ልጥፎች

ከጁላይ 19, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ልበልሽ ይሆን ውዳሴ? ይመቸዋል እና ለነፍሴ፨

ምስል
·        https://www.lora.ch/programm/alle-sendungen?list=Tsegaye ·        https://www.facebook.com/sergute.selassie/ https://sergute.blogspot.com/2021/02/blog-post.html?spref=tw

ፍትህ ፈላጊ ቅድሚያ #ለራሱ ፍትህ ይስጥ።

  ፍትህ ፈላጊ ቅድሚያ #ለራሱ ፍትህ ይስጥ።  ፍትህ ፈላጊ በቅድሚያ ለሚፈልገው የትግል #አቅጣጫ ፍትህ ይስጥ።  ፍትህ ፈላጊ ለሚያራምዳቸው #ሃሳቦች ፍትህ ይስጥ።  ፍትህ ፈላጊ የሌሎችን #የፍላጎት አቅጣጫም ያድምጥ።  ይህን ሳያደርግ ፍትህ #ጠማኝ መሆን አይችልም።  ምክንያት ፍትህ አሰጣጥ ከራስ ስለሚጀምር።  ሥርጉትሻ2024/07/19

#ስኬት የሰማይ #መና አይደለም።

ዕውነት ዬሕይወት #ውበት ነው።  ዕውነት ከህይወት ጋር ሲዋህድ ጠረኑ ለሰው ልጅ #ቅርብነት ነው። ዕውነት ሲኖር ቅርብ የሆነ የሰው ልጅ #ሽታ #በጣዕም ይከሰታል። ዕውነት ስለሰው ልጅ #ቅርፅ አይደለም። #እእ ።  የሰው ልጅ ሰብዕና የይዘቱ ፍልስፍና የዕውነት ውበት ነው።  ሥርጉትሻ2024/07/19   #ስኬት የሰማይ #መና አይደለም።  ስኬት የአመራር #ብቃት ውጤት ነው። #ልቅናም የአመራር ጥበብ ሥልጣኔ ከከፍተኛ እርከን ሲደርስ የሚገኝ ውጤት ነው።    #የአመራር #ብቃት + የአመራር ጥበብ #ልቅና = #የአመራር #ልዕልናን ብራንድን ይፈጥራል።  ይህ እንግዲህ ለታደሉት የሚሰጥ ፀጋ ነው። መማር ብቻውን ለዚህ የሚያበቃ አይመስለኝም።  የማስተዋል፤ የአትኩሮት፤ የማቀድ፦ የመረጋጋት ተመስጦ እና የመፈፀም ክህሎታዊ አቅምን ይጠይቃል።  ከሁሉ የፈቃደ እግዚአብሄር እና የፈቃደ አላህ መቅደም፤ ጥሞናዊ ራስን የመግራት ሂደት የስኬትን #ደርባባ #ቋሚ #አሻራን ይወልዳል የሚል ሙሉ እምነት አለኝ። ሥርጉትሻ2024/07/19  

ክህሎት ...

 ክህሎት በሂደት የሚገኝ የተመክሮ አወንታዊ ቅምረት ነው በእኔ ዕይታ። ክህሎት የሚገኘው ተሰጥዖን በማዳበር እና #ስሜት እና ህሊናን #በማሰልጠን ነው የሚል ሙሉ ዕምነት አለኝ። ሥርጉትሻ 2024/07/19

ሰው #ከዕንቁ በላይ የከበረ ነው።

  ሰው #ከዕንቁ በላይ የከበረ ነው።  ለሰው ልጅ #ስሜት እና #ህሊና #ቅርበት እና #ትርጉም መስጠት ነው መሪነት። መሪነት ማዕከሉ #ሰው ሊሆን ይገባል።  ይህም ልሙጥ ሊሆን አይገባም። #ሰብዓዊ መሆን ይገባዋል።  የሰው ልጅ መከፋት ሆነ መደሰት #ውስጡ ሊሆን ይገባል።  በምድራችን ካሉ ድንቅ ነገሮች በላይ የሰው ተፈጥሮ #ዕፁብ #ድንቅ ነው። ዕፁብ ድንቅ ተፈጥሮው የሰው ልጅ ምድርን በጥበቡ ለመኖር ብቁ አኗኗሪ ፈጥሮ ይጠበብባል።  ስለሆነም ከሰው የሚነሳ ዕሳቤ #ሰዋዊ እንጂ #ሸቀጣዊ ሊሆን አይገባም። ሰዋዊነት እንደ ሸቀጣ ሸቀጥ #በገቢያ ህግ ስለማይገዛ። ሥርጉትሻ 2024/07/19

ሕይወት

  ሕይወት #የጥያቄ እና የመልስ #ጭማቂ ናት የሚል ዕምነት አለኝ። ይህ ማለት ህይወት በዬራሳቸው የአፈጣጠር አንባ የሰሉ ሁለት የማይጣጣሙ ተቃራኒ ነገሮች ጥምረትም ናት እንደ ማለት። ሥርጉትሻ 2024/07/19

እንዳሻህ ሂድብኝ ...

  ግድዬለም፦ ግድዬለም እንዳሻህ ሂድብኝ አዬር ካልቸገረኝ፦ እኔ ምን ሲገደኝ ብቻማ --- ብቻማ /// ምልሰትህ አይራቀኝ ሰባዕዊነት ጥራኝ።  ጠረንህም ይጥማኝ!  ሥርጉትሻ024/07/19

በመልካምነት ውስጥ ...

 በመልካምነት ውስጥ #በቀል የለም።  በደግነት ውስጥ #ምቀኝነት የለም።  በርህርህና ውስጥም #ኢጎ ድርሽ አይልም።  በአዛኝነት ውስጥ #ምቀኝነት የለም። በአይዟችሁም ውስጥ #ጥርጣሬ የለም።  በቅንነት ውስጥ #ቅጥፈት ድርሽ አይልም።  በአወንታዊነት ሰብዕና ውስጥ #ክልል አይኖርም። ሥርጉትሻ2024/07/19

#ማመዛዘን እና #ማስተዋል ሲኖር የሰው ልጅ #መከፋት ውስጥህን ይፈትሽ ዘንድ ትፈቅዳለህ።

  #ማመዛዘን እና #ማስተዋል ሲኖር የሰው ልጅ #መከፋት ውስጥህን ይፈትሽ ዘንድ ትፈቅዳለህ።  ወሰን አይኖርህም። ደንበር አትሰራም ዝልቅ ዕሳቤ ለተፈጥሮ እና ለሰው ልጅ ይኖርኃል። እንክብካቤ እኩል እንዲሆን ትሻለህ። ልዕልት ዓለም ተባደግ ብትሆንም።  ለሌላው መከፋት ውስጥህን ስትገብር #ፈቃዱ #ያስጨንቅኃላ #ያ ነው #ሰባዕዊነት ፤ ያ ነው #ተፈጥሯዊነት ። አፈፃፀሙ ተባደግ ሆነ እንጂ ለሁሉ ሰው ሆኖ ከመፈጠሩ ጋር በእኩልነት የተሰጠው በረከተ - ፀጋ ይህ ብቻ ነው።   ሥርጉትሻ 2024/07/19

" #እምዬ፤ #ማር፤ ጌታ፤ ብላቴ፤ ሊጋባ፤ መልካምሰው፤ ደግሰው"

  # ሰባዕዊነት ሆነ #ተፈጥሯዊነት የመማር ያለመማር ጉዳይ አይደለም። የሰው ልጅ የመፈጠሩን ሚስጢር በጥልቀት ከማገናዘብ የሚገኝ #የማስተዋል #አቅም እንጂ። " #እምዬ ፤ #ማር ፤ ጌታ፤ ብላቴ፤ ሊጋባ፤ መልካምሰው፤ ደግሰው" የሚሉ የበጎነት የክብር ሥሞች #ከሃይድልቨርግ ዩንቨርስቲ ከጀርመኖች ተመርቀው አልነበረም ቀደምቶች የርህርህናቸው ጥልቅነት በፈርኃ #እግዚአብሄር ፤ እና በፈረኃ #አላህ የታሸ የተቀመመ - የነጠረም ስለነበረ አገርን በሙሉ ክብር ልዕልና ልቅና #በደግነት #ቀመር የሰጡን።  ለሰው ልጅ አገር ከመኖር በላይ ምን #የሐሤት #አውታር ይኖረዋል? ለዛውም "ከእነ እምዬ፤" ለዛውም "ከእነ ማር።"  ሥርጉትሻ2024/07/19

#ሸር #አረም ነውና።

  #የህይወት #ልምድ በሥማ በለው ሳይሆን ሕይወቱን ስትኖርበት የሚገኝ #ምርቃት ነው።  የሕይወት ልምድን የሚያጋሩ #ቅኖችም #በሸር ውስጥ አለማለፋቸውን በቅድሚያ ከራሳቸው ጋር ሊመክሩ ይገባል።  #ሸር #አረም ነውና። አረም ሲበቅል ደግሞ #ሰብል #ስለሚጫጫ ። በተጨማሪም የልምድ ልውውጥ ተብሎ #ውርስ #ሸር እንዲሆን እማንፈቅድም አለን እና።  ንጽህና የፆታ ድንግልናን ብቻ ሳይሆን #የመንፈስ #ፀዓዳነትን ይጠይቃል። የሕይወት ልምድ እንዲያጋሩ የሚጠዬቁ ሰብዕናወች በሂደታቸው #ሸር አለመኖሩን ጠያቂውም // ተጠያቂውም ሊያረጋግጡ ይገባል።  ሥርጉትሻ 2024/07/19