ልጥፎች

ከኦክቶበር 11, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ሥነ ግጥም - ለአረጋጊ ባለመክሊት ዬኛው።

ምስል
„አቤቱ የፊትህ ብርሃን በላያችን ታወቀ።“   መዝሙር ፩ ቁጥር፮ ከሥርጉተ©ሥላሴ 11.10.2018 ከጭምቷ ሰዊዘርላንድ *** ያን ቀን „ቀኑ“ ተከስቶ ወፍ ጎሽ! ብሎት ያዬሁ ለታ ስብሰለሰል ስወያይ „ከቀኑ“ ጋር እንዲያ ለ እ ፍታ መተከዜን ዘብ አቁሜ ለ አ ፍታ ብቻ ብቻ ህልም ሲፈታ እንዲያ እና እንዲህ ሲፈታታ፤ የነፍስ ውሽክታ - በመልካም የልብ ስንኝ ፈገግታ፤ የቅኔ ቤት፤ የዋሸራ፤ የመንፈቀ ሌሊት - ልዑቅ ዕድምታ ተረገጥ ሆነ የመገኘት የኔታ! ያለተረዱት ቢፈልጉት፤ ባይፈልጉት ያልፈለጉት ሳይረዱት፤ ባይረዱት የተረዱት በእሺታ አይሆ ንም ን አ ረዱት! ሲሆን ሲሆን ማታማታ የነበረ ለናት እንጂ አልነበረም ለህምታ። ሲያማክረው የሩቅ አገር ወፍ ያወጣው ያለስርቅታ ያ ቀንዲሉ የዘመን ተደሞታ፤ በአርምሞ - በክህሎቱ ተመስጦ ያለውካታ ቀነ የሰጠው የቅንነት ብርቱ እርካታ፤ የአባት አደር የወልዮሽ የሎሬቱ ገበታ! የህልመኛ ባዕት ብጡልነት ትርታ ያልነበረ ለቱሙታ፤ ግን እንጂ በቅብዕው ያልነበረው ቅሬታ ስለ ምህረት ተስፋው ስለዘለቄታ የንጽህና ድንግልና ግርምታ፤ የዘመን ሙሉ ስንዳታ! ሴራን ላይወዳጅ፤ ላይ ዳ በል ከካኳቴ ጋራ ከሆታ ቂምን ላይቋጥር፤ ሊሆንለት ብቻ ብቻ ለይሁንታ፤ የርህርህና አንበል ያ ብላቴና፤ ያ ከርታታ ከልብ እንጂ ማዳመጥን ማህተሙ የተመታ። በሩቅ ምናብ ሆኖ ሰታዘበው፤ ... ጥድፊያ ሲሮጥ ሲያሯሩጥ በትዝበቱ ሲከትብ ሲመሰጥ በእጬጌታ፤ አድብየለሽ ሲባክን ሲጋት የሲቃ ኩልልታ ... የጠዛ እልልታ ያ ባተሌ ልበቅኑ ይታደማል በጸጥታ። ሲያድጥ ሊያላልጥ የሸር ጎርምጥ አይ ተድሮ ሲኮበልል ሊሸ...

ቤተ መንግሥት ክራንች ላይ ያሉ ወገኖቸን ሲያከብር ማዬት ናፈቀኝ።

ምስል
ኢትዮጵያዊነት የውስጥ ሲሆን የመከራ ቋት ያመነጫል። „በጎውን ማን ያሳዬናል የሚሉ ብዙ ናቸው። አቤቱ የፊት ብርሃን በላያችን ታወቀ።" መዝመረ ዳዊት ፪ ቁጥር ፮ ከሥርጉተ © ሥላሴ  11.10.2018 ከጭምቷ ሲወዘርላንድ።                   የኔዎቹ እግራቸውን በደንብ አድርጋችሁ እዩት አደራ! መነሻ። https://ethiomedia.com/2018/10/08/famed-former-pilot-returns-to-ethiopia-after-years-in-eritrea-prison / Famed former pilot returns to Ethiopia after years in Eritrea prison እያማጥኩን ተመለከትኩተኝ የዚህን አራትዓይናማ ጀግና የእግር እጣቶች። እያለቀስኩኝ ተመለከትኩኝ የዚህን አርበኛ የሰራ አካላት። ወስጤ እርር ኩምትር በሎ አዬሁት የዚህን ብርቱ ሰው የህሊና ቁስለት። ከጠላት እጅ መግባት ይህን ያህል ዋጋ ያስከፍላል። ኢትዮጵያ ብትገኝም ይህን መሰል ሰቆቃ ይፈጸምበታል። ቁም ነገሩ አሁን ባለው የፍቅራዊነት ጉዞ ምን ያህሉን እጅ ለመፈወስ፤ ለመካስ ዝግጁነት አለ ነው። የቀሩትስ የኢትዮጵያ ልጆች እስረኞች በምን ሁኔታ ላይ ይገኛሉ? መቼነውስ ከጎደለው አካላቸው፤ ቅስሙ ከተሰበረው ሥነ - ልቦናቸው ጋር ለአፈራቸው የሚበቁት? ኢትዮጵያዊነት እንዲህ ይገለጻል። ለአንዱ ረመጥ ለሌላው ደግሞ ገነት፤ ለአንዱ የክብር መንበር ለሌላው ደግሞ የመከራ ግዞት። አዎን ኢትጵያዊነት ለቅኖች ሩህሩህ አይደለም። ለገሮች እራስ እግሩ መንገዱ ሁሉ ትሬኮላታ ነው። ኢትዮጵያ በሚቀኑበት ሰብዕና ውስጥ ልክ እንደ ጀግናው ፓይለት ኮ/ ታደስ ...

ኮ/ ጎሹ ወልዴ ለአብይ ሌጋሲ አማካሪ ቢሆኑ?

ምስል
ቅጥልጥልጥልጥል። የድንገቴ ደረሽነት ዘላቂ ጠያቂ ነው ፍትህነት። „ነፍሴ እጅግ ታወከች፤ አንተም አቤቱ እስከ መቼ ድረስ ነው?“ መዝሙር ፮ ቁጥር ፫ ከሥርጉተ©ሥላሴ 11.10.2018 ከጭምቷ ሲወዘርላንድ። ለኢትዮጵያ እኒህ የምርጥ ምርጥ ዕንቁ ዜጋ አሁኑኑ ያስፈልጓታል! ትንሽ ነገር ማለትን ፈለግኩኝ። ትናንት ተፈጠረ ስለተባለው ጉዳይ የእኔ ምልከታ ደግሞ ትንሽ ለዬት ይላል። ትንሽ ወደ ኋዋላ ልመለስ የ2010 መባቻ መስከረም ገፋ አድርጎ ወራት ሲከታተሉ የድንገቴው ሁኔታ ሱናሜ ነበር። ይህን ሱናሜ በእርጋታ በማስተናገድ እረገድ የቀደመው ኦህዴድ/ ኦዴፓ ይዞት የተነሳውን ዓላማ ለማሳካት ሰማይ እና መሬት ቢደባለቅ አለቅም ብሎ ሞጥሮ ከገዱ መንፈስ ጋር ሲታገል ነበር። በሱማሌ ክልል ወደ አንድ ሚሊዮን ህዝብ መፈናቀል፤ ቀጥሎም ሙያሌ አካባቢ 50 ሺህ ዜጎች መፈናቀል ብቻ ሳይሆን ወደ ኬንያ በርካቶቹ መሰደድ በሚመለከት የሚችለውን በማድረግ በተረጋጋ መንፈስ የቁልፍ ቦታ ባለቤትነት ላይ ትጋቱ የኦህዴድ እንደ ባህል መወሰድ የሚችል ይመስለኛል እኔ የታዘብኩት እንደዛ ነውና። ነገሮችን ተረጋግቶ መመልከት።  አሁን ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ወደ ሥልጣን ከመጡባት ማግሥት ጀምሮም መፈናቀሉ፤ ሞቱ፤ ሳቦታጁ በእጥፍ ቀጥሏል። እሳቸው ደግሞ በነበረው ሙቀት ልክ ተረጋግተው የሚችሉትን እዬከወኑ ነው። ይህ መረጋጋት የዶር ለማ መገርሳ፤ የዶር አብይ አህመድ፤ የአቶ ደመቀ መኮነን፤ የዶር ገዱ አንዳርጋቸው የመንፈስ አቅም ይመስለኛል። ዶር አብይ አህመድ አይደናገጡም። አይርበተበቱም። ይህ መልካም ነገር የሚያሳዬው በራስ የመተማመን አቅም ነው። ነገር ግን በራስ መተማመኑ ካልተመጣጠነ ቸለልተኝነት ፈጥሮ አደጋ ሊያስከትል ይችላ...