሚጠይቁ፤ ስክነትን የሚሹ፤ መረጋጋትን የጠጡ ጥረቶች ብቻ ለስኬት ይበቃሉ። መቼ? የት? እንዴት? ይህ የፈቃደ እግዚአብሄር እና ቅባ የተሰጠው አቅም የሚወስነው ይሆናል። የማይታይ ግን ሊሆን የሚችል አመክንዮ በጊዜው ለጊዜው መጥኖ ብቅ ይላል። ማን ህወሃት ከንጉሦች ንጉሥ አጤ ሚኒልክ ቤተ መንግሥት ይለቃል ብሎ አስቦ ነበር???? ተስፋችን አምላካችን።
ክብረትቼ ደህና እደሩልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
30/10/2023
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ