#ተናኘ።

 

መንፈስህ ይጠራኝ ዘንድ ተማፅኜ
ከአንተ ጋር እዘልቅ ዘንድ ተጠሙኜ
ባላዬሁሽ እንዳታልፈኝ ተንበርክኬ
ለምኘ አባብዬ
ስለአንተ ለመኖር ቃል ገብቼ
እራሴኑ ሞግቼ
እንሆ ረትቼ፤
ዝንፍ ላል አንተን ተማምኘ
ጋሻ ጥላዬ ብዬ
ጥማትህ ራሃብህ ----------------------- #ተናኘ
ጥሪህ ይምረኝም ዘንድ ፀልዬ
ርህርህናህ ስቦኝ ቢማርከኝ
ምን ይደንቅ አንተዬ?
ዕፁብ ድንቅ ልዩ አዋዬ
መካሪዬ!
ሰባዕዊነት - ደግዬ
ተፈጥሯዊነት - መልካምዬ
የጽናት ፅዋዬ
የአደራ የእምዬ
የአሻራ የተክልዬ።
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
19/07/024
ሰዓት 13.10
ሰባዕዊነት ይመስጠን።



አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።