የሰኔሉ መደመር። የቹቻቸው መደመር!
ነፍስ ይማር … „ኃጢያትን እንደ ውኃ የሚጠጣ ሰው ምንኛ ያንስ?“ መጽሐፈ እዮብ ፲፭ ቁጥር ፲፮ ከሥርጉተ ሥላሴ Sergute Selassie 23.06.2019 ነፍስ ይማር ለሜ/ጄ ብርኃኑ ጁላ የጦር ኃይሎች ጠ/ አዛዥነት የሥልጣነ ሹመት እና ለጃዋራዊው የጢቾ ባላባት ለአቶ ንጉሱ ጥላሁን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ፕሬዚዳንትነት ሲባል መስዋዕትነት ለከፈሉት ለዶር አንባቸው መኮነን እና ለጄ/ ሳህረ መኮነን፤ በተጨማሪም ለአቶ እዘዝ ዋዜ ህልፈት። እጬጌውን ሂደት ታሪክን ይፍረደው፤ ነፍሳቸውን አርያም ገነት ፈጣሪ ያስገባልን። ለኦነጋውያኑ የምንፈስ ልዕልና ሲባል ለተገበሩት ወገኖቻችን። አሜን! ኩዴታ ነው ካለ የ ኢትዮጵያ መንግሥት ኩዴታውን ያካሄዱት እንሱው እራሳቸው ነፍሳቸው ለጊዜው ምድር ላይ ያሉት ይሆናሉ ... ፎቶውንም ይናገራል። ጠርዝ ላይ ኩዴታ ተካሂዶ አያውቅም። የ አዲስ አባባው ግር ግር ቁሮ ነው ...መለበጫ መስትሽ። ለኦነጋውያኑ የድል ዕለት ብቻ ሳይሆን ለግባቸው አንድ ትልቅ የመገናኛ ድልድይ እርካብ ነው። እነሱ ባቀዱት ልክ አትርፈዋል። ለካቴና ራት እንዲሆኑ ለተፈለጉት ለብ/ጄኒራል አሳምነውና ጽጌ እና ለጓዶቻቸው ደግሞ ጽናቱን ብርታቱን ይስጣቸው። ይህ ሁለት ዓላማ አለው። ህወሃትን ለማስደስትና ልቡ ትንሽ ቢራራ ተብሎ ነው። ተራ በተራ ግን ለአንሳ ሥጋ እዬሰጡ ወደ ማረጃው እንደሚወሰደው ሁሉም ይደርሰዋል የጊዜ ጉዳይ ነው። ሌላው ግን ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት ከተመረጡ ጀምሮ ሥራቸው አጀንዳቸው የአማራ ብሄርተኝነትን ማጠውልግ እና መቅበር ለሆነው አብይወለማ መንገድ ጥሩ ባይታሚን ነው። የአማራን ቅስም ለመሰበር፤ ጃዋረዊው የጢቾ ባላባት አቶ ንጉሡ...