በቃል መገኘት መልካም ነው። በቃል ወስጥ ተስፋ አለና።

በቃል መገኘት መልካም ነው።
በቃል ወስጥ ተስፋ አለና።
የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፤ እግዚአብሔር
ደግሞ አካሄዱን ያቃናለታል“ ምሳሌ ምዕራፍ ፲፮ ቁጥር ፱
ከሥርጉተ©ሥላሴ
 Sergute©Selassie
27.02.2019
ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ



·       መነሻ።

Ethiopia / ዐብይ 10 ወራት የያዙትን ሚስጥር አወጡት [ሙሉመግለጫ] Ethiopian news - PM Abiy Ahmed speech

Ethiopia / ዐብይ 10 ወራት የያዙትን ሚስጥር አወጡት [ሙሉመግለጫ] ክፍል 2 Ethiopian news - PM Abiy Ahmed speech 2


ውዶቼ እንዴት ናችሁ?

በዚህ በጠ/ሚር አብይ አህመድ ገለፃ „ይህ ቀን ይመጣል ተብሎ አልተሰበም ነበር፤ ቀድሞ የተናገረ አንድም ፖለቲከኛ አልነበረም።“ ብለዋል እሳቸውን ጨምሮ ይህን ከሥር የለጠፍኩትን ሊንክ ገብቶ መፈተሽ ነው። ቀን ከሌት ነበር የተተጋበት። 

ለማገናዘብም ሳተናው ድህረ ገጽም ላይ አብዛኛው የሙግት መንፈስ ይገኛል። የተወሰነው ቢነሳም ማለት ነው። „ምጥን እና ህሊና“ ሳተናው ላይ ባይኖሩም እዚህ አርኬቡ ላይ አሉ ሁለቱም ጹሑፎች።

ቀሪዎቹ ደግሞ ሳተናው ድህረ ገጽ ላይ ይገኛሉ። ሳተናው እራሱ በምን ያህል ጥንካሬ እንደተጋ መዳህኒዓለም አባቴ ብቻ ነው የሚያውቀው። ፍጹም ቅን የሆነ ፍጥረት ነው ሳተናው። ያ መልካም ተስፋ በዛ ድህረ ገጽ ውስጥ ባይኖር ኖሮ እንደሌሎቹ የእሱም ድህረ ገጽ ልሙጥ ይሆን ነበር። በግሉ እራሱ ስንት ጥረት ነው ያደረገው ሳተናው ለኢትዮጵያዊነት ሲባል። ብቻ የእኛ ነገር የፊቱ የኋዋላ፤ የኋዋላው የፊት እዬሆነ ተቸገርን እንጂ። 

ይልቅ ኦህዴዶች / ኦዴፓዎች እነሱ በቃላቸው ውስጥ ስለመዝለቃቸው እራሳቸውን መመርምር ያለባቸው ይመስለኛል። ከዚህ በተረፈ በሎቢ የተሠራውን ወሳኝ ጉዳይ እዮር ያውቀዋል። ይመሰክረዋልም። ከፈለጉ ጠ/ሚር አብይ አህመድ የጀርመኗን ጠ/ሚር ክብርት ወ/ሮ አንጌላ ሜርከልን መጠዬቅ ነው።  

ይልቅ ቃል የዕምነት ዕዳ ነውና በቃል ውስጥ ጸንቶ በመቆም ሁሉን ኢትዮጵያዊ ዜጋ እኩል በተስፋው ልክ ቤተኛ ማድረግ ላይ ቢበረቱ መልካም ነው። የመርዶ ዜና አቁስሎናልና። ህዝቡም ስጋት ላይ ነው። በተጨማሪም ትእግስት ሲያልቅ ፍቅር መሰደዱን ልብ ሊሉት ይገባል። ፍቅር ያዘነበው ህዝብ ድንጋይ ለመወርወር አያቅተውም። ፍቅርን መስጠት ግን የመደዴ ጉዞ አልነበረም። 

የሆነ ሆኖ እኛ የታገለነው ለኢትዮጵያዊነት እንጂ ለኦሮሞያ አገራዊነት ወይንም ለኦሮሞ ኢንፓዬር አይደለምና። ቅንነትን ተሸናፊ ማድረግ  የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሊሂቃን ባህል መሆኑ ግን ከማንም በላይ እኔን ያሳዝነኛል። ሁሉንም ነገር በቅንነት አይቼ ሳልጠራጠር  እተጋበት እና መጨረሻው መርዶ ነው የሚሆነው።  

አሁን ከሰሞኑ ርዕዮት ተርጎሞ ያወጣው እንቅልፍ የሚነሳ ጉዳይ ነው። የከረባት የገበርዲን መቀያዬር ሳይሆን ዕውነት እራሱን ችሎ የሚቆምበት ዘመን ናፍቆን ነበር ያን ያህል በግራ በቀኝ ሰላማችን እዬታወከ እሳት ውስጥ ገብትን የተማገድንላቸው። የዛሬው ጨዋታ ደግሞ ሌላ ሆኗል። ኢትዮጵያ እኮ ካለዜጎቿ ምድረ በዳ ናት። ዛሬ በለገጣፎ ለገዳዲ ያለው ዜጋም ዜጋቸው ነው።

ኢትዮጵያ የእነዚህም መስኪኖች እናትም ናት። አልሰማሁም አልሰማን ማለትም አይቻልም። ይህ ከሆነ የቡራዩን እንዴት ሰምተው ነው ጠ/ሚር አብይ እቦታ ተገኙ? ቀድሞ ነገር የኦህዴድ /ኦዴፓ ሊቀመንበር እኮ ናቸው። የታሰርኩበት ገመድ አለ ቢሉን ይልቅ ያስማማናል። 

ወይንም ቅደመ ሁኔታ አለብኝ ቢሉን። ይህንንም ከሐምሌው ዝምታ ጀምሮ ልብ የምንላቸው ጉዳዮች ስላሉ … በውጭ ጉዳይ ይሁን አገር ውስጥ ባሉ ነገሮች የሚስተዋሉ የዘበጡ ጉዳዮችን እንታዘባለን። እኒህ ሰው ነፃ ናቸውን እስክንል ደረስ የደረሱ ጉዳዮች አሉና።

·       የሆነ ሆኖ ይህን ፈጽሞ አልጠብቅም ነበር ከዶር ለማ መገርሳ - እኔ።

Ethiopia: Reyot - ርዕዮት የአዲስ አበባንና ዙርያዋን የህዝብ ተዋጽኦ Demography ለመለወጥ እየተሰራ መሆኑን አቶ ለማ መገርሳ አምነዋል፡፡


ወደ ቀደመው ምልስት ሳደርግ ቀድሞ የተሻለ ቀን ይመጣል ብለን ግን መተንበዩን  ተናግረናል፤ ተግተናል፤ ሰርተንበታል። ያ ድካመ ለአንቶ ሌንጮ ለታ ዓላማ ስኬታማ መሆኑ ነው መከራው። ያ ጥረት ያ ድጋፍ እና ያ ተዝቆ የማያልቀው እምነት በልግስና የተሰጠው ፍቅር ለጃዋርውያን፤ ለአራርሳውያን፤ ለህዝቃያላውያን መፈንቅለ መንፈስ መዋሉ ነው አሳዛኙ ጨለማዊ ትዕይንት። አሁን ደግሞ ዶር አረጋይ በርሄን ኮፍሳችሁ ዘውድ መድፋታችሁን እያስተዋልን ነው።

ቅኖች እንደ ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ አገላለጽ „ሞኞችማ“ ተጋንበት እኮ መልካም ዘመንን ተመኝተን። በዬትኛውም ሁኔታ አማራ መገፋቱን ቀድመን ነው የነቃነው። በአንደበት ለመግለጽ እኮ እያቀተ አይተናል። ኦዴፓ እነማን እንደሚቀርቡት ዓይን አለን እናያለን፤ ጆሮ አለን እንሰማለን።

… ብቻ እኔ የሐምሌው ዝምታ የቡና ፖለቲካ የተከዘነ መከራ አለበት ብዬ ስለማስብ ይህ መፈንቅለ ተስፋ ከዛ ወዲህ የመጣ ነው ብዬ አስባለሁኝ። ሌላ ቅድመ ድርድር  በእገታ እንደተከወነ ነው እኔ እማስበው። እራሱ የሰኔ 16 ጉዳይም ትብትቡ ብዙ ነው። ቀደም ብዬ ጽፌዋለሁኝ። በራሳቸው ሰዎች የታቀደ እንደሆነ ነው እኔ የሚሰማኝ። በዚህም በስፋት ጽፌበታለሁኝ።

በሌላ በኩል አሁንም እኔ እማምነው የቀደመው የጠ/ሚር አብይ መንፈስ ሰውኛ ነው፤ ተፈጥሮኛ ነው፤ በሥነ - ግጥማቸው ውስጥ ኢትዮጵያ በውስጣቸው ያሰበለች ስለመሆኑ ተርጉሜ ደርሸበታለሁኝ። የጋዜጠኛ እና የጸሐፊ ፍቅር ስንታዬሁ „ የኦህዴድ ሞተር ማነው“ የሚለውም እንዲሁ ብዙ ነገሮችን ይገልጻል።

የሆነ ሆኖ በማህል ያለ የታመቀ ዲያቢሎሳዊ መንፈስ እንዳለ ግን ይረዳኛል። እራሱ የቆሞስ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ሞት ደመ ከልብነት ጀምሮ አቅጣጫውም ያሰጋኛል። ወንጀል የሚባሉት ሁሉ እዬታፈኑ እንዲቀመጡ ወይንም በቀጠሮ እንዲከዘኑ መደረጉ ራሱን የቻለ የምርምር ተግባር ነው። እንዳይገላጥ የሚፈለግ ድፍን ሴራ አለ። በንጽህና ውስጥ ያለ ማሸነፍ ይዘልቃል። በስተቀር ግን እንደለመደብን አፍሰን መልቀም፤ ለቅመን ማፍሰስ ነው … መቼስ ሐሴት አታግኙ ተብሎ የተፈረድን አይደለን።

·       ክቡር ሆይ! እስኪ ይህን ጊዜ ካለዎት ይመርምሩት።


የሆነ ሆኖ „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ እውነት ካልነበረም ኢትዮጵያዊነት አታሎ፤ ከድቶ፤ ሸውዶ ማለፍ አይቻልም። ኢትዮጵያ አምላክ ያላት አገር ናት እና። ይልቅ ራስን ወቅሶና አርሞ እና ገስጾ ግድፈትን ማረም የሚገባ ይመስለኛል። ምርቃቱ ከመነሳቱ በፊት። ሁለት ወዶ አይሆንም። አንዱን መምረጥ ነው ወይ እንደ ጃዋርውያን ኦሮሞ ዜግነትን ወይን ደግሞ እንደ ምልዕቱ ኢትዮጵያዊ ዜግነትን።

ዛሬ በጫና የሚፈለገው ነገርን ማስፈጸም ይቻል ይሆናል። „ኦሮምኛ ቋንቋ እና  የአዲስ አባባ ጉዳይ እዬተሰራበት“ መሆኑ ስለተገለጸ። ነገ ግን ጫና ተከሉ ዓዋጅ አይበረክትም። ከሁሉ በላይ የቅኖች አማላክ ይክሳል። ከእዮር ቁጣ የሚያመልጥ አንዳችም ነገር የለም። ቅኑ፤ ደጉ፤ የዋሁ፤ ሰው አማኙ አማራም ቢሆን ፈጣሪ አለለት። „የሚመካ በእግዚአብሄር ይመካ“ ይላል ቅዱስ ቃሉ።

ግልጽ መንገድ ነው ጥሩ ነገር። ሰውር መንገድ ሰውሮ ነው የሚቀረው። ቀድሞ ነገር ፈጣሪ ብርሃን ነው። የፈጣሪ ስራ የብርሃን ነው። ጨላማን የሚሻው ዴያቢሎስ ብቻ ነው። ከዲያቢሎስ ጋር ከተሆነ ደግሞ መጨረሻው አያምርም። ከ አንድ ክርስቲያን ሊሂቅ ደግሞ ይህ አይጠበቅም። መጨረሻው አያምርም እና ... 

ቀደም ባለው ጊዜ አንድም ቀን OMN የጠ/ሚር አብይ አህመድ እና የዶር ለማ መገርሳ የኦሮምያ መስተዳደር ፕሬዚዳንትን ምስል መልካም ተግባር አቀርቦ አያውቅም። ጣና ኬኛ እራሱ የተፈጥሮ ጥበቃ ዘመቻ ብለው ነበር ያለፉት። ዛሬ አራጊ ፈጣሪ ደግሞ እነሱ ናቸው። ያን ጊዜ ግን ቅኑ አማራ ነበር ተግቶ ተቀባይነት እንዲኖራቸው የሠራው። ማተብ የሚባል ከኖረ።

ቸር ወሬ ያሰማን አማኑኤል። አሜን!



                                        የኔዎቹ ኑሩልኝ።

                                         መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።