መሪነት የህይወትን ማህደርነት መመርመር አለበት ስል ...

  

 መሪነት የሕይወት #ማህደርነትን መመመርን ይጠይቃል። ሕይወት በዥንጉርጉር ቀለማት ህብረ ዝማሬ የቆመች ናት። 

ስለዚህ አክብሮ ተነሰቶ ማድመጥን ይጠይቃል። ሕይወትን ግርግር ማድረግ የመሪነትጥራት አይደለም። 

ሕይወትን ርጉ እና የማህበረሰቡን የቀደሙ ልማዶችን ፈጥኖ አለመዳፈርን ይጠይቃል። ስክነት።


ሥርጉትሻ 2024/07/19

 

መሪነት የህይወትን ማህደርነት መመርመር አለበት ስል የዛሬውን ብቻ ሳይሆን፤ የማህበረሰቡን የቀደሙ ማንነትን መስታውት መሆኑን አምኖ በቅንነት መቀበል ይገባል። 

የትላንቱን - ከዛሬ፤ የዛሬውን - ከነገ ጋር በማጣጣም እና በማገናዘብ የተሻለ የሕይወት ጎዳናን ማመላከት ይጠበቅበታል። 

ዕውነት ውስጥ ሆኖ ዛሬን ተሻግሮ ነገን ለማኖር የአቅም #ጥሪትም ሊኖረው ይገባል። 

በዚህ አመክንዮ ትናንት #ዛሬን ስለሰጠው ዛሬ ላይ ተቀምጦ ትናትን መውቀስ፦ መንቀስ እንዲያም ሲል የትናንትን አበርክቶ #መደፍጠጥ አይገባም።

 ለዛሬ እርሾው ትናንትን አልቦሽ ዛሬ ዬለም። ፍላጎቱ ተንሳፋፊ እና #ትንታበትንታ ይሆናል። የታነቀ ህቅታ። 

የብዙ ውድቀቶች መሠረቶችም እርሾ አልቦሽ ጉዞ ነው ለብላሽ ገብያተኝነት የሚያጋልጠው። 

ሥርጉትሻ2024/07/19

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።