ሥነ ግጥም - ለአረጋጊ ባለመክሊት ዬኛው።

„አቤቱ የፊትህ ብርሃን በላያችን ታወቀ።“
 መዝሙር ፩ ቁጥር፮
ከሥርጉተ©ሥላሴ
11.10.2018
ከጭምቷ ሰዊዘርላንድ




***

ያን ቀን „ቀኑ“ ተከስቶ ወፍ ጎሽ! ብሎት ያዬሁ ለታ
ስብሰለሰል ስወያይ „ከቀኑ“ ጋር እንዲያ ለፍታ
መተከዜን ዘብ አቁሜ ለፍታ
ብቻ ብቻ ህልም ሲፈታ እንዲያ እና እንዲህ ሲፈታታ፤
የነፍስ ውሽክታ - በመልካም የልብ ስንኝ ፈገግታ፤
የቅኔ ቤት፤ የዋሸራ፤ የመንፈቀ ሌሊት - ልዑቅ ዕድምታ
ተረገጥ ሆነ የመገኘት የኔታ!

ያለተረዱት ቢፈልጉት፤ ባይፈልጉት
ያልፈለጉት ሳይረዱት፤ ባይረዱት
የተረዱት በእሺታ አይሆንምረዱት!

ሲሆን ሲሆን ማታማታ
የነበረ ለናት እንጂ አልነበረም ለህምታ።

ሲያማክረው የሩቅ አገር ወፍ ያወጣው ያለስርቅታ
ያ ቀንዲሉ የዘመን ተደሞታ፤
በአርምሞ - በክህሎቱ ተመስጦ ያለውካታ
ቀነ የሰጠው የቅንነት ብርቱ እርካታ፤
የአባት አደር የወልዮሽ የሎሬቱ ገበታ!

የህልመኛ ባዕት ብጡልነት ትርታ
ያልነበረ ለቱሙታ፤
ግን እንጂ በቅብዕው ያልነበረው ቅሬታ
ስለ ምህረት ተስፋው ስለዘለቄታ
የንጽህና ድንግልና ግርምታ፤
የዘመን ሙሉ ስንዳታ!

ሴራን ላይወዳጅ፤ ላይበል ከካኳቴ ጋራ ከሆታ
ቂምን ላይቋጥር፤ ሊሆንለት ብቻ ብቻ ለይሁንታ፤
የርህርህና አንበል ያ ብላቴና፤ ያ ከርታታ
ከልብ እንጂ ማዳመጥን ማህተሙ የተመታ።

በሩቅ ምናብ ሆኖ ሰታዘበው፤ ... ጥድፊያ ሲሮጥ ሲያሯሩጥ
በትዝበቱ ሲከትብ ሲመሰጥ በእጬጌታ፤
አድብየለሽ ሲባክን ሲጋት የሲቃ ኩልልታ ... የጠዛ እልልታ
ያ ባተሌ ልበቅኑ ይታደማል በጸጥታ።

ሲያድጥ ሊያላልጥ የሸር ጎርምጥ
አይ ተድሮ ሲኮበልል ሊሸመጥጥ ያሻማጥጥ
ግንስ አለ አንድዬ ሆምጣጤን የሚያስምጥ።

አያ እንቶኔ ያ ኢጎኛ ስብራትን፤ ሰንጥቃትን ሲሰለስል
ጉርሽጥ ቢሆን እንሶስላን ሲያንከባልል
ዙር ተመለስ የድንብልብል ዝርግ ድንብላል
ፍርስት ጥሰት፤ የፍርሻ እጢ የቁርሾ እንክብል፤
እንቅልፍ የለሽ እለታዊ የሸር ግልገል።

ፊት - ለፊት፤ ውስጥ ለውስጥ
ገጥም - ለገጥ፤ የሃቅ ሰርጥ
ሁነኛነት - መሆንነት - ማኛ የፈረጥ
እኛዊነት የሩህ ብሩህ ባለትውፊት ስለጌጥ።

ጥበብ ድንቂት በክህሎቷ
ለጣትም ሰውነቷ
ለሱ አደረች ሥህነቷ፤
ብልሃቷ ነው ውበቷ።

የትም ይሂድ - የትም ይሁን?
መቼም ይሁን - መቼ ይሁን?
ለምን ይሁን - እንዴት ይሁን?
ወዴት ይሁን  -እስቲ ይሁን?
የትህትና አንባሳደር ንብም ይሁን
ብቻ ብቻ የአብሥራ የናት ይሁን!

ብስጭትን በፈገግታው ብቻ ወጊ
ዓይነታነት ምርት ሰንዳቂ፤
ቁጣ አርጋቢ ድል አደራጊ
በመሆን ውስጥ አጋጊ!

·        ተጻፈ 11.102018 ሲዊዝሻ
·        እርእሱ ትርታ ነው።


/ አብይ ሰልፍ ከወጡት ወታደሮች ጋር ስፖርት ሲሰራ


ኢትዮጵያዊነት ብልህነት!
ኢትዮጵያዊነት ከዕውቀት በላይ ነው!
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
ማለፊያ ጊዜ።






አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።