ልጥፎች

ከሜይ, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ጭንቁ ሌቦቹ አቅም አገኙ ነው።

ምስል
              ጭንቁ ሌቦቹ አቅም አገኙ ነው።  ለውጡን የመቀማትም ዕድል ሊኖር መቻሉ መጤን አለበት።                                                                       ከሥርጉተ ሥላሴ 28.05.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ ) „የኢትዮጵያ ቶጳዝዮን አይተካከላትም፤ በጥሩ ወርቅ አትገመትም። እንግዲያሳ ጥበብ ከወዴት ትመጣለች? የማስተዋልስ ስፍራ ወዴት ነው? ከሕይዋን ዓይን ሁሉ ተሰውራለች። ከሰማይ ወፎች ተሸሽጋለች። ጥፋትንና ሞት ወሬዋን፣---  በጆሮቻችን ሰማን ብለዋል።“ (መጽሐፈ እዮብ ምራፍ ፳፰ ከቁጥር ፲፱ እስከ ፳፪) ·                                        መቅድም። ታዲያ ወያኔ ሃርነት ትግራይ የማንን ጎፈሬ እንዲያበጥር ይጥበቃል? የቡላ አጥሚቱን፤ የጎን አጥንት ሾርባውን አዘጋጅተን ስናገጠግጠው በጡጧ ሰነባብተን የለም። ለወያኔ ሃርነት ትግራይ እኮ አቅሙን ያደራጀንለት እኛው እራሳችን ነን። ለውጡ ሊቀለበስ እንደሚችልም ማሰብ ይገባል። ምክንያቱም ትግሉ ከለውጡ ጋር ነውና። በተቃዋሚ ሥም ገንዘብ የከፈለ ሁሉ ምርጥ ዜጋ ነው።  ስለሆነም በአገኘው ተቀባይነት እና ዕወቅና ሽንጡን ገትሮ ቀን ሲገነባ ሌሊት ሲያፈርስ ነው የከረመው። የትኛው ሚዲያ ነው ይህን ለውጥ ደግፎ የተነሳ? የትኛው? አንዲት ነገር እዬመዘዘ ሲታመስ አይደለም የተከረመው። እያንዳንዱ ሂደትን በስላቅ ሲዥጎረጎር አይደለም የተከረመው። ለውጡን የሚቃወሙ ሰዎች እዬተፈለጉ አይደለም ቃለ ምልልስ እንዲያደርጉ ሲደረግ የተከረመው። በምክንያቶች ላይ ሳይሆን በሳቢያዎች እና በዘሃቸው ላይ ብቻ ነበር ውርክቡ። የትኛው ሰው ነው ለውጡን በጤነኛ መንፈስ የሚይ ቃለ ምልልስ የተደረ

UEFA Champions League 2018.

ምስል
                አሳዛኙ ስውር የራሞስ ሴራ አሸነፈ።                                  ከሥርጉተ ሥላሴ 27.05.2018 (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።)                „ልጄ ሆይ በክፉ ሰዎች አትቅና፣ ከእነሱ ጋር መሆንን አትውደድ፣ ልባቸው ግፍን ታስባለች እና፣                     ከንፈራቸውም ሽንግላን ትናገራላችና።“ (መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፳፬ ቁጥር ከ፩ እስከ ፪ ።) የ2018 የአውሮፓ ሻንፒዮን ሊግ የዋንጫ ውድድር ፍጻሜ ቀን ነበር - 26.05.2018። እኔ ለሁለቱም ቡድኖች በተመጠነ ስሜት ለመከታታል ነበር ዕለቱን የታደምኩት። ምክንያቱም እኔ ወይ ከገዳመ አገር ከሲዊዝዬ አንድ ክለብ ወይ ከጀርመን ባዬር ሙንሽን / ዶርትሙንድ ቢኖሩልኝ ነበር ምኞቴ። የሆነ ሆኖ ያው ዘረ ዶርትሙንድ ስለነበር የተሻለ የስሜት ዝንባሌ ነበረኝ። የአስልጣኝ ዩርግን ክሎፕ አብነታዊ የውሳኔ ሰብዕና እጅግ ስለምመሰጠበት ዝንባሌዬ ለሊቨርፑል ነበር ማለትን በእርግጠኝነት መናገር እችላለሁኝ። ያው የጠይም ዕንቁ ቤተመንግሥታዊ የሰርግ ማግስትም ስለሆነም ወደ እዛ ወፍ ቢያዳላ ምርጫዬ ነበር። በዛ ላይ አፍሪካዊነትም በኮብነት ሴኒጋል እና ኢጅብት በጉልሁ አለበት። የስፔን ደጋፊ ሆኜ አላውቅም። በተለያዩ ሁነቶች በገጠሙኝ አመክንዮች የተጫኝነት መንፈስ አለባቸው። ·          እ ንዲህ ነው የሆነው … እንዲህ በኮከብነት ተጫዋችነቱ የስፔኑ ብሄራዊ ተጫዋች ራሞስ ከአገሩ ክለቦችም ለሪያል የረጅም ጊዜ ተጨዋች ነው። ዛሬ የሰራው ሴራ ግን ፈጣሪ አምላክ አንድ ቀን ብድሩን ይሰጠዋል። እንዲዚህ መሰል ከጨዋታ ህግ ውጪ በረቀቀ ሁኔታ ሴራን አቅደው የሚከውኑ ስፖርተኞች መጨረሻቸው በዝምታ የተከደነ ይሆናል። ዓ

ክቡር ተዋናይ ኪሮስ ኃ/ሥላሴ።

ምስል
                       ለባለግርማው የጥበብ ክህሎት                          ለተዋናይ ኪሮስ ኃ/ሥላሴ                             ምህረቱን ይላክ አዶናይ                                        „አሜን!“                               ከሥርጉተ ሥላሴ 25.05.2018 (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።) „ምንም እንኳን በለስም ባታፈራ፣ በወይን ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፤ የወይራ ሥራ ቢጓደል፤ እርሾችም መብልን ባይሰጡ፤ በጎችም ከበረቱ ቢጠፉ፤ ላሞችም በጋጥ ውስጥ ባይገኙ፤ እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤ በመዳህኒቴ አምላክ ሐሴት አደርጋለሁኝ። ጌታ እግዚአብሄር ሃይሌ ነው። „አሜን!“ ይሁንልን! ይደረግልን! (ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ከቁጥር ከ፲፯ እስከ ፲፰) የውስጥ መስመር ... ጥበብ ዘር የላትም፤ ጥበብም ፍቅር ናት፣ ጥበብ ቅርጽ የላትም፤ ጥበብ ብርሃን ናት፣ ጥበብ ፎርም የላትም፤ ጥበብ ነባቢት ናት፣ ጥበብ ቀለም የላት፤ ጥበብ የሁሉም ናት፣ ጥበብ መኖርም ናት መልካም ሐዋርያ ትርሲታዊ ሰናይ፣ ለፈቀዳት ሁሉ የምታደላድል የመንበር የበላይ። ·          ጥበብ እንዲህም ናት … የትህትና መዝሙር የአገልግሎት ዝክር የድካም ዕንቢልታ የጥንካሬ በር። መች ሆና ስታውቀው ጥበብ ወረተኛ የትውፊት ውሃዋ የዓይን ዘበኛዋ። ·          ጥበብ ፊት አትሰጥም … ጥበብ አይደለችም የጉድፍ አንቀልባ የልዩነት ዳባይ ጥበብ ጎታ የላት ለኩፉኝ እኩይ። ጥበብ ፊት አትሰጥም ለስንኩሉ ገደል ለሃሰት ቃል አባይ፤ ጥበብ አይደለችም የክፋት ኩነኔ የክፉ ላብ ብካይ። ሰነፍ ጥበብ የለች አልተፈጠ

Toni Dreher-Adenuga GNTM 2018.

ምስል
ሞዴል Toni Dreher-Adenuga    የ አፍሪካ የውስጥ ውበት የ2018                  የጀርመን ቆንጆ ሆና                   ዛሬ ተመረጠች። ከሥርጉተ ሥላሴ 24.05.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።)   „ከቸር ሰው ጋር ቸር ሆነህ ትገኛለህ፤ ከቅን ሰው ጋር ቅን ሆነህ ትገኛለህ፤ ከንጹህ ጋር ንጹህ ሆነህ ትገኛለህ፤ ከጠማማ ጋር ጠማማ ሆነህ ጥገኛለህ።“ (መዝሙር ምዕራፍ ፲፯ ከቁጥር ፳፭ እስከ ፳፮) እሺ የኔዎቹ አፍረካዊነት ዛሬ አማራበት። ቶኒሻ አሸነፈች። ያሸነፈችበት ፎቶ አሁን ያሁ ለጥፎታል ግን ጥራቱ እንብዛም ስለሆነብኝ ሌሎችን መምረጥ ግድ አለኝ። ብቻ ማሸነፍ እንዴት ደስ ይላል? እንዴትስ ይደላል? ደስታ እንዴት ውብ ነገር ነው። ዛሬ ግንቦት 24.2018 እ.አ.አ አቋጣጠር ያን ረጅም ፈተና ተሻግራ አፍሪካዊቷ የ18 ዓመቷ ቶኒ ድንቅዬ የጀርመን ምርጥ ቆንጆ ሆና ተመረጠች። ቶኔ ውበቷ ውስጧም ነው። የተመረጠችው እሷ ብቻ አይደለችም አፍሪካም እንጂ። የተመረጠችው እሷ ብቻ አይደለችም ሙሉ ሞራሏ አንጂ። ይህች የ18 ዓመት ወጣት ለጋራ ሥራ ብቁነቷን በትዕግስት የጠለፈች የመቻቻልም አብነት ናት። ቶኒ ሁልጊዜ ከፊቷ ፈግግታ የሚታይባት ፎሎቄ ወጣት ናት። ቶኒ ለካፋቸው የውድድሩ ተሳታፊዎች ሁሉ አጽናኝ፤ አበረታች፤ ሃይልና ጉልበት ሰጪ ጠይም ዕንቁ ናት። ቶኒ ተፈጠሯዋን ትወደዋለች። ቀለሟን ትውደዋለች። የሚሰጣትን የቤት ሥራ በአግባቡ ትክውናለች። ታዳምጣለች። ዓላማዋን ያወቀች ወጣት በመሆኗ ከጀርመንም ባለፈ ዓለም ዓቀፍ ዕድሎችን ወደፊት በስፋት እንደሚገጥማት በጣም እርግጠኛ ሆኖ መናገር ይቻላል። ሞድ የጋራ ጉዞ፤ የጋራ ሥራ፤ የጋራ ሃላፊነት፤ የጋራ አክብሮት፤ የጋራ ክንውን የሚጠይቅ ሲሆን መቻቻልን