ልጥፎች

ከጁላይ 14, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ይገባቸዋል! ስፔኖች ኢንግላዶችን 2 ለ 1 እረተው ዋንጫዋን ቀብ አድርገዋል።

ምስል
  ይገባቸዋል! ስፔኖች ኢንግላዶችን 2 ለ 1 እረተው ዋንጫዋን ቀብ አድርገዋል። የገረመኝ የኢንግላንዶች ትካዜ ነው። ለዚህ እኮ ሊበቁ የሚገባቸው ቲሞች መራራ ስንብት አድርገዋል። በዕድል ትራንስፖርት በፔናሊቲ ትኬት ነው ለዋንጫ ውድድር የበቁት። ለዕድል ዕውቅና ሊሰጡ ይገባቸዋል ኢንግላንዶች። ስንት ስማርት የሆኑ ቲሞች ተሰናብተው እኮ ነው እነሱ ለዚህ የበቁት። ሁለተኛ ደረጃው ሎተሪ ነው የወጣላቸው። ልዑል ዊሊያም፤ ለዬት ብሎ ከተፈጠረው ልጃቸው ከልዑል ጆርጅ ጋር እንደ Das Erst ዘገባ 170 ሺህ ተመልካች በተገኜበት በበርሊን ስታዲዬም ተገኝተዋል። ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ነው። ከእምዬ ሲዊዝሻ ጋር በነበረው ውድድርም ተገኜተው ነበር። የስፔን ንጉሣዊ ቤተሰቦችም ተገኝተዋል። እነሱም ለድጋሚ ነው የተገኙት። ያቺ ጩጬ ሰሞኑን 17 ዓመት የሞላት ታዳጊ ድንቀነቷ የጉድ ነው። የመጀመሪያውን ጎል ያሰናዳች እሷ ናት። ስፔኖችኢንግላንዶችን እስከ 72 ደቂቃ ላይ አሯሩጠዋቸዋል። የኢንግላንዱ ግብ ጠባቂም ፋታ አልነበረውም። ነገር ግን 72 ኛው ደቂቃ ላይ ኢንግላንዶች ባገኟት ድል ለአቻነት ዘልቀው፤ ጥቂት ደቂቃወች ሲቀሩ ጨዋታው ሊራዘም ሁለተኛውን ደግመው ስፔኖች አሸናፊ ሆነዋል። ጥረዋል። ተግተዋል። ይገባቸዋልም። የጨዋታው አከፋፈት እጅግ ደማቅ፤ ግርማ ሞገስ የነበረው ነበር። እንደ እኔ ከመክፈቻው ይልቅ ዛሬ ጨዋታውም ሥርዓቱም ደማቅ ነበር። ልዕልት ድንቡልቡልም ስፔንሻን መርጣ ሽቶው ውኃ ነው እያሉ ሚዚወቿ ጎዳናዋን ወደ ስፔን ……… ታድላ ሁልጊዜ ሙሽራ። ጥሩ ጨዋታ ነበር። ማራኪም። የእኔ ውቦች ሥርዓቱ አልተጠናቀቀም። ደህና እደሩልኝ። ጩጨዋ ተሸለመች። ይገባታል። ኪንግ ናት። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 14/07/024 ኳሲት ለምልሚ የእኔ ውድድድድድድ። go...

ድማሚት።

ምስል

በይልነ - ዘለግ።

ምስል
·        https://www.lora.ch/programm/alle-sendungen?list=Tsegaye ·        https://www.facebook.com/sergute.selassie/ ·        https://sergute.blogspot.com/2021/02/blog-post.html?spref=tw

በነጭ ከበሮ ሥነ - ግጥም።

ምስል