ልጥፎች

ከፌብሩወሪ 24, 2019 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ይባረኩ! ጸሐፊ አቶ ግርማ ካሳ።

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  ይባረኩ  ጸሐፊ አቶ ግርማ ካሳ። „በጎ ነገር ማድረግ ሲቻልህ፤ በወዳጆችህ ላይ ክፉ አትስራ።“ መጽሐፈ ምሳሌ ፫ ቁጥር ፳፰ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 24.02.2019 ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ። ·          መነሻ። https://www.satenaw.com/amharic/archives/64150 የአቶ ንጉሱ የተለሳለሰ አስተያየት ግፈኞችና ዘረኞችን የሚያበረታታ ነው ( ግርማ ካሳ )   February 24, 2019 የኔዎቹ እንዴት ናችሁ? ዘለግ ላለ ጊዜ በአቶ ንጉሡ ጥላሁን ላይ ሰፊ ማብራሪያ ስጽፍ ቆይቻለሁኝ። መጀመሪያ ጠ/ሚር አብይ አህመድ  ወደ ስልጣን እንደመጡ የልብ ስለሆኑ ለኦህዴድ ቃለ ምልልስ OBN አድርገው ነበር። አንዲትም ቦታ „ኢትዮጵያ“ ሲሉ አላዳምጥኳቸው። „በአገሪቱ ተጀምሮ በአገሪቱ ተጠናቀቀ“ እራሱ ቃለ ምልልሱ ደመመን የተጫነው ነበር። አንዳች ምናምን በተጫነው መንፈስ ውስጥ በጭንቅ የሚወጣ ቃል ነበር ያዳመጥኩት። ከዚህ ጊዜ በሆዋላ እሳቸውን መከታተል ጀመርኩኝ።  በጠ/ሚሩ በመጀመሪያ ጉብኝትም ወደ አማራ ክልል ባደረጉበት ጊዜ የታዘብኩትን ታዘብኩኝ። ለውጡን በመቀበል አይደለም ችግራቸው እኔ እንደማስበው። ዶር ለማ መገርሳ ጠ/ሚር ቢሆኑ እንዲህ ፈተና አይሆኑም ነበር። ውስጣቸው ቁርሾ አለበት። እኔስ እንዴት አንሳለሁ የማለት።  በለውጡ ውስጥ ገነው የወጡ ሥሞች ረብሸዋቸዋል ብዬ አስባለሁኝ። ከሁሉም የከፋው ግን በሚሊዬነም አዳራሽ ለአባገዳ ጃዋር መሃመድ ያደረጉት ቅጥ ያልተሠራለት የፈጠጠ ገመና ነበር። ያ በውነቱ ክብደታቸውን በ እጅጉ ቀንሶታል። ከኢትዮጵያዊነት በላይ ክብር የለም። ኢትዮጵያ

የብላቴ ሎሬት ጸጋዬ የታቦትነት ንግሥና እጬጌው ዘመን ዘውድ ደፋለት! ተመስገን!

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  መሬት እራሱ ዘመንን ዳኘች፤  ለቅኔው ልዑል ዘውድ ደፋች። ተመስገን! „ ምንም እንኳን በለስም ባታፈራ፣ በወይን ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፣   የወይራ ሥራ ቢጓል እርሾችም መብልን ባይሰጡ በጎችም ከበረት ቢጠፉ ላሞችም በጋጥ ውስጥ ባይገኙ   እኔ ግን በ እግዚአብሄር ደስ ይለኛል፤ በመዳህኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ። “ ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯ ቁጥር ፲፰ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ።                                                     ታቦቴ!                                        „የማይድን በሽታ ሳክም                                         የማያድግ ችግኝ ሳርም                                         የሰው ህይወት ስከረክም                                         እኔ ለኔ ኖሬ አላውቅም።“ ዛሬን ዋዜማውን ሳስብ በውስጡ አንድ ትልቅ ቁመነገር ይዟል። ያ ቁምነገር የአንድ ንጹህ ፍጥረት መንፈስ ወደ ቅኖች መንፈስ ይጠጋል በዘወትርኛ። አሁን ሻማ አብርቻለሁኝ። ሌላም አቅም የለኝም እንጂ ባደረግለት በወደድኩኝ። የአቅሜን ለማድረግ ደግሞ በፍርደ ገምድሎች ህሊናዬ ታስሮ እንዲቀመጥ በግፍ የተፈረደብኝ ዜጋ ነኝ። ጭምቷ ሲዊዘርላንድ ባንድም በሌላም ለቅኔው ልዑል ለብላቴ ጸጋዬ ሥም አዲስ አይደለችም። በዛ ጥንካሬ እና ብርታት ቀጥሎ ቢሆን ጸጋዬ ራዲዮ እና ጸጋዬ ድህረ ገጽ ሲዊዝም የጸጋዬ ሚዲያም እኩል ተፎካካሪ ሆኖ መውጣ ሙሉ አቅም ነበረ