ግሥ የሌለው መሪነት አልቦሽነት።

ግሥ የሌለው መሪነት አልቦሽነት።
"ከንቱ የከንቱ ከንቱ
ሁሉም ነገር ከንቱ።"
ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ #ማሰሪያ #አንቀጽ የላቸውም። የድርጊቱ መነሻም መዳረሻውም ከኦዲዬንሱ ውጪ ነው። አሁን አሁን ሳስበው መሪነት ጽንሰ ሃሳቡ የገባቸው አይመስለኝም። በሌላ በኩል #የመሪነት #ስሜቱንም የተረዱት አይመስለኝም። በተጨማሪነት የመሪነት #መነሻውን ያወቁትም አይመስለኝይ።
ይህም ብቻ አይደለም #የመሪነት #ቅደም ተከተሉንም የተረዱት አይመስለኝም። እርግጥ እሳቸው ያቀዱትን እዬከወኑ መሆኑን አያለሁኝ። ያ ማለት ግን የአገር መሪነቱን ሚና እዬተወጡ ነው ማለት አይደለም።
መሪነት ለእሳቸው 365 ቀን መናገር፤ ለሳቸው ደስ የሚላቸውን ፕሮጀክት የድሎት አቅዶ መፈፀም፤ አስደሳች እና አዝናኝ የሆኑ ጉዳዮችን ነጥሎ ትኩረት መስጠት መሪነት መስሏቸዋል። በፍፁም የመሪነትን #ስሜቱን አልተረዱትም። በፍፁም። መጓዝ፤ ንግግር ማድረግ፤ ድንገተኛ ክንውኖች ላይ አቅምን ማፍሰስ መሪነት መስሏቸዋል። የሠፈር መሪ አይደሉም። የዓለም የሰላም አባት የሚመራውን አገር ቀጠናውን በሰላም ማስተዳደር የተሳነው፤ እወክለዋለሁ በሚለው ኦሮምያ ክልል እንኳን ከህዝቡ ጋር የተቆራረጠ። ከበሻሻ በስተቀር በዬትኛውም ሁኔታ የወጡበት ማህበረሰብ ውክላዊ ፖለቲካዊ ሂደት አብሰንት የሆኑ።
የሚገርመኝ እሳቸው ከተደሰቱ፤ እሳቸው ከደለቁ ከ110 ሚሊዮን ህዝብ በላይ የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ስሜቱ ምን ይሁን ምን ጉዳያቸው አይደለም። እረፍት አልባ የሚታትሩት ለራሳቸው ፍስኃ ስለመሆኑ ነው እኔ እማስተውለው። ህዝቡ ሲከፋው አይከፋም። ሲያዝን አያዝኑም። ሲራብ አይራቡም። ሲያለቅስ አያለቅሱም። ለእኔ የቤተ መንግሥቱ #ሃውልት ወይንም ማስዋቢያ ዲኮሬሽን ሆነው ነው የሚታዩኝ። ኦሮሞ ጠቅላይ ሚር ሆነ። በቃ።
አንድ ምሳሌ ላንሳ ………
ይህ አረፍተ ነገር ስሜት ይሰጣልን? አክሽኑ ምንድን ነው። ቤቱ ፈረሰ? ቤቱ ቀለም ተቀባ? ቤቱ ተቀዬረ? ቤቱ ተሰራ? ቤቱ ፈረሰ? ቤቱ ተናደ? ቤቱ ፀዳ? ቤቱ ተጀምሮ ቀረ? አይታወቅም። የዓለሙ የሰላም አባት ሎሬት ጠሚ አብይ አህመድም የሚመሯት ኢትዮጵያም፤ እሳቸውም እንዲሁ ናቸው። ገና በይሆናል የሚያስቡት የህሊና ፋንታዚ ለእሳቸው ፍንደቃ ለእኛ ደግሞ የዕዳ ካዝና ነው። ዕዳው የጊዜ፤ የታሪክ፤ የትውፊት፤ የትውልድ፤ የመብት እና ግዴታ መለኪያ የለለው። ሙሉ ስድስት ዓመት ባከነ ከምል #አረረ#ተኮማተረ። ተጨማተረ።
አንድ ምሳሌ ሌላ ላንሳ የጎርጎራ ፕሮጀክት። በእኔ ዘመን እዬሄድን እንዝናናበት ነበር። ሠርግ ልደት እዛ ይከወናል። ዛሬ ይቻላል? አይቻልም። ሊቀድም የሚገባው የህዝቡ በሰላም የመኖር ዋስትና፤ በለመደው አኗኗር እንዲኖር ነፃነት ማግኜት ነበር። ውሃ ማግኜቱ ቢቀር?? መማሩ ቢቀር? ይህ ፕሮጀክት ግሎባላይዜሽን ታስቦ ነበር። ለቱሪዝም። አይደለም ለግሎባል አገሬው እዛ ሄዶ የሚዝናና የለም። ስሜቱም ተጎድቷል፤ ሰላሙም ተጎሳቁሏል። ስለዚህ ፋንታዚው እና ሂደቱ ተቋርጧል። ለዚህ ነው ማሰሪያ አንቀጽ የሌለው መሪነት ያልኩት።
በንግግር ጥበብ ሦስት ወሳኝ ጉዳዮች አሉ። ይኽውም
1) ተናጋሪ፤
2) አድማጭ እና
3) ግብረ መልስ። የሦስቱ ውህደት ንግግሩ የተሰናዳበት የግብ መቋጫ ውስጥነት ነው። በመሪነት ውስጥም ይህ ይኖራል። አሁን እኔ እማዬው እሳቸው በባዶ ምድረ በዳ ላይ ካለ ኦዲዬንስ እንደሚጮህ #ናስ ነው። አመራራቸው ለተፈለገው ማህበረሰብ ውስጥነትን አላገኜም። ይህ ደግሞ ወና ሆኖ ነው እማዬው።
እኔ እንደ ሥርጉተ እሳቸው እራሳቸውን የሚዩበት፦ የሚፈትሹበት፤ ጊዜ ሊኖራቸው ይገባል ብዬ አስባለሁኝ። ኢትዮጵያን ለመምራት በሞራል፤ በሥነምግባር፤ በአቅም መጥኛለሁ ወይ ብለው እራሳቸውን መጠዬቅም ያለባቸው ይመስለኛል።
ሙሉ ስድስት ዓመት ቋሚ ሥርአት ተፈጥሮ ተቋማት ተገንብተው ወህ በሚባልበት ጊዜ አዲስ #ሪቮሊሽን የሚናፍቀን መሪው እና ምኞቱ እኛን አድሬስ የማያደርግ በመሆኑ ነው። በድህነት ለመኖር ሰላሙን የተቀማ፤ በድህነት ለመኖር መኖሩን የተቀማ ህዝብ እና መሪነት የማይጠቀጥል ይሆናል። ከሁሉ በላይ አረመኔነት። ዜጋ ተገድሎ መኪና በበላዩ የሚሄድበት በቀል፤ ተገድሎ ለጅብ የሚሰጥበት ግዑዛዊ ሂደት አይቀጥልም። ማህል ላይ ይቦደሳል።
ሌላው በኽረ ጉዳይ ለእንድ መሪ #ከመጠላት በላይ ከባድ የጉዞ ሂደት የለም። ማቅ ለብሰው፤ አመድ ነስንሰው የካዱትን ዕውነት ምህረት የሚጠይቁበት ጊዜ ሊኖራቸው ይገባል። በጣም ብዙ ሰው #ድምፃቸውንም#ምስላቸውንም ማዬት አይሻም። ለፁሁፌ የራሴን ፎቶ መለጠፋ ይቀለኛል። ከሳቸው ፎቶ ይልቅ። ምቾት አይሰጥምና።
ምስላቸውን የሚለጥፋ ወገኖች ታዳሚወቻቸውን ይቅርታ ይጠይቃሉ። ከሄሮ ወደ ዜሮ።
ውዶቼ እንዴት ናችሁ። ምዕራፍ ፲፩ ላይ ነን። በሰከኑ ዕይታወች ጊዜ ይፈተሻል። ሂደት ይበረበራል።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
30/10/2023
መሪነት ዝልቦነት አይደለም!

 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።