ልጥፎች

ከፌብሩወሪ, 2019 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የዴሞክራሲ ግማዱ እና ገመዱ;

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  የዴሞክራሲ   ግማዱ እና ገመዱ ። „ ምንም እንኳን በለስም ባታፈራ፣ በወይን ሐረግ   ፍሬ ባይገኝ፣ የወይራ ሥራ ቢጓል እርሾችም መብልን   ባይሰጡ በጎችም ከበረት ቢጠፉ ላሞችም በጋጥ ውስጥ   ባይገኙ እኔ ግን በእግዚአብሄር ደስ ይለኛል፤ በመዳህኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ። “ ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯ ቁጥር ፲፰ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 28.02.2019 ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ። ·        እፍታ። ውዶቼ እንዴት ናችሁ ደህና ናችሁ ወይ? አንዳንድ የኢሜል ወዳጆቼ መልዕክት እዬላኩልኝ ነው። እምታምኛቸው መሪዎች „ ኢትዮጵያን ከዱ“ እዬተባልኩ ማለት ነው። እኔ እኮ መልካም ሲሰሩ እንደማመሰግናቸው ሁሉ ትክክል አይደለም የምለውን ደግሞ እስሲበቃቸው ድረስ ነው እማከናንባቸው። ቅን መሆን፤ ልብን ከፍቶ መቀበል፤ አወንታዊ መሆን፤ አዲስ እንግዳ ሲመጣ አንጥፎ ጎዝጉዞ መቀበል የአባት አደሩ ነው። ይሄ ሆነ ብዬ ወደፊትም መልካም ነገር ሳይ አልሸሽም።  በሌላ በኩል በቀደመው ጠ/ሚር ከመሆናቸው በፊት በነበረው የጠ/ሚር አብይ አህመድ ንግግር ውስጥ ሁሉ አንደም ውስልትና በኢትዮጵያ ላይ አላገኘሁም። አሁንም ይህ ጽኑ እምነቴ ነው። የአፍ ወለምታ ግን አያለሁኝ። ይህንም በተለያዬ ጊዜ ሞግቻቸዋለሁኝ። እራሱ የሰሞኑን የለገጣፎ ጉዳይ የድርጅታቸውን ወስኜ "አላውቀውም የከተማ ከንቲባ ስላልሆንኩ" ያሉትን ጽፌባቸዋለሁኝ። አፋር ላይ „ደርግ የወረደው ህዝብ ስለጨፈጨፈ ነው“ ስላሉም ይህንንም ሞግቻቸዋለሁኝ፤ በቅርቡም እንዲሁ አንድ ከብድ ያለ አምክንዮ እነስቼ ሞግቻለሁኝ።

በቃል መገኘት መልካም ነው። በቃል ወስጥ ተስፋ አለና።

ምስል
በቃል መገኘት መልካም ነው። በቃል ወስጥ ተስፋ አለና። የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፤ እግዚአብሔር ደግሞ አካሄዱን ያቃናለታል“ ምሳሌ ምዕራፍ ፲፮ ቁጥር ፱ ከሥርጉተ©ሥላሴ  Sergute©Selassie 27.02.2019 ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ ·        መነሻ። Ethiopia ፡ ጠ / ሚ ዐብይ ለ 10 ወራት የያዙትን ሚስጥር አወጡት [ ሙሉመግለጫ ] Ethiopian news - PM Abiy Ahmed speech https://www.youtube.com/watch?v=2juObKZP3Io Ethiopia ፡ ጠ / ሚ ዐብይ ለ 10 ወራት የያዙትን ሚስጥር አወጡት [ ሙሉመግለጫ ] ክፍል 2 Ethiopian news - PM Abiy Ahmed speech 2 https://www.youtube.com/watch?v=s0kXEK0zXc8&t=2s ውዶቼ እንዴት ናችሁ? በዚህ በጠ/ሚር አብይ አህመድ ገለፃ „ይህ ቀን ይመጣል ተብሎ አልተሰበም ነበር፤ ቀድሞ የተናገረ አንድም ፖለቲከኛ አልነበረም።“ ብለዋል እሳቸውን ጨምሮ ይህን ከሥር የለጠፍኩትን ሊንክ ገብቶ መፈተሽ ነው። ቀን ከሌት ነበር የተተጋበት።  ለማገናዘብም ሳተናው ድህረ ገጽም ላይ አብዛኛው የሙግት መንፈስ ይገኛል። የተወሰነው ቢነሳም ማለት ነው። „ምጥን እና ህሊና“ ሳተናው ላይ ባይኖሩም እዚህ አርኬቡ ላይ አሉ ሁለቱም ጹሑፎች። ቀሪዎቹ ደግሞ ሳተናው ድህረ ገጽ ላይ ይገኛሉ። ሳተናው እራሱ በምን ያህል ጥንካሬ እንደተጋ መዳህኒዓለም አባቴ ብቻ ነው የሚያውቀው። ፍጹም ቅን የሆነ ፍጥረት ነው ሳተናው። ያ መልካም ተስፋ በዛ ድህረ ገጽ ውስጥ ባይኖር ኖሮ እንደሌሎቹ የእሱም ድህረ ገጽ ልሙጥ ይሆን ነበር። በግሉ እራሱ

እሸት ራዕይን ምራቁን በዋጣ ቻይነት ምህንድስና ብቻ አዋጭ ነው።

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  ጠንቃቃነት ያተርፋል እንጂ አያከስርም።  „ ምንም እንኳን በለስም ባታፈራ፣ በወይን ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፣   የወይራ ሥራ ቢጓል እርሾችም መብልን ባይሰጡ በጎችም ከበረት ቢጠፉ ላሞችም በጋጥ ውስጥ ባይገኙ   እኔ ግን በ እግዚአብሄር ደስ ይለኛል፤ በመዳህኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ። “ ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯ ቁጥር ፲፰ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 26.02.2019 ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ።                                ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ እንዴት አላችሁልኝ። ደህና ናችሁ ወይ? በአንድ ጉዳይ ዙሪያ ትንሽ ነገር ልል አሰብኩኝ። አብን ሚሊዮነም አዳራሽ በተከታታይ ጠይቆ እንዳልተፈቀደለት ይልቁንም OMN እንደተፈቀደለት ገልፆል። በዚህ አብን ተከፍቷል። ተገልለኩኝ እያለ ነው። ይህን መጠበቅ ያስፈልጋል። ስለምን? አሁንም የዞግ ፖለቲካ ነው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው። አውራው ፓርቲ ደግሞ ኦዴፓ ነው። የምናደምጣቸው ዝበት ያለባቸው ነገሮች ከኦዴፓ የመነጩ ሳይሆኑ ከራሱ ከኢትዮጵያ የዞግ ፖሊሲ ነው የሚመነጨው። አድሎ፤ መገለለ፤ መጫን፤ ጭቆና ዴሞክራሲ በሌለበት አገር ግድ ነው። ተጋድሎው እኮ ሁሉን እኩል የሚያደርግ ቋሚ ሥርዓት ይፈጠር ነው። ለዛ ደግሞ በአንድ ጀንበር የሚሆን አይደለም።  የለውጥ መሪዎቹ እራሱ እኮ ከዞግ ድርጅት የወጡ ናቸው። ሥነ - ልቦናቸው፤ ልምዳቸው ተመክሯቸው በዛ ዶክተሪን የተቃኜ ነው። ከዚህ ለመፈታት ጊዜ ይጠይቃል። እያንዳንዱ መሪ ከራሱ ጋር እኮ አሁን ፍትጊያ ላይ ነው ያለው። ሬድ ሜድ እንዲሆኑም እንሻለን።  አሁን እኔ ዶር ለማ መገርሳ እና ዶ