ነፃነት
አንድ ሰው ሰብዕናው ሲመዘን ምን ያህል ዕውነት በእሱ ላይ አድሮ ዕውነት ዕውን ሆኗል ከሚል መነሻነት ሊሆን ይገባል። ይህንን የሚደፍሩ #ነፃነታቸውን በውል ፕራክቲስ ያደረጉ ሰብዕናወች ናቸው። ነፃነት ጋር የተዋወቁ ሰብዕናወች ቅጽበታዊነት #ዝር አይልባቸውም።
ቅጽበታዊ አክሽን ለትወና መልካም ነው፦ የጥበቡም ቤተኛ ነው። መደበኛ ሕይወት ለሚመራ ሰብዕ ግን ቅጽበታዊነትን የሙጥኝ ካለ በቅጽበት ውስጥ ብዙ ነገር ይናዳል። አብሶ ለዬትኛውም ደረጃ #መሪ ከተሆነ። ብዙ ምስቅልቅ ይፈጠራል። ምኞቴ እና ህልሜ #ቅጽበታዊ ሰብዕናወች ተከታይ እንዳይኖራቸው ነው።
ጎዳናው አጥፊ ስለሆነ። #ባልነቃው #ሕሊና ታቅዶ በደራሽነት ስለሚከወን የአደጋ ጊዜ #አበረካች ስለሆነ። ቅጽበታዊነት #አክ ሊባል የሚገባ ባህሬ ነው። ነፃ አስተሳሰብ የሚያራምዱ የሚደነግጡበት፤ የሚቻኮሉበት፤ የሚጣደፋበት ምንም ነገር ስሌለ ሰክነው አስበው እረግተው ይራመዳሉ።
ሥርጉትሻ 2024/07/19
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ