የሰኔሉ መደመር። የቹቻቸው መደመር!

ነፍስ ይማር …
„ኃጢያትን እንደ ውኃ የሚጠጣ ሰው ምንኛ ያንስ?“
 መጽሐፈ እዮብ ፲፭ ቁጥር ፲፮
ከሥርጉተ ሥላሴ
Sergute Selassie
23.06.2019


ነፍስ ይማር ለሜ/ጄ ብርኃኑ ጁላ የጦር ኃይሎች ጠ/ አዛዥነት የሥልጣነ ሹመት እና ለጃዋራዊው የጢቾ ባላባት ለአቶ  ንጉሱ ጥላሁን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ፕሬዚዳንትነት ሲባል መስዋዕትነት ለከፈሉት ለዶር አንባቸው መኮነን እና ለጄ/ ሳህረ መኮነን፤ በተጨማሪም ለአቶ እዘዝ ዋዜ ህልፈት። 





እጬጌውን ሂደት ታሪክን ይፍረደው፤ ነፍሳቸውን አርያም ገነት ፈጣሪ ያስገባልን። ለኦነጋውያኑ የምንፈስ ልዕልና ሲባል ለተገበሩት ወገኖቻችን። አሜን!

ኩዴታ ነው ካለ የ ኢትዮጵያ መንግሥት ኩዴታውን ያካሄዱት እንሱው እራሳቸው ነፍሳቸው ለጊዜው ምድር ላይ ያሉት ይሆናሉ ... ፎቶውንም ይናገራል። ጠርዝ ላይ ኩዴታ ተካሂዶ አያውቅም። የ አዲስ አባባው ግር ግር ቁሮ ነው ...መለበጫ መስትሽ።

ለኦነጋውያኑ የድል ዕለት ብቻ ሳይሆን ለግባቸው አንድ ትልቅ የመገናኛ ድልድይ እርካብ ነው። እነሱ ባቀዱት ልክ አትርፈዋል።

ለካቴና ራት እንዲሆኑ ለተፈለጉት ለብ/ጄኒራል አሳምነውና ጽጌ እና ለጓዶቻቸው ደግሞ ጽናቱን ብርታቱን ይስጣቸው። ይህ ሁለት ዓላማ አለው። ህወሃትን ለማስደስትና ልቡ ትንሽ ቢራራ ተብሎ ነው። ተራ በተራ ግን ለአንሳ ሥጋ እዬሰጡ ወደ ማረጃው እንደሚወሰደው ሁሉም ይደርሰዋል የጊዜ ጉዳይ ነው። 

ሌላው ግን ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት ከተመረጡ ጀምሮ ሥራቸው አጀንዳቸው የአማራ ብሄርተኝነትን ማጠውልግ እና መቅበር ለሆነው አብይወለማ መንገድ ጥሩ ባይታሚን ነው።  የአማራን ቅስም ለመሰበር፤ ጃዋረዊው የጢቾ ባላባት አቶ ንጉሡ ጥላሁን እንዳሻቸው እንዲፏልሉ … ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል። 

መጪው የ አማራ ክልል ፕሬዚዳንት እሳቸው ናቸው። ለዚህ ነው ከኤርትራ መንግሥስት ጋር ተደራዳሪ ሆነው የተላኩት እሳቸው ነበሩ። ዶር ገዱ አንዳርጋቸው፤ ዶር አንባቸው መኮነን ተቀምጠው። ኦነጋውያን ሥልጣኑን ከሰጧቸው ቆዩ ... 

ወግ ደርሷቸው፤ ሳያገቡ ሳይዳሩና እና ሳይኳሉ ዘር ሳይተኩ በተንሳፋፊነት በማዕላዊ መንግሥት በቋሳ ሲታሹ ባጅተው፤ ፍዳቸውን ሲከፍሉ እንደባከኑ ከሁሉም እንዳይሆኑ የአንቦን ጉዞ በማደራጀት ሰብዕናቸው ላይ ዶፍ እንዲለቀቅ ሆኖ፤ እንዲሁ እንደ ቆሞስ ስመኛው በቀለ እና ቆሞስ ተስፋዬ ጌታቸው ላለፉት ለዶር አንባቸው መኮነንም ነፍስ ይምር! በአገር ውስጥም በውጭም ለሚኖሮ ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን ፈጣሪ ይስጥ። አሜን!

የዶር ገዱ አንዳርጋቸው አሸኜኘት ላይ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ሲገኙ ጃዋራዊው አቶ ንጉሡ ጥላሁን ግን አልተገኙም ነበር። በአማራዊ ጉባኤ እምብዛም ተገኝተው አያውቁም? ለምን ለሚለው የተመኙትን ወንበር ሲያገኙ የሚታይ ይሆናል። 

ሌላው ለሞገዶነት በቅንነት የተማገዱት እና ታቅዶ የተከወነውን ብሄራዊ መልክ ለመስጠት በነበረው ኦፕሬሽን ሰለባ ለሆኑት በሥም ብቻ የጦር ኃይሎች ጠ/ አዛዥ ለነበሩት ለስላላሰ ናቸው ተብለው ስለሚነገርላቸው ለጄ/ ሳህረ መኮነን ቤተሰብም መጽናናትን ፈጣሪ ይላክ። አሜን! ዜና ማሟቂያ ማጣፈጫ ሆኑ ... 

የአብይወለማ ጉዞ እነሱ ሁል ጊዜም በረጅሙ አቅደው ነው የሚከውኑት ለእኛ ግን በድንገቴው ሱናሜ መጥለቅለቅ ለምዶብናል እናም ይቀጥላል የድንገቴው ጥቁር ትወና በ ዓይነት ማነው ባለሳምንት እያልን። የሃምሌው ዝምታ የሰኔው ግርግር ዓመት ድገሙ ብሎናል። መራራም ቢሆን።

በዚህ ውስጥ ይህ ታቅዶ የተከወነ ጉዳይን ከልብ ሆኖ ከመጪው ዘመን ጥቁርነት ጋር በወጉ ሊታይ፤ ሊፈተሽ እና ሊበረበር ይገባዋል „ጦርነት እንገባለን የጠ/ሚር አብይ አህመድ ዛቻ „እንሟሟታለን“ የአቶ ለማ መገርሳ ትልም፤ የአብሪያቸው የጦማሪ አቶ ስዩም ተሾመ  የአማራ ትጥቅ ይፍታ ዝላይ በድርብ ለግብ የበቃበት ኦፕሬሽን ነበር ሰሞናቱ። የቆሞስ እንጂነር ስመኘው የሞት ዋዜማ ነጋሪም እኒሁ ጦማሪ ነበሩ ...

ጦማሪ ስዩም ተሾመ ከአንድ አፍታ ሚዲያ ጋር ያደረገው አነጋጋሪ ቃለ ምልልስ!!

| Ethiopia

Published on May 6, 2019

ለኦነጋውያን ድል ተነባብሮላቸዋል። የተከደነ የሐሤት ሰሞናት። የዲሲው ዘመቻ አህዱ ነበር። ለጊዜው ከሽፏል ግን አዘናግተው ይመለሱበታል። ወይ ደግሞ አውሮፓ ላይ ይቀጥላል መሰሉ አፈናም ግድያም፤ የምግብ ብክለትም። ሁሉም ተራውን በወረፋ ይጠብቅ። ከዚህ ጋር የጋዜጠኛ ደምስ በለጠ ህልፈትም በቅጡ ይቃኝ። እንዴት የውሽማ ሞት ሆኖ እንደቀረ ... 

በሌላ በኩል ሆን ተብሎ ያለፈው ሳምንት ቀጠሮ እንደራዘም ተስፋ ቆራጭነትን ሰንቆ የጥቁር ቀንን ዳመና ለብሶ ተስፋን ደቁሶበት፤ ጢስን ሰንቆ ደግሞ ባለደራስ ወደ ባዕቱ ይመለሳል። ነገ ቀኑም ለእሱ ክው ብሎ ደርቆ ይጠበቀዋል። ሌላ ትዕይንት ደግሞ ይጠብቅ … ወደ ዛሬ እንዲዛወር የተፈለገበትም ታቅዶ ሆን ተብሎ ነበር። ለዚህም የጢስ ፖለቲካ ላይ ጽፌው ነበር።

አላዛሯ ኢትዮጵያ እንሆ ቀውስ ታቅዶ የሚከወንባት ምድር ሆናለች፤ ቀውስ አደራጁም፤ የበለጠ ተቀባይነቱን ለመጨመር፤ ተቀባይነቱ የተናደ ሲመስለው፤ ወይንም ሌላ ተፎካካሪ ሲመጣ በዬጊዜው በሚያሰናዳው ግርግር "ኩዴታ" አቀናባሪውም፤ መሪውም፤ አስፈጻሚውም፤ ፈጻሚውም አዛዡም ናዛዡም እሱ በእሱ ነው ኦነጋውያኑ። የኦነግ ፖለቲካ አሳምሮ አመቻችቶ እዬሰለቀን ነው። ደቁሶናልም።
  
የአቶ ለማ መገርሳ ወደ መከላከያ ሚ/ር የተዛወሩበት የመጀመሪያው ሚሽን በድል ተጠናቋል አገር ውስጥ ። የመስከረሙን የብአዴን ጉባኤ እንዳሻው ዘውረው ሥልጣኑን ለጃዋራዊው አቶ ንጉሡ ለመስጠት ትልሙ እንኩት ብሎ ነበር፤ አሁን በሰጋር ፈርስ መጪ ነው እንደ 16ኛው መቶ ክ/ ዘመን … ወረራውን …

ዲሲ ላይ ነበር ቀዳሚው ሚሽን ከኢሳት ያፈነገጡን ለመክላት የፕ/ ሰክሪያታርያቱ እና የግንቦት 7 የወልዮሽ የዲሰ ጉዞ በጋዜጠኞች ላይ የነበረው የጥቃት ሂደት ተከታይ ነው የትናንቱ የአማራ ክልል የሰኔው ግርግር ብለን ልናዬው እንችላልን … ኩዴታ ሳይሆን የወርኃ ሰኔ የጢሳማው ግራዋማ ግርግር ነው … በመንግሥት ታቅዶ የተከወነ።

የሰው ልጅ ህሊናውን በተቀማጭነት ሳይሆን ነገሮችን በልክ በቁመናቸው እና በሁነታቸው መመርምር፤ ማገናዘብ ይገባዋል። ይህ ትዕይንት
የአማራ ብሄርተኝነትን ለመግደል የታለመ ነው። ይህም ማለት ኢትዮጵያዊነት ላይ የተነጣጠረ ጦሮ ነው። የዲሞግራፊ ፍልስፍና ኢላማው ይኸው ነው።
የሚወገደውን ማሰውገድ፤ የሚበወዘውን መበወዝ።
የአማራ ብሄርተኝነት ከሞተ የኦነግ መንፈስን ለሙሉ ድል አብቅቶ ኢትዮጵያ በቅኝ ትገዛላች …

አማራ  ጃዋራዊውን የአቶ ንጉሡ ጥላሁንን የመስተዳደር ፕሬዚዳንትነት የተቀበለ ዕለት እንደ ህዝብ ቀብሩ ይፈጸማል።

አቶ መላኩ ፈንታ ከሆኑ ደግሞ ትንሳኤው ይቀጥላል … አንዱ የመከራ ምዕራፍ ሌላ የመከራ ምዕራፍ እንዳይከፍት በብዙ ሁኔታ መጠንቀቅ ይገባል።
ለአፍታ ታቅዶ ስለመከወኑ መዘናጋት አይገባም። ፌክ ነው ኩዴታ የሚሉትም ከ እጃቸው የገቡትን እንዳሻቸው ለመሰልሰል ነው።

የወሎ የጠ/ሚሩ ጉዞንም በዚህ ውስጥ ማዬት ነው። ቆሞስ አንጂነር ስመኛው ሊሰዉ በዋዜማ ደልዳላዋ እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸውን ባለቤታቸው ወደ ጎንደር ልከው ነበር፤ „ልብ ያለው ሸብ“ እንደ ጎንደሮች።
 
የፈጣሪ ነገር ደግሞ እንመልከተው የቆሞስ እኒጂነር ስመኛው ህልፈት እና ከስሜን አሜሪካ መልስ የሀምሌው ዝማታ የአውሮፕላኑ የቡና ፖለቲካ፤ የመጋቢት አንዱ የባልደረስ ጉባኤና የቤተ መንግሥቱ ፉክክር እና የአውሮፕላን አደጋው፤ የወሎ ጉዞ እና የቤተ መንግሥት የሃዘን ሰሞናት፤ ከዛ መልስ የባህርዳሩ የሰኔ ግራዋማ ግርግር፤ የባልደረስ ንቅናቄ እና የዶር አንባቸው መኮነን ለመስዋዕት መቅረብ፤

 … ውዶቼ ከልብ ሆናችሁ ሂደቱን እና እዮራዊ ተደሞውን አመሳጥሩት። በዚህ ማህል ም/ጠ/ሚሩም፤ ውጭ ጉዳይ ሚ/ሩም አገር ውስጥ የሉም። ቀኑ የተመረጠው በዚህ መልክ ነው። የሚገርመው እስከዛሬ ድረስ ተሰውሮ የነበረው የም/ጠ/ሚሩ አቋም አሁን ላይ በሰጡት መግለጫ ፍንጭ ተግኝቷል። ዘመድ ከዘመዱ እንዲሉ ...

https://www.satenaw.com/amharic/archives/68584

የመፈንቅለ መንግስት ሙከራው የአማራን ህዝብና ክልል የማይመጥን አሳፋሪና አሳዛኝ ክስተት ነው:- አቶ ደመቀ መኮንን

አሁን እኔ ለብጹዕን ፓትርያርክ አባቶቻችንም እብዝቼ አፈራለሁኝ፤ ሊተኳቸው ይችላሉ ስለሚበሉት እጬጌ እነሱ ስላሰናዱ … የጥምቀት ቡራኬ እንዲሰጥ ያደረጉት በኦሮምኛ ሁሉ ነበር … መከራችን ብዙ ነው።

በዚህ መከራ ውስጥ በአብይወለማ በድንገቴ ሰበር እዬተሰባባርን መቀጠል ሳይሆን ተቋማዊ የሆነ እድምታ ያስፈልገናል፤ የአርምሞ ጊዜም። መከራው ግን ቀጣይ ነው። ተጋድሎው ከሲብልና ከወታደራዊ የደህንነት ባለሙያ መሪዎች ጋር ነው። መንግዱም ግርፍ አይደለም፤ መስዕውዕትነቱም ሽርክት አይደለም። 

አንድ ሚሊዮን ህዝብ ለከተማ ዴሞግራፊ ብለህ ለፖለቲካ ትርፍ ስታፈናቀል ያልከበደህ ለ አንድ ሁለት ነፍስማ ምን አለው? ሎቱ ስብኃት ለደም ጥመኞች፤ ለቀወስ ፋፍሪካ ከፋቾች ... 

Ethiopia: ሰበር መረጃ - / አምባቸው መሞታቸው ተረጋገጠ |
ብርጋዴር ጀነራል አሳምነው ጽጌ ታሰሩ | ተጨማሪ መረጃዎች | Dr Ambachew
Published on Jun 23, 2019
ቸር ወሬ ያሰማን አምላካችን አሜን!

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።