ልጥፎች

ከጁላይ 28, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ጭካኔ ሞገስ አይደለም።

  ጭካኔ ሞገስ አይደለም። ጭካኔ ክብር አይደለም። ጭካኔ የሚያስቀና አይደለም። ጭካኔ የአስተሳሰብ ድህነት ነው።  ጭካኔ ኋላቀርነትም ነው። ጭካኔ የአስተሳሰብ እድገት #መጫጫት ። በምንም መሥፈርት፤ በምንም ሁኔታ ከሰው ልጅ ህሊና #ርህርህና #እንዲመንን - #እንዲሰደድ መፍቀድ ሰማያዊው፤ እዮራዊው #ምርቃት እንዲነሳ መፍቀድ ነው።  እዮራዊው ምርቃት ሲነሳ #ባዶነት ይታጫል። ባዶነት ደግሞ ትውልድን አገርን #ሰብል #አልቦሽ ከማድረግ ውጪ ምንም ዓይነት ፋይዳ አይኖረውም።  ጭካኔ ሰው የተፈጠረበትን #ሚስጢር ፈቅዶ #ማፍሰስ ነው። እራስን #መቅደድ ። እራስን ሰብዕና ፈቅዶ እና ወዶ ማህበ #ዙ መቀዬርም ነው። እግዚአብሄር ይስጥልኝ። ኑሩልኝ ማህበረ ቅንነት። ሥርጉትሻ 28/07/024