መሪነት ከማህበረሰብ ለመማር መፍቀድን ይጠይቃል እንጂ "ደንቆሮ" እያሉ ማህበረሰብን ማቃለል፤ ማጣጣል መሪነት አይደለም። ሳይለንት ማስ ዲስክርምኒሽንም ይቁም እላለሁኝ።

  ብዙ ጊዜ "#ደንቆሮ" የሚለውን ቃል የሚደፍሩ ሰብዕናወች ይገርሙኛል። እነሱ ተፈላስፈው ወይንም ተጠበው ዓለምን #ከውችንፍር ያዳኑበትን የእውቀት ጥግ ቢያሳዩን ምንኛ ባደነቅናቸው ነበር። 

አንድ ስብስብ መምራት እያቀተ ሲፈርስ //ሲሰራ ለሚውል #የአቋም #አክሮባቲስትነት ላይ ተፈናጦ እግዚአብሄር፤ አላኃችን በአምሳሉ ለምስግና የፈጠረውን የፍጥረት አውራ የሰው ልጅን ሰርክ " "ደንቆሮ/ ደንቆሮወች" እያሉ ሲዳፈሩ #ቅጭጭ አይላቸውም። አይፀፀቱም ይቅርታም አይጠይቁም።

 #መሪነት በዚህ ውስጥ ዕዳ ወይንስ ባላንጣ ለተፈጥሮም ለሰባዕዊነትም ብለን ጥያቄ እንድናነሳ እንገደዳለን። 

እግረ መንገዴን እምለው #ዝምታችን #ይከበር። ሳይለንት ማስ ዲስክርምኒሽንም ይቁም እላለሁኝ። 

ሥርጉትሻ 2024/07/19

 

መሪነት ከማህበረሰብ ለመማር መፍቀድን ይጠይቃል እንጂ "ደንቆሮ" እያሉ ማህበረሰብን ማቃለል፤ ማጣጣል መሪነት አይደለም። 

እንዲህ ያለ ሰብዕና አይደለም ለመሪነት #ለመመራትም ብቁ ነው ብዬ አላሰብም። እግዚአብሄር // አላህ በአምሳሉ የፈጠረው ፍጡር ለዛውም በወል እንዴት "ደንቆሮ" ይባላል። 

በግለሰብም ደረጃ ቢሆን የህግ ጥሰት ነው። አንጎልማ ድንቢጥም አላት። የሰው ልጅ ህሊና ስላለውም ነው ከእንሰሳት የሚለዬው።

 ታላቅ የፍጥረት ዓውራን "ደንቆሮ" ማለት #ምጥ እና #ዳጥ። የሆነ ሆኖ መሪነት #ከማህበረሰቡ #ለመማር መፍቀድን ይጠይቃል። 

#አክብሮ መነሳት። ይህ ማለት በማህበረሰቡ የህይወት #ውጣ #ውረድ ፈቅዶ #በንቃት መሳተፍ ይገባል።


ሥርጉትሻ 2024/07/19

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።