የተጋነነ ምስክርነት አላዳመጥኩም
#ምዕራፍ ፳።
#ለመታዘዝ የፈቀዱ። መታዘዝን በገቢር ያስተማሩ።
በቅድሚያ አቶ ሙሼ ሰሙን እንኳን ደስአለወት ልበላቸው። ሪኮመንዴሽናቸው ተሳክቶላቸዋል። መደመጥ ችለዋል። ዕድለኛም ናቸው።
"በዕድሜ ጠና" ያሉ ብቻ ሳይሆን በተመክሮም "ጠና" ያሉ ይመስለኛል ፕሮፌሰር ብርኃኑ ነጋ። እንዲቀጥሉ ተደርጓል። በአካልም አይቻቸዋለሁኝ። እሳቸውን የሚተካ በዚህ ቦታ ለማግኜት ይከብዳል። ለራሳችን #ቅንነትን መግበን፤ በማስተዋል ብንመረምረው፤ ጉዳዩን የእኔ ብለንም ብንከታተለው የመንግሥት ሠራተኛ መሆን እና ከዚህ ልምድ እና ተመክሮ ውጭ ሆኖ መኖር በብዙ ይለያል።
ከአንድ ዓለምን ማነቃነቅ ከሚችል ፖለቲከኛ፤ በንግግሩም ይሁን በፖለቲካ አደረጃጀት ተመክሮው ከላቀ ሰብዕና ይልቅ፤ መሬት ላይ አንድ ቀበሌ ማህበር ሊቀመንበር ሆኖ የሚመራ የህዝብን የውስጥ ውስጥነት የማድመጥ ዕድል አለው። ይበልጣልም ሞገድ ላይ ጠንክሮ ከሚታዬው ይልቅ።
ይህን ዕድል ሳያፈሱ ፕሮፌሰር ብርኃኑ ነጋ ተጠቅመውበታል። የመንግሥት ቋሚ ሠራተኛነት #አንድ ማንነት ነው። አዲስ ማንነት። ለመሪነትም ቁልፍ መስፈርት ሊሆን ይገባል ባይ ነኝ - እኔው። በዚህ ውስጥ ለመገኜት መወሰን ከኢትዮጵያ የፖለቲካ ባህል አንፃር ወጀቡ፤ #ወበቁ ማት ነው። ይህን ተቋቁሞ ኢትዮጵያን ለማገልገል ባገኜው ስንጥር ዕድል መወሰን፤ በዛ ውስጥም ለመዝለቅ መሆን ፈተና ነበር። ይህን ችለዋል ፕሮፌሰሩ።
በፖለቲካ አደራጅነት እና መሪነት ከአየሁት ሰብዕና ይልቅ ዕድሉን አግኝተው፤ በዕድሉም ተጠቅመው ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ያደረጉት #የመሰጠት ብቃት እና ጥረት የሚሠፈር፤ የሚለካ ተግባር ታይቶበታል። እኔ በፕሮፌሰር ብርኃኑ ነጋ የእሽታ አብነት፤ ሁሉ እያላቸው ለመታዘዝ፤ በሥርም ሆነው ለመማር የፈቀዱበት መስመር ካሪክለም ሊሆን ይገባል ባይ ነኝ።
የፖለቲካ ድርጅቶች የሚታገሉት ለሞድ ሳይሆን ለፖለቲካ ሥልጣን እናም ህዝብንም ለማገልገል ነው። ይህን ዕውን አድርገዋል። ሪሰርች ሊሠራበት ይገባል። ዝቅታን መፍቀድ። እልኽኝነትን አሸንፎ ኢትዮጵያን ለማገልገል እሺታ ለእኔ ልዩ ነው።
በፖለቲካ ህይወት ውስጥ ተከታታይነትን ለማምጣት ነባሩን ከአዲሱ ወጣት ዘመን ጋር አዋህዶ መሥራት ግዴታ ነው። ይሄ በወጣት ብቻ የሚባለው ነገር አክሳሪ ነው። ታላላቅ ፖለቲከኞችን አቅልሎ ማዬት የተገባ አይደለም። ህይወታቸው ዩንቨርስቲ ነው። ወጣቱ ይህን ሚስ ሊያደርግ አይገባም። አፍለኛ ፍላጎቱንም ረብ ሊያደርገው፤ ሊገራውም ይገባል።
የዕድሜ ሂደቱ ልምድም፤ ተመክሮም #ክህሎት አመንጪ ነው። ይህ ደግሞ በዕድሜ ብቻ የሚገኝ ነው። አሁን ጠቅላይ ሚ/ር አብይ አህመድ አሊ ከመጡ በኋላ ወደ ፖለቲካ የመጡ ሰወች አብዛህኞቹ ስክነት ያንሳቸዋል፤ ብስጭትም ይቀናቸዋል። ለምን? አድማጭነት ከተመክሮ ክህሎት ስለሚቀዳ። ከእነሱ ጋር መግባባትም በፍጹም አይቻልም። "አዲስ ወጠ ሰሪ ድንብላል አቅራቢ ይሉታል" ባለቅኔ ጎንደሮች ይህን መሰል ገጠመኝ ሲናኝ። ብዙ የፖለቲካ ትርምስ እና የአመክንዮ ስክነት ጅዋጅዊቱ በዚህ ምክንያት ነው።
በኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስተር ያልታዩ፤ ያልታሰቡ፤ ያልታቀዱ አዳዲስ የፈጠራ ጅምሮች እና ስኬቶችን አስገኝተዋል ፕሮፌሰር ብርኃኑ ነጋ። በአንድ መድረክ አግኝቻቸው ሳለ "ክቡር" ብያቸው "ክቡር" የሚለው ይነሳልኝ ስላሉ ነው። አይፈልጉትም። ከ50 ዓመት በላይ የኖረን ችግር እንደ ጉም አትንነው ተብለው ሊጠየቁ አይችሉም። ፕሮፌሰሩ ሊለኩ - ሊመዘኑ - የሚገባቸው ኃላፊነቱን ከተረከቡ ጀምሮ ያለውን በሥራቸው የጊዜ ማዕቀፍ ብቻ ሊሆን ይገባል። በሌላ በኩል የሳቸው ፓርቲ ኢዜማ አይደለም አውራ ፓርቲ።
እኔ ንግግራቸውንም ይሁን የተግባር መስካቸውን እከታተላለሁኝ። በዘርፋ ሙያተኛም አይደለሁም። ልምድም የለኝም። እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ግን እከታተላለሁኝ። ቢቀጥሉ የሚል የጸና አቋም ነበረኝ። ተሳክቷል። ኢትዮጵያ ነው የምትጠቀመው። የታመቀ አቅም፤ ህብራዊ - ልምድ፤ ዘመን ዘለቅ - ተመክሮ፤ የዕውቀት ኃይል ዕድል ሲያገኝ ምን እንደሚመስል እኔ አስተውያለሁኝ። በውነቱ ብነግራችሁ በዚህ ልክ የተጠና፤ የተደራጄ አዳዲስ ጎዳናወችን ፈጥረው አያለሁ ብዬ አላሰብኩትም ነበር።
#የሹመቱ የጠቅላዩ የንግግር ዘይቤ።
1) የተጋነነ ምስክርነት አላዳመጥኩም ከጠቅላይ ሚኒስተሩ። ይህ መልካም ነገር ነው።
2) ለተነሱ ሃሳቦች መልስ ሰጥተዋል ጠቅላይ ሚኒስተሩ። ባይበሳጩ ጥሩ ነበር። ዕውነት ካለ መስካሪ አይጠፋምና። ዕውነት ቦታውን ለቆ እንደማያውቅ ሁሉ።
3) የበታች አካሎቻቸውን የሚከታተሉበትን መንገድ ይፋ አድርገዋል - ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ። ለቀጣዮቹ አለርም ነው። ከስለላ ጋር የተያያዘ ሰብዕና በየትኛውም የሥራ መስክ ከኖረ ይህ አይቀሬ ነው። በግል ኑሮም ጓደኝነታቸው ይህን የመሰጠረ ነው። ሳያዩ ያያሉ። በስለላ ሙያ ያለ ይሁን የሠራ ኤክስፐርት የራሱንም ኑሮ ይሰልላል ሙያው አይደለም የሌላውን። ጠቅላይ ሚ/ር ይሁን ም/ጠ/ሚ ሁለቱም የደህንነት ሰብዕና ስላላቸው ለተሿሚወች ይከብዳል። እሳቸውም ደጋግመው ተናግረውታል። ከባድ ኃላፊነት ነው "ከመደብ" አምጥተን ይህን ኃላፊነት ስንሰጥ ብለዋል። ጠቅላዩም ይሁን ምክትላቸው እርስበእርሳቸው መሰለል አይቀሬ ነው። ሙያው ተጠራጣሪ፤ ንቁ፤ ቆቅ ስለሚያደርግ።
4) ሁለቱም ጠቅላይ ሚኒስተሩም ይሁኑ ምክትላቸው የዘመኑን IT ሥልጣኔም አላቸው። ይህ ደግሞ ለክትትል የሚረዳ ሌላው ገጠመኝ ነው። ይህ የዕውቀት ዘርፍ የዓለምን ሆድዕቃ እየመራ ያለ ነውና። በዛ ላይ የሚሊተሪነት ጉዳይም አለ።
5) አንድ ጠይም ዕንቁ የፓርላማ አባል ያቀረቡትን ሃሳብ ተንተርሶ የክትትላቸውን መንፈስ የገለጠ ጠንካራ ንግግር አድርገዋል። በብዙ ሊመነዘር፤ በብዙ ሊዘረዘር የሚችል። ቃል- በቃል ቢተረጎም ብዙ ዲያሎጎችን ሊያስተናግድ ይችላል። ኃላፊነቱን የተረከቡት ጽፈው ቢያጠኑት ጥሩ ነው። እንደ ዋዛ ባያዩት።
6) እንደ ስለት ልጅ የሚዩትን፤ የትውልድ አድርገው የደከሙበትን፤ ውስጤ ለሚሏቸው የሚሾሙበትን የቀድሞው የሳይንስ እና የቴክኖሎጂ ሚ/ር፤ የአሁኑን የኢኖቬሽን ሚ/ር ለወ/ት ፍሬህይወት ታምሩ ሰጥተዋል። ተቋሙ ሴት ሚ/ር ሲመደብበት የመጀመሪያው ነው። ለጠቅላዩ የመሻት አቅጣጫ የቴሌኮም ካፒቴን ሳሉ የልባቸውን ክብርቷ ባያደርሱ ይህን ተቋም አይሰጡም ነበር።
7) ከአፋር የተቃዋሚ ፓርቲ #አቅመኛ ሰብዕና ወደ ካቤኔ ገብተዋል። በብዙ ስብሰባወች የምከታተላቸው ናቸው።
ስምንት) ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ራሳቸውን ብቻ ነው የሚያደምጡት። የራሳቸውን መሻት ነው የፈጸሙት። አሁን ፍትህ ሚኒስተር ላይ ብይናቸው ይገርማል ለእኛ። ለሳቸው ግን ዶር ገዲዮን ጢሞቲወስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስተር እና ፍትህ ሚኒስተር ናቸው። ሌላ ሰው ቢመደብ አይቻልም። ስለዚህ የትዳር አገራቸው በአደራ ጠባቂነት ተሹመውበታል።
9) የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ሹመት ሲብራራ አቶ አዲሱ አረጋ የት ነበሩ???? ለሽ ብለው ነበር። ዝለውም ነው የገቡት። ከቲም ለማ ካቢኔ ውስጥ የቀሩት እሳቸው ብቻ ናቸው።
#ሴት ሊቃናት በተመለከተ "9 ተመጣጣኝ አይደለም" በዚህ ጠቅላይ ሚር አብይ አይታሙም። ባይሆን ……
1) …… የሚል አንዲት ክብርት የፓርላማ አባል አቅርበዋል። በበፊቱም ፓርላም የነበሩ ስለመሆናቸው ገልጸዋል። ሴት ሊቃናትን ወደፊት በማምጣት እረገድ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ስስታም አይደሉም። ሊታሙም አይገባም ባይ ነኝ።
በዘመነ ህወሃት የእኔን ብዕር እምትታውቁ ሁሉ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ባህል የገበርዲን እና የከረባት ስለመሆኑ እንደ እኔ የሚሞግት አልነበረም። ሙግቴን አድምጠው ህወሃትን ሲመዝኑ የነበሩ የዓለም የፖለቲካ ሊቃናት ነበሩ። በአጋጣሚ ዶ/ር አብይ አህመድ የኢህአዲግ አካልነታቸው ይህን ነፍስ ያለው መሻት ከእኛ ሳይሆን፤ ካላሰቡት አካል ለኢህአዴግ የወቅቱ ሥ/አ ሲነገር አደመጡ። ሰነቁትም። ዕድል ቀናቸው እና ጠቅላይ ሚ/ ር ሆኑ። ካቢኒያቸውን 50% ሴት አደረጉ። ዓለም ጉድ ነው ያለው። ያን ጊዜ የራዲዮ ሎራ ቲም ገርሟቸው በዜናው ጠይቀውኝ #አወንታዊ የሆነ ዕይታዬን አጋርቻለሁኝ።
ድምጽ አልባወቹ የኢትዮጵያ እናቶች ሞቶዬ ነበር። የኢትዮጵያ እናቶች ዕንባ መቆም ያልቻለው፤ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውክልና ሴት ሊቃናት ስለተገለሉ ነው የሚል ዕምነት ነበረኝ። ሴቶች 50%// 70%// ቢሆኑም ጥያቄው ዕንባው ቆሟል ወይ ነው?
ሴት የኢትዮጵያ ሊቃናት ዕድሉን አግኝተዋል። እና በዕድላቸው ውስጥ ዕንባማ እህቶቻቸውን በእቅፋቸው ውስጥ አድርገው አጽናንተዋል ወይ? ይህን ሎጅክ ዕውን ያደረገ ገጠመኝ አላየሁም። ደብረብርሃን ቅርብ ነው። አንድ ሰንበት ብቅ ብለው ተፈናቃይ እህቶቻቸውን አይተዋል ወይ? ጦርነቱ እና ጦሱን ሲያስቡስ ምን ይሰማቸዋል?
እና ክብርት ሆይ! 9 አያንስም ----- ከሠሩበት። ሌላው ሴት ስለተሆነ ብቻ ሳይሆን፤ ለቦታው መጥኖ መገኜት፤ ዲስፕሊኑ መሟላት አለበት። የብልፄው ወጣት አሉ በጣም ይገርሙኛል። አክቲቢስት ናቸው። ግን በምክትል ሚ/ር ደረጃ የብልፄው ዋና ቢሮ ቤተኛ ናናቸው። ቱግ ቱግ ነው የሚሉት። የሚዲያም የቦርድ አባል ናቸው። ወጣትነታቸው አገር --- እያመሰ ነው። አተንፍሱ ባይም ናቸው። ቢገሩ ጥሩ ነው። ፓርቲያቸው እንዲሰክኑ ቢረዳቸው እንላለን። ወጣት ሆኖ ፖለቲካ ውስጥ ከተገባ የዕድሜ ጫና ጋር መተላለፍ ግድ ይላል። ከሁሉ ጋር ቲካ ቲካ ሲሉ ነው የማስተውላቸው።
2) በየመምሪያው፤ በኮሚሽኖች፤ በአንባሳደርነት፤ አዳዲስ በሚጀመሩ ፕሮጀክቶች በበላይነት፤ በምክትል ሚ/ር ደረጃ ብዙ የሴት ሊቃናት አሉ። የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ እኮ ሴት ናቸው። አዲስ አበባ ግሎባል ናት እኮ።
/// ቦታው አለ።
/// ሹሙቱ አለ ተሰጥቷልም።
///#ዕንባውም አለ ተጠናክሮ ቀጥሏልም። የጠበቅኩትን፤ የሞገትኩበትን አላገኜሁም። እናትነት ከኃላፊነቶች ሁሉ የላቀ የድርጊት እመቤትነት ነበር።
3) በሴቶች ውክልና ላይ ዶር አብይ አህመድ ሴት ካመጡ #የእስልምና ዕምነት ተከታይ ከሆነ ኩፍታ መኖር አለበት። ኩፍታ የማይለብሱ የእስልምና ሴት ሊቃናትስ? ይህን የሚያደርጉበት መንገድ ይገባኛል። በዚህ የሚሠራ የፖለቲካ ቁመና አለ። ጉዞም ሲያቅዱ በዚህ መስፈርት የተናኜ ነው። ጠቅላይ ሚር አብይ ፓን አፍሪካኒስት ወይንስ-------- ? የቤት ሥራው ለእናንተ ነው። "ሁሉን ቢናገሩት ሆዶ ባዶ ይቀራል።" እኔ አይደለሁም። የጎንደሮች ብሂል ነው።
ሌላው ከአማራ ማህበረሰብ ሴት የፖለቲካ ሊቃናትን ወደ ካቢኔ መጥተው ሊሆን ይችላል በአሁኑ ምደባ? #ተብዕት የፖለቲካ ሊቃናትስ? ለምን - ስለምን #ተፈሩ? ተራገፋ ወይንስ ተገረፋ???? ---- እዚህ ላይ የወሰዱት እርምጃን መርምሩት፤ አቃላችሁ፤ አሳንሳችሁ አትዮዋቸው ዶር አብይ አህመድን እምለው ለዚህ ነው። ብልጫውን እዩት "ሙያ በልብ" ናቸው።
ብዙውን ነገር ቀላል በምትመስል ኩነት ሸብለል አድርገው ያቀርቧታል። ግን በውስጡ ጥልቅ የሆኑ የአመክንዮ ክምችቶች አሉ። ተፎካካሪወቻቸው፤ አጥብቀው የሚሞግቷቸው ብዙ፤ በጣም ብዙ ጉዳዮችን እንደምን አያይዘው እና ሲፈልጉም ሊንዱት እንደሚችሉ አድርገው እንደሚያዋቅሩት ከልብ አድምጡት። በሳቸው ልክ ለመሆን አንጋፋው ህወሃትም አልቻላቸውም። ህወሃት እሱ በእኩልነት ለድርድር እንዲመጣ ነበር ሲያምስ የባጀው፤ እሱ ተረስቶ ጉዳዩ የኢትዮ ኤርትራ ይሆን ዘንድ ያደረጉትን ጉዞ በማስተዋል መርምሩት።
4) ዶር አብይ አህመድ አሊ ደጋግመው በጉልበታም ቃል የተናገሩት አለ። አንዱን ውስጤ፤ ነፍሴ፤ ፍቅሬ ትንፋሼ ጠረኔ --- ሲባል በዚህ ውስጥ ግለት፤ ግለቱ - መከፋትን፤ መከፋቱ - ጤናማ ግንኙነትን አያጎሳቁልም ወይ?? ከተበተነ በኋላስ እንደምን መሰብሰብ ይቻላል???
5) ደጋግመው የገለጹት ጥልቅ የሆነ የማጣራት ተግባር እንደ ተከናወነ፤ ጥልቅ የሆነ ጥናት እና ክትትል እንደተደረገ ነግረውናል። እኔም ታዝቤያለሁኝ። ከትግራይ ሁለት የካቢኔ አባላት ሊሾሙ ሲታሰብ እስላም እና ክርስቲያን ብለውናል፤ ለአፈ ጉባኤ እንዲህ ለማድረግ ለምን አልደፈሩም? እንዳይቀር የሚሳሱለት የዕምነት ዓይነት አለ፤ አደብዝዘው የሚዩትም አለ - በግለት። ለሥልጣን ዘመን አሻራቸው በፍጹም አይጠቅምም። ስለ አባት ደጋግመው አንስተዋል። አባት አንዱን የክት ሌላውን የእዳሪ፤ አንዱን ልጅ ሌላውን እንጀራ ልጅ አያደርግም። አባት ለልጆቹ እኩል የሆነ የችሎት አደባባይ ነው። ሰበር የማይጠየቅበት። እኛ እርስወ ወደፊት ከመምጣተወት በፊት ምነወትም መለኪያችን አልነበረም።
ሥራው ቀላል ነው ብዬ አይደለም። የ130 ሚሊዮን ህዝብ ፍላጎት፤ የዓለም ተጨባጭ ሁኔታ፤ የአገራችንም ሁኔታ እራሱ የሚከብዱ ነገሮች አሉበት። ህወሃት እኮ የዘመን መከራ ነው። ያልፈበረከው የቀውስ ትዕይንት አልነበረም። ሌላው በየዘመኑ የባጁ ችግሮች እንደ ጉም ይተናሉ ከሚል አይደለም እኔ ሃሳቦቼን እማቀርበው። በኢትዮጵያ ፖለቲካ ወጣትነቴን ገብሬበታለሁኝ። ደክሜበታለሁኝ።
"#ድሮ ድሮ ድሮ" --------------"ዛሬ ዛሬ ዛሬ ዛሬ" ጥሩ አይደለም። ያን እያነፃጸሩ የቂም በቆልት አይበጅም። ውስጥንም ይጎዳል። ኢትዮጵያ በአንድ ጀንበር የተበጀች አገር አይደለችም።
ዶክተር አብይን ከዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ፤ ከዝቅተኛ ቤተሰብ፤ ከዝቅተኛ የኃላፊነት ደረጃ ሌ/ኮነሬል ያደረሰው ድሮው እራሱ ድሮ ነው። ፊደል ቀርጹ ሀሁ አስቀጥሎ የዓለሙ ሎሬት ተሸላሚ ያደረገው የድሮው ዊዝደም ነው። ለዓለም የሰላም አባት ያበቃው የድሮው ኢትዮጵያዊነት ነው። ይህ ያሻን በአሻ ሰዓት የሚያስፈጽም ድሮው በሠራው መንግሥታዊ ሥርዓት ነው። ያው የድሮው ሥርዓቱ ተዘርግቶ በዛ ሂደት ታልፎ አብዛህኞቻችን እኩል ፊት ለፊት ወጥተን #መስክረን ይሁን ብለን ይለፍ ሰጥተን ነው። ቢረሳ ቢረሳ በዛች ቀውጢ ቀን ሙሉ 45 ድምጹን ሸልሞ ለዚህ ያበቃወት ብአዴን እንዴት ይረሳ?
ሥልጣኑ አይደለም ኦሮማራ ባይሳካ ኖሮ በስድስት የተሳለ ሰይፍ ከዓይን ጋር ያለው የአቶ ጌታቸው አሰፋ እርምጃስ አስባችሁት ታውቃላችሁን። ህይወታችሁ ያተረፈው የቅንነት ማዕከል የሆነው ማህበረሰብ በፈቀደው፤ በሰጠው ይሁንታ ነው። ካቴናም አይፈቀድም ነበር ልቅምቅም አድርጎ ህወሃት ድብዛችሁን ያጠፋው ነበር። በስንት ኤሉሄ ነፍሳችሁ ተርፎ ኢትዮጵያን ያህል አገር ስትረከቡ የዲፕሎማሲያዊ ማህበረሰብ ይሁንታ ከወንዝ ዳር የታፈሰ አሽዋ አልነበረም። ብዙ ተደክሞበታል። ብዙም ተለፍቶበታል። በጦርነቱ ጊዜም ህወሃት ድጋሚ ሲታጭም።
#ስብጥር ጠብቀናል። (ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ።)
1) ጠቅላይ ሚ/ር፤ ም/ጠ/ሚ የፓርላማ የፓርላማ አፈጉባኤ፤ የፌድሬሽን አፈጉባኤ ቁልፍ ቦታወች ናቸው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ #ተዋህዶስ። መልሱ "መ" መልስ የለም ነው። {}። የውስጤን ብነግረወት የሚያስፈራ ነገር አለው። "ጥምዶ" መጣሁ ሲል እሱ ሳይሆን የሚያስፈራው የተዋህዶ ዕንባ ነው ብየወታለሁኝ። የተዋህዶ ግለት፤ ተጠቂነት፤ ክብር ማጣት ዝምታ አይበጅም። ኢትዮጵያን ጸሎት ነው የሠራት። ሱባኤ ነው የቀመራት። ፈርሃ እግዚአብሄር፤ ፈርኃ አላህ ነው ያበጃጃት።
2) የካቢኔ አባላት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ውክልና ስንት ፐርሰንት ነው? 1%// 2// 3// -%/። ኦርቶዶክስ የሥም ኦርቶዶክስ ሳይሆን ትውፊቷ ህይወታቸው ይመራበት ዘንድ የፈቀዱት።
3) የብሄረሰብ ተዋፆም እንዲሁ ማየት እንችላለን። በጣም የተገፋ፤ የተገለለ ማህረሰብ አይታይም ወይ? ታስቦበት፤ ታቅዶ ስለመከወኑ አዳምጫለሁኝ። ኮታቸው እንዳይቀር ጥንቃቄ የተደረገላቸው እንዳሉ አስተውያለሁኝ፤ ለምሳሌ ደቡብ። ሌላው ደግሞ ያለውንም አጥቶ ተነቅሎ ወይንም ተንሳፋፋ ቁራሽ ጠባቂ ………
4) የትግራይ ጉዳይ ታሳቢ መደረጉ ለእኔ አበረታች ጅማሮ ነው። የጦርነት ጣጣው ተጠናቆ በፓርላማም፤ በፌድሬሽን ምክር ቤትም ውክልናቸው ባሊህ ይባል ዘንድ እመኛለሁኝ። ህወሃት ሁሉንም ነው ያሳጣት እቴጌ ትግራይ የራሷ የሆነ ጠቃሚ ንጥረ ነገሯን ኢትዮጵያ እንድታጣ አልፈልግም። ምን አልባት ሥምረት ፓርቲ ቢሳካለት ተመጣጣኝ ዕድል ሊኖር ይችላል።
5) የአርሲ የፖለቲካ ሊቃናት ሰፊ ዕድል አግኝተዋል። አርሲ ላይ ያለው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዕንባስ - በዶር አብይ የግምገማ ሂደት እንዴት ነበር?? #ጭካኔው የፖለቲካ ነው። እኔ አርሲ ኑሬያለሁኝ። ከደግነት - ከርህርህና - ከለጋስነት - ውጪ - ከሰው ወዲጅነት ውጬ ያዬሁት መልከ ጥፋ ምግባር አልነበረም። ገጠሩንም አውቀዋለሁኝ። ይናፍቀኛል - ቀዩ።
ትናንት ሰዋዊ ተፈጥሯዊ የሆነ ባዕት - ዛሬስ? የምንሰማውን ርህርህና የነጠፈበት፤ ሊቆም ያልቻለ ጭካኔን በበላይነት ሲመሩ፤ ሲያስተዳድሩ የነበሩ ሰብዕናወች በፌድሬሽን ደረጃ ሲመጡ ከዛሬ --- ከነገ ጋር ምን እና ምን እንዲሆኑ ታስቦ ይሆን። በውነት መልካም ባደረግን መስቃው ቁስል ሲያደርገን ነው የባጀው። በቀሉም የሚቻል አልሆነም። ይህን አስታግሶ ሰውኛ ዘመን ለማምጣት እንዴት ይቻል ይሆን???
የፆታ ስብጥር ቅሬታ የለኝም። እስኪ መጀመሪያ ይሥሩበት የተሰጠውን *ዕድል። ዶክተር አብይ አህመድ በሚገኙበት ቦታ ሁሉ ሴት ሊቃናት አብረው ይገኛሉ። ዕውቅና ይሰጣቸዋል። "በአፍሪካ የለም" ብለዋል። ዕውነት ነው። አቅም ያጡት የኢትዮጵያ ሴት ፖለቲካ ሊቃናት እንጂ ቦታውማ በዝቀሽ ተሰጥቷል። ወቀሳም ነቀሳም ሊቀርብበት የሚገባ አይደለም።
በሌላ በኩል ሴቶችን በማሳተፍ እረገድ በኢትዮጵያ የተፎካካሪ፤ የተቃዋሚ፤ የተጠማኝ፤ የተግባቢ የፖለቲካ ድርጅቶችም እንዲህ ያለ ሁነት አልነበረም። የነጠፈ ልሙጥ ነበር። ነፍሳቸውን ይማረው እና የፕ/ በየነ ጴጥሮስ፤ የፕ/ ዶር መራራ ጉዲና ፓርቲ ምን ነበረው? የሴት ሊቃናት ሆነ የወጣት ፖለቲካ ሊቃናት ጉዳይ የተገለለ አመክንዮ ነበር።
ሌላው በአሁኑ አደረጃጀት የተከፋ የአማራ ወገኖቼን አይቻለሁኝ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተርነት ከዘመነ #ህውሃቲዝምወአብይዝም ቀጥሏል። ነገረ አማራ ውጭ ጉዳይም ነበር አይደል? አንድ ሁለት ሚኒስትሮች ነበሩ?
ያንጊዜም #እርካታ አልነበረም። የአማራ ሊቃናት ተመድበውም ያደረጉት ነገር ሲባል ምን አለ? ……… ተሰለፈ ……… ተሰለፈ የአማራ ወጣት፤ "ከጎዳና ወደ ፓርላማ" ተብሎም ሞካከረ። መጨረሻው ዱር ቤቴ ሆነ። ቅራኔው - ተካረረ። ሁሉም ቀርቶ አሁን ጭራሽ ጉዳዩ ወደ የሁለት አገሮች ፍጥጫ ሆኗል። በዚህ ውስጥ የአማራ ፖለቲካዊ ጥያቄ የሚባል የለም። ሊደራደሩ የሚችሉት ዕድሉ ከተገኜ የኤርትራ መንግሥት እና የኢትዮጵያ መንግሥት ብቻ።
/;/ ልዩ ማስታወሻ።//
"#ወ" ሊንክ ተውሼ ወይንም ቀስሜው አይደለም። ወይንም ኮርጄው አይደለም። ልክ ብልጽግናን #ብልፄው እንደምለው፤ የእኔ #የራሴ ዘይቤ ነው። አብይወለማ፤ ደመቀወገዱ እያልኩ በኦሮማራ ዘመን መፃፌን የብዕሬ ደንበኞች የሳተናው የዘሃበሻ አምደኞች ታውቅታላችሁኝ።
ወደ ቀደመው ስመለስ ኃላፊነት ቦታውን ማግኜቱ ብቻ ሳይሆን፤ እንደ ክቡር አቶ ሙስጠፌ መሐመድ ነፍስ ያለው ተግባር መፈጸም ይገባል። ነገ ጠቅላላውን የኢትዮጵያን ካቢኔ ሊይዙ የሚችሉ እሳት - የላሱ፤ ሳተና፤ ትንታግ፤ ዓራት ዓይናማ የሱማሌ ወጣት የፖለቲካ ሊቃናትን ሁሉ አፍልቀዋል። ክልሉ ሰላም ነው። የፓርላማ አፈ ጉባኤነት፤ የሱማሌ ክልል የአመራር መቅኖ ያስገኜው የስበት ቅኔ ነው። ይገባቸዋል። ስንት ነገራችን ቆጥበዋል። የመንፈስ ስለሆነ መመዘን አይቻልም። ዕንባችን ቁሟል። እረድተውናል።
ብዙ አቅማችን ተቆጥቧል። ዕንባችን ታብሷል። የምንከፋበት ሁነት ተሻሽሏል። የቀረው የፖለቲካ ውክልና በሱማሌ ክልል #ተዋፆ ብቻ ነው እንጂ ለመኖር፤ ኢንቤስት ለማድረግ፤ እርፍ ብሎ ለመመለስ ሱማሌ ክልል ናሙና ነው።
እዛ የሚመደቡ የዩንቨርስቲ ተማሪወች ሰቀቀን የለባቸውም። ወላጆችም አያስቡም። የፖለቲካ ጭካኔ አናዳምጥም። ሲመደቡም፤ ምደባ ተሳካልኝ ቢሉ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ የአቶ ሙስጠፌ ጉዳይ ነው። የተመደቡ ዕለት ነው የፃፍኩት። የመጡበት የማንነት መደብ #ሰብዕዊነት ነው። ይህን በገቢር አይቻለሁኝ።
ኢትዮጵያ የሜዳሊያ ሽልማት ካላት ሱማሌ ክልል መስተዳድሩ እና ህዝቡ ሊሆኑ ይገባል ባይ ነኝ። ብዕራችን በሳቸው ምስክርነት አላፈረችም - እስተዛሬ። ነገን ሲመጣ …… ነገ ይዳኜው። በዚህ ቀውጢ ጊዜ ተፈትነው ስላለፋ ልምዱም፤ ተመክሮውም ሲኖር የተሻለ ተስፋ ይኖራል ለነገም ብዬ አስባለሁኝ።
አፋር ክልልም የተከበሩ አቶ ሃጂ አወል አርባም ህወሃት ከሚፈጥረው #ቀውጢ ህውከት ባሻገር፤ ሌላ ቦታ የሚታዩ የጭካኔ አይነቶች፤ የማንነት መገፋት፤ ከባዕት መነቀል አላደመጥነም። ምስጉን ክልል ነው። የፖለቲካ ውክልና ተዋፆ ግን ሊታሰብበት የሚገባ ይመስለኛል። የአማራ ክልል ሁሉንም ይይዛል፤ ሌላው ክልል ግን ምንም።
የማከብራችሁ ቤተ ሥርጉትሻ ቅኖችም ውዶቼም።
ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ የሰጡትን መልስ አዳምጡት። እያንዳንዱን ቃል፤ ሐረግ፤ ስንኝን ……… ትዕዛዝ አይደለም። ኧረ ምን በወጣኝ? ብዙ የታመቀ የአመክንዮ ሁነቶች ስላለበት ……
Schau dir "Ethiopian Parliament Live Today | Prime Minister Abiy Ahmed’s New Cabinet Appointments | አብይ አህመድ"
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
08/10/926.
ይህን ዝርዝር የወሰድኩት ከኖር በጊዜ ፔጅ ነው። አመሰግናለሁኝ።
"አቶ ተመስገን ጥሩነህ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት ሲቀጥሉ ኢትዮ ቴሌኮምን ሲመሩ የነበሩት ፍሬህይወት ታምሩ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል ።
1. ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቶ ተመስገን ጥሩነህ ለምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት ዕጩ አድርገው አቅርበዋል።
2.ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው በጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዕጩነት ቀርበዋል።
3.አቶ አዲሱ አረጋ የገብርና ሚኒስትእ ሆነው እንዲሾሙ በጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዕጩነት ቀርበዋል።
4.ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) የገንዘብ ሚኒስትር ሆነው እንዲሾሙ በጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዕጩነት ቀርበዋል።
5.አቶ መሀመድ እድሪስ የሀገር መከላከያ ሚኒስትር ሆነው እንዲሾሙ በጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዕጩነት ቀርበዋል።
6.ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በድጋሚ የትምህርት ሚኒስትር ሆነው እንዲሾሙ በጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዕጩነት ቀርበዋል።
7.ወ/ሮ ሀና አርያስላሴ የፍትህ ሚኒስትር ሆነው በጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዕጩነት ቀርበዋል።
8.ወ/ሮ ያስሚን ወሀብረቢ የንግድና ቀጠናዊ ስትትር ሚኒስትር ሆነው በጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዕጩነት ቀርበዋል።
9.ፍስሃ ይታገሱ (ዶ/ር) የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ሆነው በጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዕጩነት ቀርበዋል።
10.ዶክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሆነው እንዲሾሙ በዕጩነት ቀርበዋል።
11.ዶ/ር መቅደስ ዳባ የጤና ሚኒስትር ሆነው በጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዕጩነት ቀርበዋል።
12.አቶ አወሉ አብዲ የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሆነው በጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዕጩነት ቀርበዋል።
13.ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ የገቢዎች ሚኒስትር ሆነው በጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዕጩነት ቀርበዋል።
14.አቶ በረከት ፍስሃፅዮን የብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስትር ሆነው በጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዕጩነት ቀርበዋል።
15.ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ ለባሕልና ቱሪዝም ሚኒስትርነት ዕጩ ሆነው ቀርበዋል።
16.ወ/ሮ አለምፀሃይ ጳውሎስ በማዕድን ሚኒስትርነት ዕጩ ሆነው ቀርበዋል።
17.አቶ ሳዳት ነሻ የሎጅስቲክስ ሚኒስትር የሆነው በጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዕጩነት ቀርበዋል።
18.ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር የሆነው በጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዕጩነት ቀርበዋል።
19.አቶ ሙሳ አደም የሰላም ሚኒስትር የሆነው በጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዕጩነት ቀርበዋል።
20.ኢትዮ ቴሌኮምን ሲመሩ የነበሩት ፍሬህይወት ታምሩ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር የሆነው በጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዕጩነት ቀርበዋል።
21.ኢንጂነር ሙሐመድ አብዱራህማን የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ሆነው በእጩነት ቀርበዋል።
22.ሱልጣን ወሌ (ዶ/ር ኢንጂነር) የመስኖ እና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር ሆነው በዕጩነት ቀርበዋል።
23.አክሊሉ ታደሰ (ዶ/ር) የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር ሆነው በእጩነት ቀርበው ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀረቧቸው ዕጩ ሚኒስትሮች በሙሉ ድምጽ ፀድቀዋል።"
Ghion Maleda ግዮን ማለዳ
በዚህ ጉዳይ ከስር ያለውን የቴሌግራም ቻናላችንን join
በማድረግ መሰል ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ ሊንክ
See less
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ