ቤተ መንግሥት ክራንች ላይ ያሉ ወገኖቸን ሲያከብር ማዬት ናፈቀኝ።

ኢትዮጵያዊነት
የውስጥ ሲሆን የመከራ ቋት ያመነጫል።
„በጎውን ማን ያሳዬናል የሚሉ ብዙ ናቸው።
አቤቱ የፊት ብርሃን በላያችን ታወቀ።"
መዝመረ ዳዊት ፪ ቁጥር ፮
ከሥርጉተ©ሥላሴ
 11.10.2018
ከጭምቷ ሲወዘርላንድ።



                 የኔዎቹ እግራቸውን በደንብ አድርጋችሁ እዩት አደራ!
መነሻ።
Famed former pilot returns to Ethiopia after years in Eritrea prison

እያማጥኩን ተመለከትኩተኝ የዚህን አራትዓይናማ ጀግና የእግር እጣቶች። እያለቀስኩኝ ተመለከትኩኝ የዚህን አርበኛ የሰራ አካላት። ወስጤ እርር ኩምትር በሎ አዬሁት የዚህን ብርቱ ሰው የህሊና ቁስለት። ከጠላት እጅ መግባት ይህን ያህል ዋጋ ያስከፍላል። ኢትዮጵያ ብትገኝም ይህን መሰል ሰቆቃ ይፈጸምበታል።

ቁም ነገሩ አሁን ባለው የፍቅራዊነት ጉዞ ምን ያህሉን እጅ ለመፈወስ፤ ለመካስ ዝግጁነት አለ ነው። የቀሩትስ የኢትዮጵያ ልጆች እስረኞች በምን ሁኔታ ላይ ይገኛሉ? መቼነውስ ከጎደለው አካላቸው፤ ቅስሙ ከተሰበረው ሥነ - ልቦናቸው ጋር ለአፈራቸው የሚበቁት?

ኢትዮጵያዊነት እንዲህ ይገለጻል። ለአንዱ ረመጥ ለሌላው ደግሞ ገነት፤ ለአንዱ የክብር መንበር ለሌላው ደግሞ የመከራ ግዞት። አዎን ኢትጵያዊነት ለቅኖች ሩህሩህ አይደለም። ለገሮች እራስ እግሩ መንገዱ ሁሉ ትሬኮላታ ነው። ኢትዮጵያ በሚቀኑበት ሰብዕና ውስጥ ልክ እንደ ጀግናው ፓይለት ኮ/ ታደስ ሙሉነህ የጥቃት ጎራዴውን መሽጓል።

የኢትዮጵውያን የብቃት ልክ እንዲህ ቅስሙ ተሰብሮ፤ አንገቱን ደፍቶ ማዬት ጥቃቷን የሚያወጡ ልጆቿን በዚህ መልክ በመቅጣት ይወሰናል። አሁን የምናዬው ትርምስ ሁሉ ኢትዮጵያን በጥርሳቸው ከያዙት መንፈሶች ጽንሰት የፈለቀ ነው።

የአብዩ ሌጋሲ ያልገባው አመክንዮ ይህው ነው። ለዚህም ነው ኢትዮጵያዊነትን ያጎሉት ጦላይ ላይ፤ ኢትዮጵያዊነትን በጥርሳቸው ያያዙት እና የተጸዬፉት ደግሞ በኢትዮጵያ በጀት እዬተንፈራሰሱ በቢአይፒ ደረጃ ጠባቂ ተመድቦላቸው ተቀማጥለው የሚገኙት።

ዓለም እንዲህ ላለ ሰብዕና ምቹ ናት። ዓለም ማህበርተኝነቷ ለመልቲዎች ነው። መልቲዎች ድልድያቸው ብዙ፤ ክብራቸው እና ልቅናቸው ደግሞ ጥልቅ ነው። የእውነት አርበኞች ደግሞ እንዲህ እንደ መከረኛው የኢትዮጵያን መከራ ተሸክሞ እንደኖረው እንደ ተገፋው ኮ/ ሙሉነህ ታደስ ይመስላል። 

ኢትዮጵያ በታሪኳ አይታው በማታውቀው ቅንነት እና የአማራር ልህቅና መገስገሷ የአዕምሮ ቁርጥማት የሆነባቸው እኩይ ድኩማን መንፈሶች ምንግዜም አይተኙላትም። የአሁኑ የራስ እግሩ ህውከት በወረፋ ቀጥሎ የሚታዬው ከዚኸው ነው። ሰንድቅዓላማው ያስበረግጋቸዋል፤ ተፈሪነቷ ያርዳቸዋል፤ ጉልላት መሆኗ የሚጠሏት ወንዶቹ ሳይቀሩ ያምጣሉ። ኢትዮጵያ አምላክ አላት። በፈተኗት ልክ ዋጋቸውን ያገኙታል። 

ትንሽ ምስጋነውን ባዘገዬውም የኢትዮ ሚዲያ ዋና አዘጋጅ አቶ አብረሃም በላይ የጸፈውን አርቲክል እያነበብኩኝ ምስጋናዬን በአክሮት ከዚህ ከኮሽ አይሏ ሲዊዝሻ ድረስልኝ አልኩኝ።

ኢትዮ ሚዲያ ቀደም ባለው ጊዜም በዚህ ጀግና ዙሪያ ብዙ እንደተጋበት አውቃለሁኝ። የአሁኑ ግን እጅግ ላቀብኝ። ራሱ አቶ አብርሃም በላይ ነው ጹሑፉን የጻፈው። እንዲህ ህይወት ፊቷን ለነሳችው ነፍስ ወገን ከጎን መቆም የጽድቅ መንገድ ነው። ለቀናላቸው ለበራላቸው ነውና ዓለም እምታረገርገው። 

ኢትዮጵውያንስ መሬት ላይ ያሉት ዜጎቿ ለእሷ ክብር እና ነጻነት እንዲህ ክልትምትም ላሉላት ሰብዕና ወይንስ ምድራዊው ስጋዊው ሁነት ይበልጥባቸው ይሆን? አዴፓ በትልቁ የሚለካበት ይሆናል። ትልቅ የቤት ሥራ እንጅባራ ሰጥቶታል ለአዴፓ። የዛ ሰንደቅ ክብር ነው እንዲህ የሚያንከራትት፤ እንዲህ እንደ እንጨት የሚያስፈልጥ፤ እንደ እንቁላል የሚያስቀቅል። አላዛሯ ኢትዮጵያ የዚህን ጀግና ልጇን ሁነት ስታይ ገመዷን ታጥቃ እዬዬ ትበል።

የዛ ሰንድቅ ዓላማ ባላባቱ፤ አውራው ለአገሩ ለሰንደቅዓላማው ክብር ሁለመናውን የሰጠ ጀግና እንዲህ አካሉ ጎድሎ፤ ቅስሙ ተሰብሮ ሁለመናው ተራቁቶ እንሆ ለብትን አፈሩ በቅቷል።

እና የኢትዮጵያ ህዝብስ ቀና ላለው፤ ለደላው ወይንስ እንዲህ ሆኖ በጠላት እጅ ወድቆ ለደቀቀው ከማን ጋር፤ ከማንስ ጎን ይሆን የሚቆመው፤ ያ ብሩክ ዮስፌ ገብሬስ መንፈሱ ይህን ጀግና በምን ሁኔታ ያስተናግደው ይሆን?መቼም እሱ የኢትዮጵያ የክፉ ቀን ውድ ነውና። የሃይማኖት ተቋማት ስለሰበነክ ምግብር ተቋም ፈጠረው እንዲህ በመሰለው ትጋት አይባትሉም፤ ጄቲቪ ግን አብነቱ ለራሱ ለመንግሥትም ነው። መረዳዳት መተጋጋዝ ሁሉም እንዲህ የድርሻውን ሲወጣ አገር ትቆማለች። በስተቀር ግን አብሮ መክሰል ነው።

ራሱ የፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ ቤተ መንግሥት ገበርዲን እና ከረባት ብቻ ወይንስ የጀግኖችን ጀግና ይህን መከረኛ ክራንች በሙሉ አካሉ ሄዶ አካሉ የጎደለውን ያስተናግድ ይሆን? ፈተና ነው። ሁሉም ይፈታናል። ሚደያዎችም ይታያል ጉዳቸው። 

 እስከ አሁን ባለው ኢትዮ ሚዲያ የተግባር ጌታ ነው። እሱን የሚመጥን ተግባር ማን ይከውናል ነው ቁም ነገሩ? አዲሱ ትውልዱስ አገር ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንዴት ይማርበታል? እንዴት ነው ኢትዮጵያዊነት በዚህ የሁሉም ነገር ቁርሾ በተወራረደብት ጀግና ላይ ተስሎ ይሁን ተፈጥሮ የሚታዬው? ፈታኝ ነው!   

ሌላም አለኝ ዛሬ። ካፒቴን ዮሖንስ ተስፋዬ ስለ ገበሬው ካፒቴን። በናፍቆት የተለመውን የልጅነት የበራራ ፍላጎቱን አቋርጦ ፍዳውን ከፍሎ ያገኘውን ዕድል እርግፍ አድርጎ ትቶ ሞፈር እና ቀንበር ጋር፤ ከዋልካ ጭቃ ጋር፤ ከድህንት ጋር ሙግት የሚገጥም ሌላ ጀግና ደግሞ አገር የለህም፤ ዜጋ አይደለህም ተብሎ እንዲህ ተሸሽጎ ገበሬ ሆኖ ይኖራል። 

ስንት ጊዜ ይማጥ?! ስንት ጊዜስ ይለቀስ? ስንት ጊዜስ ይተከዝ? ይህን መቼም ልዕልት ቤትሻ ታፈስ ታየዋለች ብዬ አስባለሁኝ። ትንሽ የአማራ መከራን እንደ መጫን ያደረገችው ግብብግ ስለነበር።



‹‹ከባርነት ሞትን እመርጣለሁ!›› ያለው ካፒቴን ዮሀንስ ተስፋየ ህይወቱን በግብርና እየመራ ነው፡፡


ሌላው ፓይለት ደግሞ የሚሰራው አጥቶ ወጣቱ ጡረተኛ ፓይለት ሆኖ አሜሪካ እንደገባ ሰሞኑን ተዝገቧል፤ ሌሎችም በእስር ቤት ያዬዩትን መከራ አይተናል፤ ጀግና ሃይለመድህን አበራም መሰሉ ግፍ ሊፈጽመበት ሲል አወራ የሆነ የአልደፈረም ተግባር ከውኖ ሲዊዘርላንድ ይገኛል።
የዚህ መነሻ እና መደረሻ አንድ ጉዳይ ነው። 



ዜግነት ሳይሆን የቤተ ሰብ የዘር ሐረግ አማራ መሆን ነው። መከራው ይሄ ነው። ቀንበሩ ይሄው ነው። የሁሉም ቁርሾ ማወራረጃው ይሔው ነው። አንደበት ቢሶች ያሳዝኑኛል።

ፈጣሪ የፈጠረው ፍጡር እንዲህ በዬተገኘበት ሁለመናው በመዶሻ እዬተከተከተ ለሰው ሰራሽ ማንፌስቶ ካላደራችሁ ኋላቀር ናሽችሁ የሚሉት ቧልት ልብ ተረከዝ ላይ የበቀለ ያህል ይሰማኛል። 

ህሊና የሚባል ነገር አለ። አማራ ለዚህም መሰሉ ፋሽስታዊ ግፍ መቋቋም የሚያስችለው ራሱን ችሎ በብሄሩ ከመደራጃት ሌላ መፍትሄ የለውም። ጉዳዩን በባለ ጉዳዩ እንጂ በስማ በለው እማ 50 ዓመት ሲጋለብበት ተኖረ። 
በዛ ሁሉ ትግል ለፍሬ ያልበቃው ቁሞ ቀር ፍላጎት ሲዳከር ተኑሮ አሁንም እንደለመደበኝ ልናድህ ሊሆን የሚገባው አይደለም። አጋለባለሁ የሚል ነፍስ ካለ ግን ከልካይ የለበትም። መወገዝም የለበትም። ሲደርሰው ያውቀዋል። እንደኛ ሲታሽ፤ ተቀብሮ መረማመጃ ሲሆን።

ዘመን ቢለወጥ ሁኔታ ቢለወጥ ይህ መከራ ይቀል ይሆን ብዬ ስጠይቅ በፍጹም ነው መልሱ። አሁን እኔ ልዕልት ቤተልሄም ታፈስ እና የአብን ሊቀመንበር የዶር ደስአለኝ ጫኔ ቃለ ምልልስ ደጋግሜ ሳስበው እና ሳደምጠው ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚወረስ ቅብብሎሽ እንዳለ ይታዬኛል። 

ያውም እሷ የወንጌል ጽኑ አማኝ ናት። ለሃይማኖቷ ቀናኢ ናት። ነገር ግን ሰው በሚለው ማዕቀፍ ውስጥ ቂም ቁርሾን ለመገልጥ የሄደችበት መንገድ ፈጽሞ ከምትከተለው ሃይማኖትም ይልቅ የቀደመው የግራ ዘመም ዝንባሌ ቤተኛ ትወልድ ሳትሆን ግን ሆና ነው የተገኘቸው። በሲሪንጂ ለሁሉም የተወጋው ነገር አለ። አማራነት መነቀል አለበት። አማራነትን ቅስም መሰበር። አማራነት መፍለስ አለበት ተብሎ ተመስጥሮ ተይዟል። ይህም ሌላው ቁልል ቀጣይ መከራ ነው።

ወጣት ሚኒሊክ ተሰማ፤ ወጣት ወንድወስን ተሰማ፤ ወጣት አለማዬሁ ተሰማ የአንድ እናት እና አባት ልጆች ናቸው። ሌላ የአክስት ልጅም አለበት ወጣት ዳንኤል አጎናፍር እነሱን የበላ ጅብ አልጮኽ ብሏል።

 እናታቸው እንደተንሰፈሰፉ በናፍቆት፤ በትካዜ፤ በሰቀቀን፤ በስጋት ውስጥ ሆነው አልፈዋል። እዮር የዚህን ግፍ አንድ ቀን ያወራርደዋል። እነኝህ ወጣቶች ያን ጊዜ ወጣት የነበሩት የት እንዳሉ፤ በምን ሁኔታ እንደሚገኙ፤ ይሙቱ ይኑሩ አይታወቅም፤ አማራነት እንዲህ ነው ፍዳን መከፍል የመፈጠሩ ኢትዮጵያ መሬት ላይ ሚስጢሩ ይህው ነው።


በመንግሥት የደኅንነት ኃይሎች ተጠልፈው የተወሰዱና የደረሱበት ሳይታወቅ የቀየ ዜጎች ጉዳይ


ኢትዮጵያዊነት አማራነትን ለማዳን አቅመ ቢስ ነው። ስንት የሌላ ብሀረሰብ ሊሂቃን እዛ ኤርትራ ሄደዋል፤ አብረው ሰርተዋል ይህን የመሰለ አሰቃቂ ኢ-ሰባዕዊ ድርጊት ግን አልተፈጸመባቸውም። 

እኔ እንደ ሥርጉተ "በሽታውን ያልተናገር መዳህኒቱን አያገኘም" እና አማራ በተጠናከረ ሁኔታ ለራሱ ዘብ መቆም አለበት ብዬ ነው እማምነው። በስንት ፍዳ እና መከራ ስንቱን መጠራቅቅ አልፈው የወጡትም የአማራ ሊሂቃን፤ ገና ይወጣሉ ተብሎ የሚታሰቡትንም የጀግና ልጆች የሚባሉትንም ለማስተናገድ ኢትዮጵያ ቦታ የላትም።

በሌላ በኩልም የኮነሬል አንተነህ ደምሰው እጣ ፍንታም ሞጣ ታነባበታለች። እስር ቤት ልታመልጥ ነበር ተብሎ በሁለት ጥይት ተመቶ አካለ ስንኩል ሆኖ ቀርቶል።


የዘር ጥፋት የለም ብላ ለምትከራከረው ቤተልሄም ታፈሰ ደግሞ የአንድ ልጅ አባቱ የአቶ ዮናስ ጋሻው ህይወት በቀንበጥ ሥነ - ልቦናው መታረዱ እዚህ ላይ ይገኛል። አቶ አበ ካሴም መሰሉ እንደተፈጸመባቸው አዳምጠናል። ወንዶች የዘር ፍሬያቸው ሴቶች ደግሞ የሚያመክን መዳህኒት ይሰጣቸዋል።


ይህ አጠቃላይ ሥዕል የሚያሳዬን አገር ወስጥም አማራ ሆኖ መቀመጥ አይቻልም ተሰዶም ፍዳ መሆኑን ነው። ስለዚህ አማራ ቢያንስ አባቶቹ ያቆዩት አገር አለውና አገሩን አገር የማድረግ ታላቅ ተልዕኮውን ለመወጣት ራሱን በማዳን እንቅስቃሴ መጀመር አደራጅቶ እና አጎልብቶ መቀጠል ለድርድር የሚቀርብ አይሆንም።

አገር አገርህ ነው ተብሎ ህልውናው እስኪታወቅ ድረስ በአንድ ማዕቀፍ አማራነቱ ተደራጅቶ ተጋድሎውን ሰላማዊ በሆነ መንገድ መቀጠል አለበት።  እኔ ከ እንግዲህ ስለ ጦርነት ራሱ ቃሉን መስማት አልሻም። 

ሞረሽ ወገኔም የአማራን ሰቆቃ የዘገበብትን ጥናታዊ መጽሐፉን ለልዕልት ቤተልሄም ታፈሰ፤ ለማከብራቸው ለዶር ገመችስ ደስታ መላክ ይኖርበታል። እንዲሁም እሱም መሳደዱ ያልቀረለት ገደም ገብቶ የነበረው ጸሐፊ እና ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋውም ለኤል ቲቢ አወያይ እና ባለቤት እንዲሁ በአማራ መከራ ዙሪያ በጥናት የተደገፉ መጻሕፈቶችን በአድራሻ መላክ ይጠብቅባቸዋል። ትግሉ በሁሉም ዘርፍ መሆን ይኖርበታል።

አማራ እንደ ሰውም ሊታይ አለመቻሉ ተጋድሎ የህልውና ስለመሆነ የሚርመጠምጣቸው መንፈሶች ሁሉ በመረጃ የተደገፈ ስለመሆኑ ሊላክላቸው ይገባል። ከሊቅ እስከ ደቂቅ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሊሂቃኑ የፈሩትም ሚስጢር ይታወቃል። የአማራ የህልውና የማንነት ተጋድሎ ለማለት አልተደፈረም። ሃብቱ ጥሪቱ ጥሬ ሃብቱ ደግሞ ይፈለጋል። ቧልት። ሟልትን ለባልተኞች ሸልሞ አማራ "ሙያ በልብን" መተግበር አለበት። 

ግን አማራ በሰፈረ ማርስ እንዲያው ብጣቂ ብናኝ አፈር ቢያገኝ እዛ ያመልክት ይሁን? ከቶ የት ይደረስላቸው?

የአማራ ተጋድሎ ይቀጥላል!
የኔዎቹ ኑሩልኝ።

መሸቢያ ጊዜ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።