ጭካኔ ሞገስ አይደለም።

 ጭካኔ ሞገስ አይደለም። ጭካኔ ክብር አይደለም። ጭካኔ የሚያስቀና አይደለም። ጭካኔ የአስተሳሰብ ድህነት ነው። 

ጭካኔ ኋላቀርነትም ነው። ጭካኔ የአስተሳሰብ እድገት #መጫጫት። በምንም መሥፈርት፤ በምንም ሁኔታ ከሰው ልጅ ህሊና #ርህርህና #እንዲመንን - #እንዲሰደድ መፍቀድ ሰማያዊው፤ እዮራዊው #ምርቃት እንዲነሳ መፍቀድ ነው። 

እዮራዊው ምርቃት ሲነሳ #ባዶነት ይታጫል። ባዶነት ደግሞ ትውልድን አገርን #ሰብል #አልቦሽ ከማድረግ ውጪ ምንም ዓይነት ፋይዳ አይኖረውም። 

ጭካኔ ሰው የተፈጠረበትን #ሚስጢር ፈቅዶ #ማፍሰስ ነው። እራስን #መቅደድ። እራስን ሰብዕና ፈቅዶ እና ወዶ ማህበ #ዙ መቀዬርም ነው። እግዚአብሄር ይስጥልኝ። ኑሩልኝ ማህበረ ቅንነት።


ሥርጉትሻ 28/07/024

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።