ሆድ ለባሰው #ማጭድ አታውሰው።" መቸኳኳል። #የመርገብገብ ፈተና።
ሆድ ለባሰው #ማጭድ አታውሰው።" መቸኳኳል። #የመርገብገብ ፈተና። ፈተናን #የማዳቀልና የማራባት ናፍቆተኝነት። "እንደ ኃጢያታችን አላደረግብንም፤ እንደ በደላችንም አልከፈለንም።" (መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፻፪ ቁጥር ፲) ምዕራፍ ፳። https://www.bbc.com/amharic/articles/cvlyd2w477l0o «የእነ ሌተናል ጄነራል ጻድቃን ምክር ቤት ከአሁን በኋላ "በተቋቋመበት አደረጃጀት" እንደማይቀጥል አስታወቀ» #ጠብታ ። "የቸኮለ አፍሶ ለቀመ።" "የእነ ቶሎ ተሎ ቤት ግድግዳው ሰንበሌጥ።" "ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል።" "የቆጡን አውርድ ብላ የብብቷን ጣለች።" (የደፂን ህወሃት በትክክል ይገልፃል) "የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል።" እነኝህ የህሊና ቀዳሚ የመሰናዶ #አስተውሎቶች ለኢትዮጵያ ፖለቲካ ማንነት ገላጭ ይመስሉኛል። ሁሉ ነገር ጥድፍድፍ፤ ሁሉም ነገር ችኩልኩል፤ ይልና አካባቢውን በወጀብ፤ በማዕበል፤ በጦሮ ንፋስ ይንጠዋል። ደጋፊ እና ተቃዋሚም እንቅልፍ አጥቶ አቅሙን በገፍ ይመግባል። ተስፋ አያልቅም እና። ስክነት - ማጣት፤ እርጋታ ጋር አለመገናኜት፤ ማስተዋልን አለማድመጥ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሁልጊዜ ተፈታኝ ያደርገዋል። በፈተናው ውስጥ ማገዶ ይኖራል። #ማገዶ ደግሞ የሰው ልጅ ነው። መኖር፤ ሰላም ፦ እንደ አቅሚቲ ያለችው ሥልጣኔም ሁሉ አብሮ ይሾቃል። አንድ ፔና ያልገዛ ግን ሰውን ያቅዳል፤ ያጠምዳል፤ አንጋች ያደርጋል፤ መኖር ይቀራል። #እፍታ ። የትግራይ የሰላም ኃይል እና ዘላቂነቱን በሚመለከት ያለኝን ስጋት ጥፌያለሁ ከዚህ ቀደም። ትናንት ባለ አደራ አስተዳደር መዋቀሩን ይፋ መረጃ ወጥቷ...