የተጋነነ ምስክርነት አላዳመጥኩም
#ምዕራፍ ፳። #ለመታዘዝ የፈቀዱ። መታዘዝን በገቢር ያስተማሩ። በቅድሚያ አቶ ሙሼ ሰሙን እንኳን ደስአለወት ልበላቸው። ሪኮመንዴሽናቸው ተሳክቶላቸዋል። መደመጥ ችለዋል። ዕድለኛም ናቸው። "በዕድሜ ጠና" ያሉ ብቻ ሳይሆን በተመክሮም "ጠና" ያሉ ይመስለኛል ፕሮፌሰር ብርኃኑ ነጋ። እንዲቀጥሉ ተደርጓል። በአካልም አይቻቸዋለሁኝ። እሳቸውን የሚተካ በዚህ ቦታ ለማግኜት ይከብዳል። ለራሳችን #ቅንነትን መግበን፤ በማስተዋል ብንመረምረው፤ ጉዳዩን የእኔ ብለንም ብንከታተለው የመንግሥት ሠራተኛ መሆን እና ከዚህ ልምድ እና ተመክሮ ውጭ ሆኖ መኖር በብዙ ይለያል። ከአንድ ዓለምን ማነቃነቅ ከሚችል ፖለቲከኛ፤ በንግግሩም ይሁን በፖለቲካ አደረጃጀት ተመክሮው ከላቀ ሰብዕና ይልቅ፤ መሬት ላይ አንድ ቀበሌ ማህበር ሊቀመንበር ሆኖ የሚመራ የህዝብን የውስጥ ውስጥነት የማድመጥ ዕድል አለው። ይበልጣልም ሞገድ ላይ ጠንክሮ ከሚታዬው ይልቅ። ይህን ዕድል ሳያፈሱ ፕሮፌሰር ብርኃኑ ነጋ ተጠቅመውበታል። የመንግሥት ቋሚ ሠራተኛነት #አንድ ማንነት ነው። አዲስ ማንነት። ለመሪነትም ቁልፍ መስፈርት ሊሆን ይገባል ባይ ነኝ - እኔው። በዚህ ውስጥ ለመገኜት መወሰን ከኢትዮጵያ የፖለቲካ ባህል አንፃር ወጀቡ፤ #ወበቁ ማት ነው። ይህን ተቋቁሞ ኢትዮጵያን ለማገልገል ባገኜው ስንጥር ዕድል መወሰን፤ በዛ ውስጥም ለመዝለቅ መሆን ፈተና ነበር። ይህን ችለዋል ፕሮፌሰሩ። በፖለቲካ አደራጅነት እና መሪነት ከአየሁት ሰብዕና ይልቅ ዕድሉን አግኝተው፤ በዕድሉም ተጠቅመው ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ያደረጉት #የመሰጠት ብቃት እና ጥረት የሚሠፈር፤ የሚለካ ተግባር ታይቶበታል። እኔ በፕሮፌሰር ብርኃኑ ነጋ የእሽታ አብ...