የብላቴ ሎሬት ጸጋዬ የታቦትነት ንግሥና እጬጌው ዘመን ዘውድ ደፋለት! ተመስገን!

እንኳን ደህና መጡልኝ።

መሬት እራሱ ዘመንን ዳኘች፤
 ለቅኔው ልዑል ዘውድ ደፋች።
ተመስገን!

ምንም እንኳን በለስም ባታፈራ፣ በወይን ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፣
 የወይራ ሥራ ቢጓል እርሾችም መብልን ባይሰጡ
በጎችም ከበረት ቢጠፉ ላሞችም በጋጥ ውስጥ ባይገኙ
 እኔ ግን እግዚአብሄር ደስ ይለኛል፤
በመዳህኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ።
ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯ ቁጥር ፲፰

ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ።


                                                   ታቦቴ!
                                       „የማይድን በሽታ ሳክም
                                        የማያድግ ችግኝ ሳርም
                                        የሰው ህይወት ስከረክም
                                        እኔ ለኔ ኖሬ አላውቅም።“

ዛሬን ዋዜማውን ሳስብ በውስጡ አንድ ትልቅ ቁመነገር ይዟል። ያ ቁምነገር የአንድ ንጹህ ፍጥረት መንፈስ ወደ ቅኖች መንፈስ ይጠጋል በዘወትርኛ። አሁን ሻማ አብርቻለሁኝ። ሌላም አቅም የለኝም እንጂ ባደረግለት በወደድኩኝ። የአቅሜን ለማድረግ ደግሞ በፍርደ ገምድሎች ህሊናዬ ታስሮ እንዲቀመጥ በግፍ የተፈረደብኝ ዜጋ ነኝ።

ጭምቷ ሲዊዘርላንድ ባንድም በሌላም ለቅኔው ልዑል ለብላቴ ጸጋዬ ሥም አዲስ አይደለችም። በዛ ጥንካሬ እና ብርታት ቀጥሎ ቢሆን ጸጋዬ ራዲዮ እና ጸጋዬ ድህረ ገጽ ሲዊዝም የጸጋዬ ሚዲያም እኩል ተፎካካሪ ሆኖ መውጣ ሙሉ አቅም ነበረው። አቅምን በሚመለከት ተደፍሮ ነው የሚነገራቸው ለእኩዮች ሩኮሞች።

ሁሉ ያላቸው፤ አቅም ያላቸው ወገኖች ሲዊዝ ይኖራሉ። ብድርም የሚያስኬድ ምንም ነገር አልነበረም። ግን የሴራ ፖለቲካ በዜት አራምዶ። ሰውና ሰው እንዳይገናኝ በሩ ተከርችሞ አፍ ባለው መቃብር ጥበብ ተከዘነች።

የሚገርመው ግን የዛሬ የኢትዮጵያንዚም የሙጥኝ ባዮች ተስፋውን ሁሉ ነበር ያከሰሉት። ያደረቁት ከው አድርገው። የጸጋዬን መድህናዊ ተስፋውን በደባ እና በሸር ፖለቲካ ድቅቅ አድርገው ባድማውን አጠፉት እንጂ ሲዊዘርላንድ ሁሉንም ማድረግ የሚያስችል ክህሎቱ ነበር። ባከነ ጊዜው … አቅምም ተመሶ ተቀበረ።

እውነት ለመናገር ብላቴው ከሞት ተነስቶ የእነሱን ሥልጣን የሚጋፋ ሆኖ አልነበረም ያን ያህል በሽታ ሽቶሽ የታገሉት። የእነሱን ተቀባይነት የሚቀማ ሆኖ አልነበረም ያን ያህል በኔት መረብ የተዋጉት። ያ ቅዱስ መንፈስ የእነሱን አቅም የሚፈታትን አልነበረም። ከመቃብር በታች ላለ ነፍስ ያን ያህል ጦር የሚያማዝዝ መሆን አልነበረበትም። 

የጸጋዬ ድህረ ገጽ ሆነ የጸጋዬ ራዲዮ ገንዘብ ማንም ተጠይቆ አያውቅም። እርዱኝ፤ እገዙኝ አልተባሉም። መድረክ ፍቀዱልኝ አልተባሉም። በራስ ጊዜ እና አቅም ለተደራጀ የትውፊት እንብርት ሳንጃ መዘዙ። ያ የጸጋዬ ራዲዮ እና የጸጋየ ድህረ ገጽ መንፈሱ እግዚአብሄር ይስጥልን ለራስህ ኑረህ ለማታውቅው ፓን አፍሪካኒስት ለማለት ቅንነት ሰንቆ ነበር የተዳረጀው።ነፃ አግልግሎት።

                                           የዘመን  ቅኔ!
በዛ ውስጥ የሎሬት ተስፋ የሆኑ ልጆችን በአገራቸው ፍቅር ኮትኩቶ ለማብቀል ነበር ትትርናው። በትዳር መታወክ የትም ስለሚበቱን ልጆች እና አገራዊ ሃላፊነት እንዴት ማዋደድ እንደሚቻል የሚቻለውን ለማድረግ ነበር። 

መክሊት ያላቸውን ልጆች ወላጆች እንዴት በጥዋቱ በመለዬት ኮትኩቶ መክሊታቸውም ማሳደግ እንደሚቻል አቅም የፈቀደውን ለማድረግ ነበር በመረዳዳት፤ በመተጋጋዝ የህሊና አቅም በማዋጣት። ግን አልተቻለም ዘንዶው አሳገደው … ባህር አቋርጦ ወንዝ ተሻግሮ አቅሙን አጠለሸው በሽታሽቶ።

በሌላ በኩል ነፃነት የትግል ውጤት እንጂ የመና ስላልሆነ አገር ማለት በነፃነት የሚገኝ ከሃሳብ በላይ ከመኖር በላይ የሆነ ቁምነገር ስለመሆን በአምክንዮ ለማጨግዬት ነበር ልፋቱ እና ድካሙ የጸጋዬ ራዲዮ ሆነ የጸጋዬ ድህረ ገጽ ቁልጭ ያለው ዓላማው የነበረው። ሊነገድበት፤ ሊሸቀጥበት፤ እንሱ እነደሚሟሟቱለት ሽልንግ እና ዝና ለማጠራቀም  አልነበረም።

ነገር ግን አቅመ ቢሶች ዘመቱበት፤ መነጠሩት፤ አከሰሉት፤ አፈለሱት። ይህ በግልጽ ቋንቋ ኢትዮጵያዊነት አፍሪካዊነት ከመወጋት ፈጽሞ የተለዬ አይደለም። አልነበረም። ቢቻል ቢቻል ማገዝ፤ ማበረታት ባይቻል ደግሞ የቻለ ለሚያደርገው በተደራጀ እና መዋቅራዊ በሆነ ሁኔታ ማክሰም የተገባ አይደለም።

በሚከሰመው መልካም ተቋም ውስጥ ራስም መከስም አለና። ዜግነቱ አብሮ መኖሩ የተዘለለ ነው። ምን ነበር ሲዊዝ ላይ የቅኔው ልዑል የብላቴ ሎሬት ጸጋዬ ሥም ገኖ በልጽጎ ጎልቶ ቢወጣ?! ክፉዎች ግን አገዱት። ጋሼ ጸጋዬ እኮ አድዋ ማለት ነው። ነፃነት ማለት ነው። ተስፋ ማለት ነው። አሁን እሱ ምን ይጠላል?

የጸጋዬ ድህረ ገጽ እና የጸጋዬ ራዲዮ የሚከፈልበት እንጂ ትርፍ የሚገኝበት አልነበረም። የግልን ኑሮ አጎሳቁሎ፤ እንቅልፍ አጥቶ፤ ሌትና ቀን ባትሎ በነፃ ህዝብን ለማገልገል የታሰበ ፕሮጀክት ነበር።

ለዛውም እኔ ያን ጊዜ ካንፕ ውስጥ ነበር እምኖረው። ኮንፒተር አልነበረኝም ድህረ ገጹንም ሆነ ራዲዮ ፕሮግራሙንም ስጀመረው። ባይቀጥሉበትም ቅኖች እናግዝሻለን በሚል በበጎ ሁኔታ የተጀመረ አገር በቀል አትራፊ ያልሆነ ንጹህ ፕሮጀክት ነበር። ነገር ግን አቅም የሌለው አቅም ማፍለስ የተፈጠረበት ነውና በፈልጉት መልክ ከሰመላቸው። እኔም ታግዬ ታግዬ ብቻዬን ሆንኩኝ እና ተውኩላቸው።

የጸጋዬ ድህረ ገጽ እና ራዲዮ በአክራሪ የኦሮሞ ድርጅት እና በአክራሪ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት የተከሰሰው በጥዋቱ ነበር። የጸጋዬ ራዲዮን ለማዘጋት ብዙ ተሞክሯል። ይህ የሚሆነው ደግሞ ለነፃነት እንታገላለን በሚሉት እኩዮች ነው። የቅናታቸው፤ የምቀኝነታቸው፤ የሴራቸው፤ የደባቸው ልክ እና ዳር ድንበር ማውጣት አይቻልም። ጊዜ ደጉ ዛሬ ሁሉም እኩል ሆነ። ሁሉም ከዜሮ ጀማሪ ሆነ። ተመስገን!

ዛሬ ተመስገን ነው። ባለፈው ዓመት OBN የብላቴውን ህልፈት ቀን አስመልከቶ ልዩ ዝግጅት ነበረው። ምስሉ ጎላ ብሎ ወጥቶ አይቻለሁኝ በመንግሥት ሚዲያ። ዘንድሮ ይድነቃችሁ ብሎ በአንቦ ዩንበርስቲ አንድ የጥናት እና የምርምር ማዕከል በሥሙ እንደሚጀመር ከጥሞና ጊዜ ስመለስ አዲስ ዜና ሰማሁ ገልጉል እንደዘገበው።

የሎሬት ፀጋዬ ማዕከል ሊቋቋም ነው

                                                                     ተመስገን!
ትናንት ሳተናው ላይ ስገባ ደግሞ አንቦን ለማበልጸግ በሚለው ፕሮጀክት ውስጥ የቅኔውን ልዑል ሞገስ እና ግርማ ከፍ የሚያደርግ መልከማ ዜና ሰማሁኝ። ጠ/ሚር አብይ አህመድ የጃቸውን ሰዓት ሰጥተው ወደ 5 ሚሊዮን ብር በጨርታ እንደተሸጠ ሰማሁኝ።

የጠቅላይ ሚንስትሩ የእጅ ሰዓት 5 ሚልዮን ብር ተሸጠ አምቦ የኦሮሞ ነፃነት ሀውልት ናት
ዶክተር አብይ አህመድ February 23, 2019

ዛሬ ላይ ጠ/ሚር አብይ አህመድ በዚህ ስልጣን ላይ ስላሉ እንደተለመደው ቀልብ ለመሳብ ብለው ሊላቸው ይችላል። በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ቢሮውን ሲያደራጁ በጥበብ እጬጌዎች እንደሆነ እቦታ ሄዶ ማዬት መልካም ነው። እሳቸው በቅኔው ልዑል ብላቴ ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን ድንቅነት በውስጣች የእኔ ያሉ ብቸኛው የፖለቲካ ሊቀ- ሊቃውንት ባለቅኔም ናቸው። ስለሆነም የጠ/ሚር ቦታው የተገባ ነው።  

·       በቀደመው ጊዜ እንዲህ ብለው ነበር የዛሬው ጠ/ሚር አብይ አህመድ …

ከዚህ ውጪ ደራስያን ብዙ ጊዜያቸው የመከበር፤ የመደመጥ ዕድላቸው በጣም አናሳነው፤ በቅርቡየአሜሪካው ፕሬዚዳንት መጥተው በነበረ ጊዜ ንግግር ሲያደርጉ በአፍሪካ ማዲባ ብለው ማንዴላን ያነሱ ነበር፤ ሲያነሱ ስለ ትግላቸው፤ ስለፖለቲካ አመራራቸው አላነሱም፤ ማዲባ እንደዚህ ብሏል ነው ያሉት።“ „ጹሑፋቸውን ነው ሜንሽን ያደረጉት፤ ኦባማ ጥቁር ከለርም ስለላቸው ብዙም አልገረመኝ ነበር፤ በቅርቡ የኮሪያ ፕሬዚዳንት ፓርክ ሲመጡ ባደረጉት ንግግር መልሰው ማዲባን ኮት አድርገዋል። ኮት ሲያደርጓቸው የእሳቸውን የአስተዳደር ሥርዓት አንዲህና አንዲያ ነው አይደለም ያሉት። በመጸሐፉ እንዲህ ብሏል ነው ያሉት። ስለዚህ ዛሬ በቂ ክፍያ ላይከፈላችሁ ይችላል፤ ላትወደሱ ትችላላችሁ፤ ሳልጠራጠር የምናገረው ግን ሁሌም ሊያስወሳ የሚችል ሥራ ጥላችሁ ታልፋላችሁይሄ ብቻ አይደለም የፓርክ ንግግር፤ ሎሬት ጸጋዬንም አስታውሷል። ሎሬት ጸጋዬን ደፍረን መናገር የምንችል ኢትዮጵውያን ስንቶቻችን እንደሆን አላወቅም? ከእናንተ ማህበር ውጪ ስንወጣ እሳቸው ሲናገሩት ስሰማ ግን በጣም ነው ያስደመመኝ። ለካስ የኛው ሎሬት በእኛ በቂ ክብርና ውዳሴ ባያገኙም ለዓለም ያተረፉት፤ ያፈለቁት ዕውቀት ነበረ የሚል መልዕክት አስተላልፎልኛል“ 

ኢትዮጵያ - ሚኒስትሩ በንባብ ለሕይወት ላይ / Ethiopian Minister about Reading and Life


በቅንነት ለሚያው ሰው ፍጹም የሆነ አቅም አላቸው ዶር አብይ አህመድ ቀደምት የጥበብ ዕንቁዎችን ዕውቅና በመስጠት እረገድ። በንግግራቸው ሁሉ በአንድም በሌላም ጋሼ ጸጋዬ ይነሳል። ለዚህ ነው እኔ እሳቸውን በአባ ገዳ ጃዋር መሃመድ እና  በአቶ ሌንጮ ለታ ጋር አመሳስለው የሳሏቸው የጸሐፊ አቶ አሳማማው ወንዲራድን አቋም ሞግቼ እና  ተቃውሜ ትናንት አንድ ጹሑፍ የጻፍኩት።

የቅኔውን ንጉሥ ብላቴውን በውስጡ ያሰቀመጠ ሰው ከሰውነት ማዕከላዊ ሚዛን ይወጣል የሚል እምነት እኔ የለኝም። አሁን እኔ እንደ ቀደመው ሁሉ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ከዚህ መንፈስ ያፈነግጣሉ የሚል ቅንጣት ጥርጣሬ የለኝም። በቅኔው ልዑል መንፈስ የተቃኜ ማንኛውም ዜጋ ልቡም ነፍሱም ንጹህ ነው። ስለሆነም እንደ ሰው ባሉ ግደፈቶች ላይ የሰላው ወቀሳዬ ቀጣይ ቢሆንም ነገር ግን ኢትዮጵያን ከፍ በመድረግ፤ በማጉላት፤ በማበልጸግ ደረጃ ከመንፈሳቸው ተፈጥሮ ጠ/ሚር አብይ አይወጡም። ጋሼ ጸጋዬን ስትሰንቅ የሚሰጥህ የመንፈስ ብርታት አለ። ይህን እኔ ተዘርዝሮ በማያልቀው ፈተናዬ ውስጥ ያዬሁት፤ የሰለጠንኩበትም ጉዳይ ነው። ጽኑ ትሆናላችሁ።

የብላቴው መንፈስ ቢኖሩበት ውስጥን የሚያጸዳ፤ ተስፋ የሚቀለብ፤ ጽናትን የሚያወርስ፤ ኢትዮ አፍሪካዊነትን የሚያጎለብት እንጂ ከተፈጥሮ ውጪ የሚያደርግ አይደለም። ሊቃናቱ አብሶ የፖለቲካዎቹ ከዚህ መንፈስ ጋር አራባ እና ቆቦ ናቸው። ኢትዮጵያ በግንጥል ጌጥ ነውና እምትታሰበው እንዲያው ለሚያስቧት ማለቴ ነው። እማያስቧት ለሞቷ የተጉላት ደግሞ አሉና።

ኢትዮጵያዊ ተፈጥሮን በወስጡ ያደረ ሰው ብቻ ነው የብላቴውን መንፈስ የሚጠጋው። የትኛውም ሊሂቅ ሲሶ እና እርቦ ዜግነት ላይ ቆሞ ነው ኢትዮጵያን የሚለን። ስለምን ብላቴውን አልተማረውም፤ ብላቴውን አልተመራመረውም፤ በአንደበቱም በመንፈሱም አስቦትም ደፍሮትም አያውቀውም ሥሙን እራሱን ይፈራዋል። ውስጡ አሽዋ ስለሆነ። 

ሁልጊዜም እንደምለው ኢትዮጵያዊነትም አፍሪካዊነትም ለእኔ ብላቴ ሎሬት ጸጋዬ ገ/ መድህን ነው ነው፤ ለእኔ እንዲያውም ታቦቴ ነው። ባሰብኩት ልክ ተጉዤ ባሰብኩት ልክ የትውፊቱን ግርማ እና ሞገስ ለማስጠበቅ እንቅፋቴ ብዛቱ ቢያሰናክለኝም ጸሎቴ ግን ይህ ቀን እንዲመጣ ነበር።

ዛሬ ብላቴ የሥርጉተ ሥላሴ ብቻ አጀንዳ አይደለም። ሥርጉተ ሥላሴ ብቻም መከራ እምትቀለብበት አይደለም። ዛሬ የታቦቴ የቅኔው ልዑል የብላቴ ጸጋዬ ገ/መድህን ነፍስ ባለቤት አላት። ከዚህ በላይ እኔ የምፈልገው እምሻው ምንም ነገር የለም።

በሌላ በኩል እኔ አንቦን እምመለከታት በአምሳዬነት ጎንደር አድርጌ ነው። ይህ ስሜት ስለምን እንደተፈጠረብኝ ባላውቅም አንቦም ሲነሳ የጎንደር ያህል ይሰማኛል። ምን አልባት ከታቦት ጸጋዬ ጋር ባለኝ የውስጥነት የቅንነት ሀዲድ ሊሆን ይችላል። ለነገሩ የህዝቡ ሥነ -ልቦናዊ ትውፊትነት ከጎንደር ጋርም ብዙ የሚመሳሰልብኝ ሁኔታ አለው። ሰፋ ያለውን ትንታታኔ ለእድምታ ባለሙያዎች ሰጥቼ።

እሩጫዬ፤ ልፋቴ፤ ድካሜ፤ ብቻዬን መውጣት መውረዴ ግን እዮር አይቶ ባላሰብኩት፤ ባልጠብቅኩት ሁኔታ የጌታ ብላቴ ሎሬት ጸጋዬ ጣማራ የሆኑ የመንፈስ ሃብታቱ ልዕልና ዛሬ በአደባባይ እጬጌ ሆኗል። ይህንስ እንቶኔ ያሳግዱት ይሆን? አይቻላቸውም። ተሸንፈዋልም። ተመስገን!


ምን ሩቅ ቢሆን ተስፋ
እሱም ቅኔውም ምን እሩቅ ቢሆን
የቅኔው ትንቢትም ትፍስህት ሆኖ ግን ፈተናው ቢያልም
ምን ዳገቱን ለመርታት ጥልቅ ቢሆንም
ምጥቅ ቢሆን የባለቤቱ ህልሙም ሆነ መንገዱ
ምን ረቂቅ ቢሆን የምህንድስናው ብጡልነቱ ዛሬ ላይ በምልሰት የእሱን ውስጣዊ ተፈጥሮ ለምርምር ማዕከልነት መብቃቱ ሃሳቡ እራሱ ሰናይት ነው። 

እኔ በዬዓመቱ በምሰራው የሙት ዓመቱ መታሰቢያ የቅኔው ልዑል ብላቴ ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን ልንማረው የሚገባ ሌሰን እንደሆነ ነበር እማስገነዝበው። ምስጋና ቃሉ አነሰበኝ ለፈጣሪዬ ለልዑል እግዚአብሄር ለማቅረብ። በውነቱ ያንሳል። ይህን የበራ ቀን ያመጣ ፈጣሪ ይመሰገን። አሜን!

በዚህ ውስጥ ግን የዚህ መንፈስ ተቃርኖ የተሰለፉ ነፍሶች ደግሞ ልዑል እግዚእብሄር ለንሰሃ ያብቃቸው እላለሁኝ። ብዙ ነገር ነው ያጠፉት፤ ብዙ የመንፈስ ሃብት ነው የበከሉት፤ ብዙ የጥበብ ቤተሰቦችን ነው የበተኑት።

ብዙ ባለቤት የሌላቸውን የጥበብ ፍቅረኞች ነው የጉሮሮ አጥንት የሆኑባቸው። ነፍስ በፖለቲካ ጉዳይ ብቻ አትቀጥልም። መስኖ ያስፈልጋታል። የሚያለማ። ያ ደግሞ ጥበብ ነው። ሲዊዝ ብዙ ነገሯ ደርቆ፤ ነጥፎ፤ ጥገኛ እንድትሆን ተደርጓል። እዚህ ሲዊዘርላንድ ውስጥ በጸጋዬ ድህረ ገጽ እና ራዲዮ እጅግ ሰፋፊ የሆኑ ብሄራዊ ፕሮጀክቶች ነበሩ። ሁሉንም አከሰሉ፤ ሁሉንም አስበተኑ፤ ሁሉንም አመድ አደረጉ። የበቀለውን ነቀሉ።
  
ዛሬ ዓይናቸው እያዬ እነሱም እዛው ባዕት ላይ ሆነው የብላቴ ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን ልቅና፤ ቅኔያዊነት፤ እኛዊነት፤ የራስነገርነት፤ ሰዋዊነት፤ ስዋሰዋዊነት፤ ግሣዊነት፤ እጬጌነት እነሆ እዬተዘከረ ይገኛል። 

ቢቆረጥማቸው፤ ቢፈልጣቸው፤ ቢቆርጣቸው ያ እንደ ሰንሰለት የዘረጉት አፍራሽ ተቋማቸው እንሆ በጊዜ ፍች አገኜ። ዳኛም ሰብር ችሎትም ሳልማስን እዮር ቀኑን አበራልኝ። ሥርጉተ ሥላሴ በጸጋዬ ድህረ ገጽ ሆነ ራዲዮ ገንዘቧን ቀልቧን አቅሟን ከመገበር በስተቅር ለሸቀጥ አልነበረም ያን ያህል የተጋችው። ያን ያህል የተፋለመችው በግራ በቀኝ ከማህበረ ምቀኞች ጋር ስንቱን መከራ አሳለፍኩት?

ከእነሱ ሳልደርስ ሳልጠይቃቸው በቤታቸው ትውር ሳልል … እያሳዳዱ በዬሄድኩበት ሁሉ ብዕሬን ሲያሳግዱ፤ መንፈሴን ሲያሳግዱ በስውር በተተበተበ ሴራ አንዲትን ባተሌ ንጹህ እና ቅን ሴት ሲያስወግዙ፤ አሁን ለዛ ቅን መንፈስ ቀን ሰጥቶት አንድ የአገር ጠ/ሚር ባለቤት ሆነለት። ተመስገን!

„አግዚአብሄር በአንድም በሌላም ይናገራል፤ ሰው ግን አያስተውለውም“ ይላል አካል የሌለው የእግዚአብሄር አገልጋይ … ያን ጊዜ አብረውኝ የተሰለፉት ቅኖችም የመረጡት መስመር ትክክል እንደነበር ዛሬ ላይ ጊዜ ሚዛኑን ይዞ ከች ብሏላቸዋል። ዳኝነቱን ለእነሱ … ሥርጉተ ማለት ምን ማለት እንደሆነች እንዲተረጉሙት ጊዜ ሚዛን አስቀምጦላቸዋል።

ቢዘልቁ በጽናት አንድ ትልቅ ጉልበታም ሚዲያ ይወጣው ነበር … ሁለገብ ተግባራትን የሚከውን። ሚዲያ ብቻ አልነበረም በስደት አንድ ትውፊት አቅም ያለው፤ ብቃት ያለው ሲገነባ ትውልዳዊ ድርሻን መወጣት ነበር። በሌላው ጥገኛ ሆኖ ክብርን ሞገስን ለወዲያኛው ከማሸለም በራስ ውስጥ ሆኖ ራስን የአደራ ጉልላት ማድርግ ይቻል ነበር።  

በተረፈ እኔ ዛሬ ስለ ቅኔው ልዑል ምንም እምለው እምተርከው ነገር አይኖርም። መሬት እራሱ በዘመን ዳኝቷት አንግሳዋለችና። የፈለጋችሁ ጊዜው ያላችሁ የኔ ቅኖች ግን የቆዬውን ማዬት ትችላላችሁ። ቤቱንም ጎብኙለት ቅናቶኝ የተተናኮሉትን።

በመጨረሻ ድህረ ገጹን ባልቀጥልበትም ግን የተሠሩ የተወሰኑ ሥራዎች ብቻ ሳይሆን የቅኔው ልዑል የብላቴ ጸጋዬ ገ/መድህን ሥም በቋሚነት እንዳለ እንዲቀመጥ እንዲቀጥል በማድረግ ለተባበረኝ ክፍያውን ሳያቋርጥ እስከዛሬ 10 ዓመት ሙሉ ለሚከፍለው ታናሽ ወንድሜ አብዬን የእናቴ ፍሬ ከልብ የሆነ ምስጋናዬ አቀርብለታለሁኝ። በሁለቱም ተሳክቶለታል። ብጽዑኑ በክብር አገር ገብተውለታል፤ ብላቴውም መንፈሱ ዘውድ ደፍቶለታል። በአጸደ ነፍስ ይመርቀዋል።

በሌላ በኩል የብላቴ ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን ሙት ዓመት መታሰቢያ ጹሑፌን ሳያስተጓጉሉ፤ ሳይግዱ በፍጥነት በማውጣት የረዱኝ፤ የተባባሩኝ የዘሃበሻ ድህረ ገጽ እና የሳተናው ድህረ ገጽ አዘጋጆችን እግዚአብሄር ውለታቸውን ይክፈልልኝ።

እንዲህ ቀን ሊወጣ፤ እንዲህ ያ የጨለማ ጊዜ ሊያልፍ የአባታቸውን ትንግርት ይወደስ ይከብር - ይነግሥ ዘንድ ካለምንም ተዕቅቦ ያደረጉልኝ ትብብር፤ የሰጡኝ ሙሉ ፈቃድ ዘወትር የመንፈስ ስንቄ ነው። ልዑል እግዚአብሄር የልቦናቸውን ይሙላላቸው። አሜን!

ኢትዮጵያዊነት ተግባር ላይ እንዲህ ተፈጥኖ ይነጥራል። እንደ ሰው ኢትዮጵያዊነትን በከንቱ ውዳሴ  ብንጆቡነው እዬወለቁ መቅረት ነው ትርፉ። ተመልሶ ደግሞ ከእግሩ ሥር ወድቆ አዋጣን መባሉ ሌላ አማራጭ መንገድ የሌለ ስለሆነ መለመን ነው። … እሱኑ እባክህ አስጠጋኝ ብሎ የሙጥኝ ማለት፤

ኢትዮጵያዊነት … ለኢትዮጵያ የተጉት ሁሉ እኩል ማዬት፤ እኩል ማከብር ሲቻል ነው በውስጥ የሌሉትን መውቀስም መንቀስም የሚቻለው። አንተ በሌለህበት ሌላው የለበትም ለማለት ሞራሉ ከቶ ከዬት ይመጣል? ፈተና ነው። ግን ኢትዮጵያኒዝም አራማጅ ነኝ ብለህ ብላቴውን መንፈሱን አሳደህ አይሆንም …

ሌላው ግን አንቦ ስትነሳ ለወጥ እና ግንባር ቀደም ተጋድሎዋ ከጎንደር ጎጃም ጋር ይወሳል። አብሶ የኦሮሞ ማህረሰብ ወገኖቼ አንቦ ስለምን ማዕከል እንደሆነች ቢያስቡት አንቦ የኢትዮጵያዊነት አድባር ስለመሆኗ በጸጋዬ መንፈስ ውስጥ ፈጣሪ ሊያመሳጥር እነሱን ለማስተማር ነው ከዛ የተጋድሎው ችቦ አህዱ ያለው።

ይህን የሚተረጉማላቸው የእድምታ ዘመን እንዲኖራቸው እመኝላቸዋለሁኝ። ለዛሬው ይህን ያህል ተንጠራርቶ መገኜት መሰረታዊ ጉዳይ „የኦሮሞ ደም ደሜ ነው፤ ኢትዮጵያዊነት ሱሴ ነውን“ አምጦ ስላስወለደው ነው። በዚህ ውስጥ መሆን ተስኖህ ንፋስ እቀዝፋለሁ ካልክ ፍድር እና ዳኝነቱ የእዮር ይሆናል።

ኢትዮጵያዊነት አሸናፊ ባይሆን ኖሮ አንቦ ማዕክል አትሆንም ነበር። በፍጹም። 40 ዓመት አኮ እሱ ተከድቶ ብዙ በጣም ብዙ ነገር ተሞክሯል። ግን የቅንድብ ጸጉር ነው የተሆነው። ለዛሬው ትንፋሽ ኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው ለድል ሁሉንም ያበቃው። በክህደት ውስጥ የሚገኝ ነፃነት የለምና።

·       ምርኩዝ በምልሰት በጥቂቱ ለመቃኘት ለምትሹ አዱኛዎቼ።

! ያቺ ዓድዋ!“ 01.04.2018.

Laureat Tsegaye Gabre Medhin 2.24.2018.

የውስጥ እንደራሴእንደ ህዝብ … – ሥርጉተ ሥላሴ

የቅኔው ንጉሥ ፈላስፋየትውልድ ግሥ፤ የኑሮ ስዋሰዋዊምዕት፤ (የሎሬት ጸጋዬ /መድህን ሙት ዓመት መታሰቢያ)

ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው!“ የብላቴ ጌታ ሎሬት ጸጋዬ /መድህን ንዑድ መንፈስ
ትንሳኤ ነው

ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።

                                         ውዶቼ ኑሩልኝ።

                                         መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።