ኢንጂኔር ወ/ ሮ አይሻ መሃመድ - የወ/ሮ ዓለምጸሐይ ጳውሎስን ኃላፊነት ይረከቡ ይሆን?

 

#ኢንጂኔር ወ/ ሮ አይሻ መሃመድ - የወ/ሮ ዓለምጸሐይ ጳውሎስን ኃላፊነት ይረከቡ ይሆን?
 
"አቤቱ የቤትህ ቅናት በላኝ።"
 
 
ሹምሽሩን አዳመጥኩኝ። #እመለስበታለሁኝ።
በካቢኔ ውስጥ ኢንጂነሯ የሉም። ከምከታተላቸው
ሴት የፖለቲካ ሊቃናት አንዷ ናቸው። 
 
ከነበሩበት ደረጃ ጋር የሚመጥን ቦታ ሳስብ፤
የኢትዮጵያ የፖለቲካ መዕከል የጠቅላዩ ጽህፈት
ቤት ስለሆነ የወሮ አለምጸሐይ ጳውሎስን ቦታ አሰብኩት።
ለምን?
 
1) ከሙያቸው፤ ከልምዳቸው አንፃር፤
2) የጠቅላይ ሚር አብይ #ውስጠት ተመስጥሮ
ያለ መሻት ታክሎ ይህ ቦታ ለሳቸው ይሆን ይሆን አልኩኝ?
ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ የማይደብቁት፤ በአገኙት
አጋጣሚ የሚናገሯቸው አመክንዮወች አሉ። በአዲሱ
የሥራ ዘመናቸው መግቢያ መቅድመ ጊዜ ባይደጋግሙት ይሻል ነበር።
የሆነ ሆኖ ሌላም የተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የነበሩትም
ወሮ ሎሚ በዶም አልተመደቡም። 
 
በጓዳ ምነው ሥርጉትሻ በብልጽግና ስብሰባ ታተኩሪያለሽ
የሚሉ ወዳጆች አሉኝ። ይህ እኛን አይመለከተንም የሚሉ የቤታችን
ቤተሰቦች አሉ። 
 
ህዝቤ የእኔ፤ ህዝባችን የሁላችን #ኑሮው የሚመራው
በገኃዱ ዓለም #በኢሊት ነው። 
 
ስለዚህ ይህንን አስኳል አላየሁምም፤ አልሰማህም ልለው
አልፈቅድም። የአገሬ ጉዳይ ቀዳሚው #አጀንዳዬ ነው።
እከታተላለሁ፤ አደምጣለሁ። ዕይታዬንም አጋራለሁኝ።
አይመለከተነም የሚሉትም እኮ ሌላ ሥራ የላቸውም፤
ይህንኑ ሂደቴ ያሳሱታል፤ ያባዝቱታል፤ ዛሬ ሁሉንም
እዩ አጀንዳው የብልፄ ሹም ሽር፤ ሽግሽግ ይሆናል።
በአወንታዊም በአሉታዊም።
 
የዓለም መተዳደሪያ ስንቅ ፖለቲካ ነው። ሌላ የለውም።
የዓለም መተንፈሻ ቧንቧ ፖለቲካ ነው። ከዚህ ውጭ ሆኖ
መኖር አይቻለም። እኔ ደግሞ #በጋሜዬ የጀመርኩት፤
ብዙ ኮርሶችን የወሰድኩበት በመደበኛም የሠራሁበት
ስለሆነ ውስጤ ነው።
 
በዕድሜ ውስጤ፤ በሂደት ውስጥ ስሜቴ እየረጋ ሲሄድ
ከወጣትነት ዘመን ዕይታ፤ ፍጥነት፤ አስቦ የመነሳት ጉዳይ ልዩነት
ሊኖር ይችል ካልሆነ፤ በስተቀር አገር ስል ኢትዮጵያ
ስል ስለእሷ ሁለመና መከታተል #መብትወግዴታዬ ነው።
 
ከመደበኛ የፖለቲካ ሠራተኝነት ስወጣ ሚዲያ ላይ ነው
የሠራሁት፤ የሁለቱ ተመክሮ ወደ ጸሐፊነት፤ ገጣሚነት
አሸጋገረኝ። ፖለቲካ #ውስጥን ያደራጃል። ተመክሮው
ጥልቅ ነው። አድማጭ ካገኜ። #የተሰጠኝ ይህ ነው። 
 
#ጥሪዬም ይህ ነው። ቤተሰቦቼ ከጥዋቱ ጀምሮ
አይፈቅዱትም እኔ ደግሞ የበኽር ልጄ ነው። 
 
ግን ውዶቹ ክብሮቹ እንዴት አድራችሁ አረፈዳችሁ።
 
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
08/10/2026.
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
See less

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።