ልጥፎች

ከጁላይ 22, 2026 ልጥፎች በማሳየት ላይ

#ገዳይ ሃሳብ በአካልም ይሁን በመንፈስ #በታኝ ነው።

  #ገዳይ ሃሳብ በአካልም ይሁን በመንፈስ #በታኝ ነው።   "እግዚአብሄር ቃየልን ወንድምህ አቤል ወዴት አለ አለው፤ ቃየልም በልቡ ትዕቢት የወንድሜ የአቤል ጠባቂ ነኝ አለ። አቤል ንጹሕ ሰውን ሆነ ቃየል ግን ደግ ሰው ወንድሙን አቤልን በመግደል ኃጢያተኛ ሆነ።" (መጸሐፈ መቃብያን ቀዳማዊ ም ፳፰ ቁ ፬ - ፭)   #ምዕራፍ ፲፱።   እንዴት አደራችሁ ማህበረ - ቅንነት።    እኔ አቶ ሽመልስ አብዲሳን ኢትዮጵያዊ #ጎልጉል እላቸዋለሁኝ። ግልጽ እና ቀጥተኛ ሃሳባቸውን ማጋራታቸው መልካም ነገር ነው። አይደለም በአገር ደረጃ በቤተሰብ እንኳን ይህን መሰል ግልጽ እና ቀጥተኝነት ጠቃሚ ጉዳይ ነው። ትዕቢታዊ ሁነታቸው ግን ይጎፈንነኛል። መታበይ ወንዝ አያሻግርም፤ ሥልጣንንም አያጸናም።    4ሺ ኢትዮጵውያንን በጋራ አሰባስቦ ያለው አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ረጅም ጊዜ የወሰደበትን ተልዕኮ ለመቋጨት ስምንት በኽረ አጀንዳወችን የያዘ የመወያያ አቅጣጫ አመልካች ሰነዱን ሰሞኑን አስተዋውቋል። የተሳታፊ ቁጥር እየጨመረ ስለመሆኑም እያደየጥኩ ነው። " ኑ በራችን ክፍት ሆኖ ይጠብቃችኋል" የሚል ዕድምታ እንዳለም አንብቤያለሁኝ።   የሆነ ሆኖ ከዚህ ጋር በተያያዘ ብልፄው እንደ ፓርቲ ለምክክር ኮሚሽኑ አቀረበ የተባለው ሰነድ ደግሞ በአቻነት ወጥቷል። ከውስጥ የተገኜ መረጃ ይሉታል ዘመነኛ ተጽዕኖ ፈጣሪወች ወይንም የዩቱብ ባለቤቶች።    እንደምን የሚስጢር በር ለእነሱ ቧ ብሎ እንደሚከፈት፤ ለሌሎቻችን ደግሞ ክርችምችም እንደሚል በይገባኝም። የክት እና የዘወትር፤ የቤት እና የእዳሪ ልጅነት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ልሙድ ነው።   የኦሮምያ ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ አገራዊ ምክክሩን ተከትሎ፤...