በአለሁ የለሁም ሲነግሥ ተፈቅዶለት።
·
በአለሁ የለሁም ሲነግሥ ተፈቅዶለት።
„ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁ“
(ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ 3 ቁጥር 17)
ውዶቼ እንዴት አደራችሁ ልላችሁ አልችልም። እኔ
እንደምን እንዳደርኩ ስለማውቀው።
እንዴት ትውሉ ይሆን ልልም አልችልም። እኔ እንደምን
ልውል እንደምችል ስሰላማላውቀው።
አለማወቄን ስጠይቀው አለማወቁን ገልጾልኛል። እንለመደብኝ
ተስፋን እጠብቃለሁኝ።
·
ጥቂት ነገር ግን ልበል።
(1)
„ተረኝነት“ በሚል ግርዶሽ
ፋሺዝምን ስታሽሞነሙኑ የቆያችሁ የፖለቲካ ተንታኞች፤ ጸሐፍት እና ጋዜጠኞች ይህን ምን ልትሉት እንደምትችሉ እስኪ ንገሩኝ። አንድ
ነፍስ ብቻ ጥቅምት ላይ የኔታ ጎዳና ያቆብ „የማዬው ከተርኝት በላይ ነው“ ሲሉ አድምጫለሁኝ። እኔ የገዳ ወረራ፤ የገዳ መስፋፋት፤
የገዳ አስምሌሽን፤ የገዳ ዲስክርምኔሽን ብላችሁ ድፈሩት ስል ነበር የባጀሁት። የፖለቲካ ውይይቱ እጭ ላይ ነው። መፍትሄውም ተስፋውም
ሩቅ ነው ብዬም ሞግቻለሁኝ።
(2)
የኦህዴድ የማስገበር ጦርነት
በትግራይ፤ የትግራይም ኢትዮጵያን የማስገበር ጦርነት ሲመጣ ደግሞ „ህወሃት ይወገድ እንጂ ሌላው ገብስ ነው“ በማለት ተከታዮቻችሁን
ስትመሩ የቆያችሁ አክቲቢስቶች ውጡ እና ንገሩን፤ አሳምኑን። አስረዱን። ይህን በዬትኛው የፖለቲካ አምክንዮ ሊታቀፍ እንደሚችል።
የፖለቲካ ብቃታችሁን አሳዩን። ይህን ጭብጥ በሚመለከት ግልብ ዕይታ ስለነበር ሁለት ጹሑፍ ጽፌበት ነበር። ነፍስ እዬረገፈ ያለው
አቅም የለው መካች የፖለቲካ ሙግትም ስላልተካሄደም ነው። ከችግሩ አስኳል መነሳት አልተቻለም።
(3)
በጦርነቱ „ድል“ ብላችሁ የተደሰታችሁትንም፤
ደስታችሁን በልክ ያዙት አንደኛው ተጨማሪ ደስታ ስታገኙ መደርደሪያ እንዳታጡ፤ መደርደሪያችሁ እንዳይሞላ፤ ሁለተኛው ደስታችሁን ካጣችሁት
ተስፋ ቆራጭ ሆናችሁ ውስጣችሁ እንዳይጎዳ ብዬም ነበር። የጄኒራል ብርኃኑ ጁላን „ሠራዊቴ“ በማለት በፋቲክ እጅ በደረት አደርጋችሁ
ስትወጡ ከፊል ጎጃም፤ ሙሉ ወሎ፤ ሙሉ ሽዋ፤ አዲስ አበባ በኦነግ ይዋጣል ብዬም ሞግቼ ነበር። ቤተ - መንግሥቱ እራሱ አዙሮ ይወጋችኋል
ብዬ ሁሉ አጽህኖታዊ ጹሑፍ በተከታታይ ጽፌ ነበር። ለዚህም ነው አቅም ተቆጥቦ ይተዳደር የምለው። ዘመኑ እንዲህ አናባቢ ሲያጣ ያሳዝናል።
(4)
አዲስ አበበ፤ አማራ፤ ቅድስት
ኦርቶዶክስ፤ አማርኛ ቋንቋ፤ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ፤ የአማራ ወዳጆች፤ ኢትዮጵያ እራሷ የህልውና ታገድሎ ነው ማድረግ የሚገባቸው።
የህልውና ተጋድሎ የጫጉላ ሽርሽር አይደለም። ተጋድሎውን ዲስፕሊን
ለመሸከም ከዓላማው ከፍላጎቱ፤ ከግቡ ተነሱ ዴሞክራሲ የቅንጦት ነው ብዬም ሞግቻለሁኝ። ቀናቸው ላልተጸነሰ የተጋድሎ ማንነቶች ኬክ
ቆረሳ፤ የከረባት እና የገበርዲን ሸው ይህን መራር የህልውና ተጋድሎ መመከት እንዴት ይቻላል? በዛሬ ውስጥ ያለው ዛሬ ከስሏል።
እንኳንስ በዛሬ ውስጥ ያለ ነገን ማሰብ ሊችል።
የመታገያ የተደራጀ ሐሳብ እንኳን ለማፍለቅ አቅሙ
አልነበረም። አቅሙ መኖር ያልቻለው ከአሉታዊ ዴሞግራፊ ጽንሰት፤ ዓላማ እና ግብ ጋር ለመዋህድ፤ ለመቁረጥ፤ ለመወሰን አልተደፈረም።
አሁን እቅቅፎሹ ሙት መሬት ላይ ሆኖ ዕንባ።
·
ለምን አሁን ሁለገብ ወረራ። የትናንቱን ዕድምታዬን ልደገመው።
(1)
ጦርነቱን ሠሩት። በሞገድ ተውኔት።
ሽብር ያበጃሉ። ሽብር ያቀናሉ። በሽብር ያተርፋሉ። ስለምን „ተዋግተን የአገሪቱን ዋና ከተማ እና አገሪቱን ተቆጣጠርን“ የሚል ክንፍ
አደራጅተዋልና። ፎሌለ አባቶርቤ፤ ቄሮ፤ የኦነግ ወታደራዊ ክንፍ፤
(2)
ህወሃት ለድርድር ቢቀርብ ኦነግም
ለድርድር ይቀርባል። የሚደራደረው እሱበእሱ ነው ሽፍታ እና ሽፍታ።
(3)
ዶላር የሚያዝነቡ የዲታ አገሮችን
ቀልብ ለመሳብ አዲስ አበባ ዙሪያ ይህን ሽብር አደራጅቶ መፈጸም ጠቃሚ ነው። የምርጫ ሁኔታ አልቻልነም ጦርነት ላይ ነን፤ ተጨማሪ
ጊዜ ሙሉ ኢትዮጵያን ለኦነግ ለማስረከብ መስፋፋቱን በተሟላ አደረጃጀት እስከና ጠናቀቅ ጊዜ ይሰጠን ነው። በግርዶሽ የሚያረግደውም፤
በግልጽ የሚያነጥፈውም የወል ፍላጎት ኢትዮጵያን ኦሮማይዝድ ማድረግ ነው። ኢትዮጵያ ብቻ አይደለም አፍሪካም አይቀርላትም።
„አንድ እንጨት አይነድም፤ አንድ ሰው አይፈርድም“
ሆኖ ብዙ ተደከመ ግን አቅጣጫ ለማስያዝ ሲሞከረ „ተረኝነት“ በሚል ሽፋን ሁሉም በረድ ይከመርበታል። ስለ አማራ የተጉት ይጠለፋሉ።
ትራጀዲው ብዙ በጣም ብዙ ነው። ለማንኛውም ይህ ቃለ ምልልስ ይደመጥ። የአማራ ሊቃናት መጨፍጨፍ ሚስጢሩ ዘመን እዬገለጠው ነው።
የጦር ኮሚስራም ግድያ እንዲሁ።
ሽዋ ሮቢትም ምጥ ላይ ነው። አሁን ስጋቴ እስር
ቤት ያሉትንም ሽፋን ሰጥተው እንዳያሳግቱ ነው። „ምርጫ ኮንሲኮንስ አለው“ ይፈጸም ዘንድ…. በተተኛው ልክ ጥቃትን ማፈስ ነው።
·
ምርኩዝ። በጥሞና ቢደመጥ።
https://www.youtube.com/watch?v=7bDKaJ_YQhQ
ስለ አጣዬ | ከቀድሞ የአካባቢው አመራር የተገኘ ጥብቅ መረጃ | "ጦርነቱ ታላቋን የሰሜን ኦሮሚያ እንመሰርታለን የሚሉት ፕሮጀክት ነው።" |
Ethio 251
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
18.04.2021
ሰውኛ ሙሴ ፈጣሪ ይስጠን። አሜን።
በዛሬ ውስጥ ያለው ዛሬ ከስሏል። እንኳንስ በዛሬ
ውስጥ ያለ ነገን ማሰብ ሊችል።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ