ልጥፎች

ከኤፕሪል, 2021 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የጸጋዬ ራዲዮ ሙሉ መሰናዶ የ29.04.2021 በቃ! ማለት በቃ! ነው ግድለኛ የበቃ አብዮት በመላ አማራ ክልል።

ምስል

ኢትዮጵያዊው ዕውቅት የህልውና አደጋ ላይ ነው።

ምስል
    ·        ዕውቀትም ስደት ላይ ነው፤ እዬነደደ። ·          ልሙጧ ኢትዮጵያም ታጭታለች …. ·        ኢትዮጵያዊው ዕውቅት የህልውና አደጋ ላይ ነው። ·        ኢትዮጵያን የበጃት ጥበብ ቃጦሎ ታዞበት እየጋዬ ነው … ዕለተ ማክሰኞ ማዕዶተ ይግቡ በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ።   „ዝም ብዬም የመከራን ቀን እጠብቃለሁ።“ (ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ 3 ቁጥር 17) ·        ኢ ትዮጵያዊው ዕወቀትም፤ ኢትዮጵያዊው ጥበብም ነዲድ ላይ ነው። ·        ኢትዮጵያ በጠላቷ እጅ ወድቃለች እና።     o    ዕ ውቀት የጀንበር ሥራ ነውን?     ዕውቀት ህሊናዊ አቅም ነው በእኔ ዕድምታ። ፍልስፍናም፤ ጥበብም፤ ሳይንስም ነው። ያ ህሊናዊ አቅም በተለያዬ ሁነት ሊገኝ ይችላል። o    ዕውቀት ዘርፈ ብዙም ስጦታ ነው። በአራት ከፍለን ልናዬው እንችላልን።   (1)       በ ትምህርት በሥልጠና የሚገኝ፤ ክህሎት እንደማለት … (2)       በ ልምድ በሥልጠናም ከሥልጠና ውጪም የሚገኝ የተመክሮ ክፍል ነው። (3)       ከፈ ጣሪ የሚገኝ የብልህነት ዘርፍ ነው። (4)       የተለዬ ጸጋ ጥበብ የምንለው ነው፤ ያደላቸው በገኃዱ ዓለም ተምረው ተመረቅው፤ በተማሩበት   የዕውቀት ዘርፍ ዕድል አግኝተው ሲሰሩበት የህልና ንድፉ ከተግባር ጋር ሲዋደድ፤ በተጨማሪም ፈጣሪ አምላክ ሳይማሩ ጥበብ እንደ ተሰጣቸውም በድርብነት ብልህነትም የጥበብ ጸጋው ሲኖራቸው እንኝህ ሙሉዑ የሆነ ሰብዕና ያላቸው ይሆናሉ። የፈጣሪ ስጦታ ምንም የቀለም ትምህርት ሳይገበዩ በተፈጥሯቸው ብልህ፤ አዋቂ ሆነው የሚፈጠሩ አሉ። ኢትዮጵያን ያበጃት

ኢትዮጵያዊ አይዛችሁ! ባለቤት የለውም። ስደት ላይ ነው።

ምስል
  ·        ኢ ትዮጵያዊ አይዛችሁ! ባለቤት የለውም። ስደት ላይ ነው። ዕለተ ማክሰኞ ማዕዶተ ይግቡ በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። „የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፡፡ መጽናናትን ያገኛሉና፡፡ ” (የተራራው ስብከት ማቲወስ ምዕራፍ 5 ቁጥር 4)      ማዕዶተ ይግቡ ባለቤት የሌላቸው ሁለመናወች የሚዳሰስብት።   ·        ኢ ትዮጵያዊ አይዟችሁ በስደት ላይ! ባለቤትም የለውም። ·        ኢ ትዮጵያዊ ማጽናናትም ስደት ላይ ነው! ·        ኢ ትዮጵያ ከፍቷታል እምለውም ለዚህ ነው። እንደዚህ ዘመን አረማሞ የለም። ድሃ የሚጠላ፤ ድሃ የሚጸዬፍ፤ ደሃን ማዬት የማይሻ፤ ገድሎ እንኳን አይዟችሁ! ማለት የሚሳናነው፤ ሰቅሎ አይዟችሁ! የሚል ቃል ለማውጣት ስቅለት የሆነበት፤ በሚሊዮን አፈናቅሎ ውስጡ በሐሴት ዳንኪራ የሚቧርቅ ከእንደዚህ ያለ አረመኔ ጲላጦስ መሪ ኢትዮጵ እጅ መወደቋ ውስጥ አለመሆኑ ይገርመኛል። ዘመኑ ዘመነ ፍዳ መሆኑን የምታዩት ይህንን ጨለማ ሰብዕና አጅበው ምራን፤ ንዳን፤ እንደ ጋሬ ጎትተን የሚሉ ዕብን ሰብዕናዎች ናቸው። በዚህ የፍዳ ዘመን ወደ እንሰሳዊ ሰብዕና የተለወጠው ብዛት ወዘተረፍ ነው። ወደ እንሰሳ ስል ወደ ጫካው ማለቴ ነው እንጂ ውሾች፤ ፈረሶች እንደምን ታማኝ እንደሆኑ ጠፍቶኝ አይደለም። ·        አ ይዞህ! አይዞሽ! አይዟችሁ! 1.      አ ይዞህ! ፆታው ታብዕት ለሆነ ወገን የሚሰጥ የርህርህና ስጦታ ነው። 2.     አ ይዞሽ ፆታዋ አንስት ለሆነች ሴት የሚሰጥ የደግነት ሽልማት ነው። 3.     አ ይዟችሁ! አይዞን! ለሰው ልጅ በሙሉ የሚሰጥ የርህርህና ትህትናዊ ስጦታ ነው። ·        አ

ሬሳ² አብረን እንቅበራቸው።

ምስል
  ·        ሬሳ² አ ብረን እንቅበራቸው።   ዕለተ ሰኞ ማዕዶተ ጠባቂ በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። „ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁኝ።“ (ትምህርተ - ዕንባቆም ምዕራፍ 3 ቁጥር 17) ·        ሬሳ xሬሳ= ሬሳ² ·        የ ሙታን ማህበር። አብረን ብንቀብራቸው ከተቀበረው የ አማራ ቀን ጋር ደስ ይለኛል። ኑረውም አላመረባቸውም ማህበረ የቁም እንቅልፍ። ሎሌነትም አለው አይነት፤ ግርድናም አለው አይነት። ባርነትም አለው አይነት። እንደምን ለድንጋይ ዘመን ጠቀራ እንደዚህ የ እንብርክክ እንደሚሄዱ ይገርመኛል። ለነገሩ ሙጃ ለከብት እንኳን አይውልም እንኳንስ ለሰው ልጅ። እኔ እሬሳ ቁሙ የሚሄድ ነው የሚሰለኝ። አብረን ተረዳድተን   እንጦርጦስ ብንልካቸው ምርጫዬ ነው። ሁሉ ነገር ኦነጋዊው ኦህዴድ ከ እናኝህ ሙታን ጋር ተመካክሮ፤ መስጥሮ ኢሁንታ ተሰጥቶበት ነው የሚከወነው። እሰቡት ሬሳ ለድርድር፤ ሬሳ ለውል፤ ሬሳ ለክርክር ሲበቃ። ሬሳ +ሬሳ= ሬሳ! ማህበረ ሬሳ ሬሳነታቸውን የተሸከመው የሬሳ ሳጥን ህሊናቸው ገበርዲን እና ከረባት ሲሰቀለብት ግርም ይለኛል። እነኝህ ማሽንኮች የ ኢትዮጵያ፤ የስሜን ፖለቲካም ነቀርሳወች ናቸው። ኢትዮጵያን ከ አቶ ሌንጮ ለታ፤ ከዶር ዲማ ነግዖ ጋር ሆነው ቀበሯት። ለዚህ ነው አብረን እንቅበራቸው እምለው። ማህበረ ከንቱ ልጅም ቤተሰብም ሊኖራቸው ይችል ይሆናል። አገር ውስጥም ውጭም። ግን የታሪክ አተላ ነው ልጆቻቸው ተሸክመው ይኖሩ ዘንድ የፈረዱባቸው። አወን አተለ። አንቡላም። የአንቡላ ማንቆርቆሪያዎች የሞት ደመመን ተጭኗቸው በዕብነንነት እዬአረገዱ ይገኛሉ። ያልታደለ ከረባት እና ገበርዲንም ከ እነሱ ተጠግ

አብረን እንፍራ! ፍርኃት ሊገድለኝ ነው።

ምስል
  ·        አብረን እንፍራ! ፍርኃት ሊገድለኝ ነው። ዕለተ ሰኞ ጠባቂ በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ።   „ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁኝ።“ (ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ 3 ቁጥር 17)   ·        ቆ ራጣ ትህትናዊ ማሳሰቢያ።   ወዶቼ ዛሬ ማዕዶተ ጠበቂ ነው። የቀናው አጀንዳ ሁሉ አሰሳም፤ ዳሰሳም የሚካሄድበት። ቅን እና ቀና ቀን ነው። ድካም እስከ ገደበኝ ድረስ እሰራለሁኝ ዕናባዬን ዋጥ አድርጌ። ዕንቅልፍም ቢያንገላጅጀኝም። ስለሆነም አብራችሁኝ ሁኑ ስል በትሁት መንፈስ እጠይቃለሁኝ።   ስዘገይ ፖስት ሳደርግ፤ ፎቶ ስጨምር ስቀንስም ግር እንዳይላችሁ። ኮንፒተሬም ስልኬም ጤናቸው እንደ እኛው ከታመመ ወር ሊሆናቸው ነው። ስለዚህ ቅልጥፍናዬ እንደ ወትሮው ላይሆን ይችላል። እግዚአብሔር ይስጥልኝ።     ·        ፍርኃቱ ሊገድለኝ ነው።   አዲስ አበባ ላሉ የ አማራ ሊቃናት፤ የተዋህዶ ልጆች ስጋት አለብኝ። ይህ ስጋቴ አጣኜ፤ ካራቆሬ ከነደዱ በኋላ ነው የተከሰተብኝ። እስር ቤት ያሉ የቲም እስክንድር አባላት የቤተ መንግሥቱ ጫካ ከወለጋው ጫካ ጋር ተባብሮ እስር ቤቱ ተሰብሮ ተወሰዱ እንዳይባል በስጋት ነው የሰነበትኩት። ፈርቻለሁኝ። በተጨማሪ ለአቶ ልደቱ አያሌው፤ ለኢንጂነር ይልቃል ጌትነት፤ ለዶር ደሳለኝ ጫኔ፤   አቶ ክርስትያን ታደለም ወዘተ እንዲሁ ፈርቻለሁኝ። ሽፍታው ተስማምቶ እንዳያሳግዳቸው። ተሰወሩብኝ እንዳይል። ይህ የቤተ -መንግሥት ወዘተረ አራዊት መንፈስ ብዙ ነገር ነው ያደራጀው፤ ፎሌ፤ ቄሮ፤ አባቶርቤ፤ የጫካ ወታደራዊ ክንፍ፤ ስውር የከተማ ሽምቅ ተዋጊ ኃይል ሥሙ የማይታወቅ፤ በኢት

ውጽፍተ ወርቅ ሆይ እባክሽን ተለመኝን?

ምስል
  ·        ው ጽፍተ ወርቅ ሆይ እባክሽን ተለመኝን?   ዕለተ ሰኞ ማዕዶተ ጠባቂ በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። „የሰው ልጅ መንገድን ያዘጋጃል እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።“ (ምሳሌ 16 ቁጥር 9)   በሰመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አህዱ አምለክ አሜን።   አንቺ የሰማይ እና የምድር ንግሥት ሆይ! አንቺ የሰማይ እና የምድር እመቤት ሆይ! አንቺ የሰማይ እና የምድር ልዕልት ሆይ! እባክሽን ድረሽላት ለ ኢትዮጵያ! እባክሽን ጠባቂ እረኛ ለሌላቸው ልጆሽ ድረሽላቸው?   አብክሽን እንባችን እሚያብስ ሙሴ ስጭን? እባክሽን አይዟችሁ የሚል የአሮን በትር ስጪን? እባክሽ የመፍትሄውን ጎዳና ቀይሽልን? እባክሽን ከ ዕንባችን ጎን ቁሚልን? እባክሽን አንቺ የንጽህና፤ የድንግልና፤ የቅድስና ብጽዕት እናታችን ሆይ ድረሽልን? መጽናናቱን፤ መረጋጋቱን አስልኪልን። ከልጅሽ ከወዳጅሽ አንድዬን ተማጸኝልን።   ·        ቅ ድስቴ ሆይ! ዕውነቱን ብነግርሽ ውስጤ አለቀ፤ ውስጤ ተጎዳ፤ አቅመ ቢስነት ይሰማኛል። ለሁላችንም አጽናኝ አረጋጊ መንፈስ ይልክልን ዘንድ ከአማኑኤል አማልጅን። አስከፍተነዋል። ደስታችን ልክ አልነበረውም። ደስታችን በቅጡ አላስተዳደርነውም። የተሰጠን ማስተዋል በውል አልተጠቀምንበትም እና ምርቃታችን ተነሳ። አብረንም ወደቀን። ኢትዮጵያ በማህበረ ዲያቢሎስ እጅ ወድቃለች። በባዕድ መንፈስ እዬነደደች ነው። እሙ እናት ዓለም፤ እናት ዓለም ሆዴ ድረሽላት። መልስሽን እጠብቃለሁኝ። ጨንቆኛል እናት ዓለም። አይዟችሁ ባይ መንፈስ ቅዱስ ይላክልን ዘንድ ለኤልሻዳይ አምላክ አሳስቢልን። ድ

በአለሁ የለሁም ሲነግሥ ተፈቅዶለት።

    ·          በ አለሁ የለሁም ሲነግሥ ተፈቅዶለት። „ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁ“ (ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ 3 ቁጥር 17) ውዶቼ እንዴት አደራችሁ ልላችሁ አልችልም። እኔ እንደምን እንዳደርኩ ስለማውቀው። እንዴት ትውሉ ይሆን ልልም አልችልም። እኔ እንደምን ልውል እንደምችል ስሰላማላውቀው። አለማወቄን ስጠይቀው አለማወቁን ገልጾልኛል። እንለመደብኝ ተስፋን እጠብቃለሁኝ። ·          ጥቂት ነገር ግን ልበል። (1)     „ተረኝነት“ በሚል ግርዶሽ ፋሺዝምን ስታሽሞነሙኑ የቆያችሁ የፖለቲካ ተንታኞች፤ ጸሐፍት እና ጋዜጠኞች ይህን ምን ልትሉት እንደምትችሉ እስኪ ንገሩኝ። አንድ ነፍስ ብቻ ጥቅምት ላይ የኔታ ጎዳና ያቆብ „የማዬው ከተርኝት በላይ ነው“ ሲሉ አድምጫለሁኝ። እኔ የገዳ ወረራ፤ የገዳ መስፋፋት፤ የገዳ አስምሌሽን፤ የገዳ ዲስክርምኔሽን ብላችሁ ድፈሩት ስል ነበር የባጀሁት። የፖለቲካ ውይይቱ እጭ ላይ ነው። መፍትሄውም ተስፋውም ሩቅ ነው ብዬም ሞግቻለሁኝ። (2)    የኦህዴድ የማስገበር ጦርነት በትግራይ፤ የትግራይም ኢትዮጵያን የማስገበር ጦርነት ሲመጣ ደግሞ „ህወሃት ይወገድ እንጂ ሌላው ገብስ ነው“ በማለት ተከታዮቻችሁን ስትመሩ የቆያችሁ አክቲቢስቶች ውጡ እና ንገሩን፤ አሳምኑን። አስረዱን። ይህን በዬትኛው የፖለቲካ አምክንዮ ሊታቀፍ እንደሚችል። የፖለቲካ ብቃታችሁን አሳዩን። ይህን ጭብጥ በሚመለከት ግልብ ዕይታ ስለነበር ሁለት ጹሑፍ ጽፌበት ነበር። ነፍስ እዬረገፈ ያለው አቅም የለው መካች የፖለቲካ ሙግትም ስላልተካሄደም ነው። ከችግሩ አስኳል መነሳት አልተቻለም። (3)    በጦርነቱ „ድል“ ብላችሁ የተደሰታችሁትንም፤ ደስታችሁን በልክ ያዙት አንደኛው ተጨማሪ ደስታ ስታገኙ መደርደሪያ እንዳታጡ፤ መደርደሪያችሁ