ልጥፎች

ከጁን 24, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

"አሜን!"

ምስል
       አሜኑ!                „ፍቅርህ ከወይን ጠጅ ይልቅ መልካም ነውና። ዘይትህ መልካም ማዕዛ አለው፤                          ሥምህ እንደሚፈስ ዘይት ነው፤ ስለዚህ ደናግል ወደዱህ።“                        (መኃልዬ መኃልዬ ዘሰሎመን ምዕራፍ ፩ ቁጥር ከ፩ እስከ ፫) ሕይወት ነፍሷን ጠርታ፤ ተጣርታ መንፈሷን ንብ በዓውራው ሆኖ አስከፈተ በሩን። ውለላ ከማሩ ጥንግ ድርብ ለግሶ ተስፋ እዬዘመረ በጃኖ ቆምሶ እርገቱ ወረደ ማዕረጉን ተላብሶ። ማግሥት ተስልፎ አቋቋሙ አምሮ ነፍስ አባት ሆነለት ሥርዬትን አዳምሮ። ዝ ግ ባለው መንበር የውቅያኖስ እርገት ዝ ቅ ብለው ሲበሩ በዝማሬ እዕዋፋት ትውፊት ትሩፋቱ ዳርእስከዳር ስምረት። ጥጆች ሲቧርቁ በግርግሙ ብሥራት ሽምጥ ሲጋልቡ ታማኞች በአኃቲት በድብባ ስትመርቅ ወላድ የወግ ደርሷት ዛሬን ተነ ገ ላይ የሉላዊ ቅምረት። ዝልቅቱ በፍጥነት ርምጃን ጨምሮ ምጥቀት በብልሃት በጥበብ ተቃኝቶ „ መደመር “ አበራ ራዕይን አጉልቶ! „ ቃል “ ቀን ለገሰው በቅኔ ዘቃና ጉባኤ ውልደቱ ተሟልቶ ሁለንትና - ዛጉኤ፤ እቅፍቅፍ በሐመር፤ ጥላቻ በሰኔል ፍቅርም በሞገሱ፤ ክስመት  ➳ ለሳጥናኤል። ርትህ ባባንዱ ሚዛን በህሊና በህብርነት ፈክቶ የሰንደቅ ደመራ ቀደምቱ በ...

የደም ስንቁ።

ምስል
የደም ስንቁ። ከሥርጉተ© ሥላሴ 24.06.2018 ( ተማንጠግቦሽ ሲዊዝ) "የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ።"           (መክብብብ ምዕራፍ ፲፪ ቁጥር ፩) የሰው ስጋ ስንቁ፤ የሰው ደም አጥንቱ የሰው ደም ንጋቱ፤ የሰው ደም ርስቱ የሰው ደም ጥሪቱ፤ የሰው ደም ሐሤቱ። የሰው ደም ኩራቱ፤ የሰው ደም ልክፍቱ የሰው ደም አለቅቱ፤ የሰው ደም ጥረቱ የሰው ደም ጉሮሮው፤ የገዳይ ክርፋቱ። ዋ! አዲስ አባባ የአንቺ ቀን ውለቱ ጸሐይሽ ደመና በሲዖል ሽንፈቱ ሲኦሎች፤ በጋራ በስፋት በፍቅር ሸፈቱ። ሰው ለማለት ሆኖ እንዲህ፤ በአውሬነት ተስልቶ መኖር ባባዶኖት ዳምኖ ታጣፈቶ ለደም ጠማኝ ጥሪት ፍቅር ተሰውቶ። ተጣፈ በአሁኒት ደቂቃ 17.35 ሥጦታ ለደም ጥማት ርስተኞች ለእነ ማህበረ ደራጎን። የኔዎቹ ግጥም ካሰኛችሁ … እነሆ https://www.youtube.com/watch?v=3XasnG3Ena8&t=3397s ናፍቀሽኝ አገሬ። https://www.youtube.com/watch?v=76IFoT-5yrg&t=1583s አፈሬ ነው መስመሬ (23 06 2018) ኑሩልኝ እነ እማ // አባ ቅንዬ። መሸቢያ ጊዜ።  

ዳገቶ!

ምስል
ዳገቶ ከሥርጉተ© ሥላሴ 24.06.2018 ( ተአትጠገብ ሲዊዝ) ወዴት ታሰማራለህ? በቀትርስ ጊዜ ወዴት ትመስጋለህ። (መሃልዬ ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፯) በስርንቅ ታክሎ በስርንቅ ተባዝቶ በስርንቅ ተካፍሎ እሱ በእሱ ሆኖ ሾተል አግርሽቶ በጥርኝ ቀላልዶ ጉራማይሎ ዘፍኖ ዥንጉርጉር ተጎምዶ በቁርሾ ጎርንቶ አንክርዳድ ተድሮ ወስከንቢያን ሰንጎ በዛር ኩፍኝ አውሬ ተማት ተደብቶ የደም ጥርኛ ናፍቆት ሲነስት ጎልብቶ ዘመን በቃህ በለው ጉልቱን ዳገቶ! ተጣፊ በዚችው ደቂቃ 17.15 የኔዎቹ ግጥም ካሰኛችሁ … እነሆ https://www.youtube.com/watch?v=3XasnG3Ena8&t=3397s ናፍቀሽኝ አገሬ። https://www.youtube.com/watch?v=76IFoT-5yrg&t=1583s አፈሬ ነው መስመሬ (23 06 2018) ኑሩልኝ እነ እማ // አባ ቅንዬ። መሸቢያ ጊዜ።

የኔ ሰው ተፋቶ።

ምስል
       ቃ ከሥርጉተ© ሥላሴ 24.06.2018 (ተፍቅርተ ሲዊዝ) „የጣሪያችን መዋቀሪያ ዛፍ ነው።“ (መሃልዬ ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፲፯) ሲመጡ ሲሄዱ ሊያመልጡ ሊልጡ የመለበጥ ቁሮ ቃ በል ተላላጦ በመሸቢያ ድሮት እንትኑ ተቁላልቶ በምንትሶ ቅብጥርስ እንቶ ፈንቶ ደርቶ በግልበጣው ሌጦ ችካል ተቸክሎ በመቸኰል ኩሉ ፍጥርጥር ተቆላልቶ ተዚያም ተዚህ ሆኖ፤ የኔሰው ተፋቶ በክር ዝምዝማ ሙጥኝ መሰላል ተባጅቶ በከረክር አቅበት ማቃተት ተድሮ በበረዶ ክምር ባሎን ተደርድሮ በሚዛን ሲለካ ምና ተምን ተላክቶ? ሥጦታ ለቅብርጥስ ማህበር። ተጣፈ በአሁኒቱ ደቂቅ ተሰጠ ለእንቶ ፈንቶ ማህበር። የኔዎቹ ግጥም ካሰኛችሁ … እነሆ https://www.youtube.com/watch?v=3XasnG3Ena8&t=3397s ናፍቀሽኝ አገሬ። https://www.youtube.com/watch?v=76IFoT-5yrg&t=1583s አፈሬ ነው መስመሬ (23 06 2018) ኑሩልኝ እነ እማ // አባ ቅንዬ። መሸቢያ ጊዜ።

ምን ተማን?

ምስል
ምን ተማን? ከሥርጉተ© ሥላሴ 24.06.2018 (ተፍቅርተ ሲዊዝ) „ትእግስት ታላቁን ሃጢአት ጸጥ ያደርጋል እና …“    (መጽሐፈ መክብብ ምዕራፍ ፲ ቁጥር ፲፬ ) ምን ሲሉ ሲሆኑት ምን ይሁንም ሲሉት ምን ልብልም ሲሉት ልብልን ሲስሉት ምን ይሆናል ሲሉ ሊሉት ሊሰልሉት ምን ተሆነ ብለው አባብለው ሊቀልቡት በበቀለው አፈር አለበቅልም ሊያዋልዱት በበቀለው ፍሬ አልኖርም ሊያቃቡት በበቀለው ትንኝ ዘር ገብያ ሊያማርቱት ኮተት እንቶኔ በወጉ ሊልጡት። ከውስጥ በመላውም መላላ አጉርቶ ቀን ሲመሽ ሲነጋ ኩላሊት ተጎታቶ መጎተት ሲባዛ ገመዱ ተሰልቶ በስሌት ልግመኛ ቀን ከሌት ተሴርቶ መውደቅ ተደርድሮ ውድቅት ተፈታቶ በመፈታት ቀምር መጋባት ተቃኝቶ በልብ አልባ ኩፍኝ ፒኒስል ተውግቶ በውጋት ማህበር ማን ተማን ተለይቶ ? ተጣፈ በአሁኒት … ተደቂቃ 24.06.2018 ተሲዊዚሻ። ሥጦታ ለነምኖ።   የኔዎቹ ግጥም ካሰኛችሁ … እነሆ https://www.youtube.com/watch?v=3XasnG3Ena8&t=3397s ናፍቀሽኝ አገሬ። https://www.youtube.com/watch?v=76IFoT-5yrg&t=1583s አፈሬ ነው መስመሬ (23 06 2018) ኑሩልኝ እነ እማ /// አባ ቅንዬ። መሸቢያ ጊዜ።

አይሆኑ ሆነ

ምስል
አይሆኑ ሆነ የፓናማው ባለቀይ ማልያ፤   ከሥርጉተ ሥላሴ 24.06.2018 (ከውቢት ሲዊዚና።) „ዳዊት በእግዚአብሄር አመነ፤ በሱ አምኗልና መጠጊያ ሆነው፤ ከንጉሡ ከሳዖልም እጅ አዳነው። መጽሐፈ መቃብያ ቀዳማዊ“                      (ምዕራፍ ፳፩ ቁጥር ፩) ዛሬ ትንሽ ነፋሻ ትንሽ የተመጠነ ብርሃናማ ዕለት ነው። ያው የትናንትናው ደመመን ለቀቅ ቢያደርገኝም፤ ግን ጨርሶ አልተለቃለቀም። ትናንት ዝግት አድርጌው የዋልኩት አሁን ከፈት አድርጌ ሳይ ENG // PAN ግጥሚያ ላይ ነበሩ።  መቼም በመደለቅ ሠርግ እና መልስ የሚያሰኛት ድንቡልቡሊት ዛሬ እስኪበቃት ይወቃታል የተፈጠረችበት ባዕት። እልልታዋን እዬኮመኮመች ከአንዱ ወደ አንዱ ስታሽካካ የመጀመሪያው የዎህታ ክፍለ ጊዜ 5 ለምንም በሆነ ውጤት ተሸኘ ጉድ አልን እኔ እና ዓይኔ… ጤባ ጢቦ አይነት ነበር ... ህም ስንል ቆያተን ከእረፍት መልስ 45 1/ 2// 3/ እዬአለ መደመር ሲደመር ሌላ 6ኛው ድል ከች። ያው ጠይም በብዛት በርከት ብሎ በታዬበት የሁለቱ ቡድን የዛሬ እልፍኝ እንግሊዞች የጠይም ዕንቋችን ቤተ መንግሥት ገብታ የምሥራቹን መላክ አለብን ብለው ሞጥረው እዬተጉ ነው። በዚህ ዓመት የፍቅርን የመቻቻል አብነት በመሆን ጠልፈው እልልልልል አስኝተውናል። የዛሬንስ ማን ክፉ ብሎት ብዬ ተግቼ ተከታተልኩት። እጄ ይጥፋል ግን ዓይኔ ሜዳው ላይ ጠላዋ እንዳመረላት ሴት ወክ እንዲህ ይላል፤ እኔስ ጠላዬ አምሮ የለ ለነገሩ። የሞገትኩለት የፍሪካዊነት ሐዋርያ የአፍሪካ የሰላም እጬጌ ሆኖ ...

ልብጥ ልብስ በሽበሽ።

ምስል
የሥም ቅያሬ የማንነት ልብጥ ልብስ በሽበሽ። ከሥርጉተ © ሥላሴ 24.06.2018 (ከድንቂት ሲዊዚት።) „ምር ብለህ አልቅሰለት፤ አጽንተህም እዘንለት እንደ አገሩም ግዕዝ  አንድ ቀን ሁለት ቀን  አልቅስለት“ (መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ  ፴፰ ቁጥር ፲፮)  መቅድም።  እንጠብቃል ከእነ እንቶ ፎንቶ ከሞቀው እዬሄደ ከሚጣደው መንፈስ አዲስ ሥያሜ። አሁን ይህን ጊዜ ስሌት በስሌት ነው። እስከ አሁን እንኳን አተረፈልን ስልክም ተደውሎ ይሆናል? አይተፈር? ከረባትህን አዥጎርጉረህ በወደቀው ፖለቲካህ ውስጥ ነገ ደግሞ ጠጋ ብለህ ወይ ውጠህ ወይ በትንህ ስታምስ ትገኛለህ። የተፈጠርክበት ከወዴት ሲለቅ … ሆድ ዕቃ። አንዱን ተፎካካሪ ከሌላው ጋር እያሳመስክ እና በደቦ ሴራ እያራከስክ ማህበራዊ መሰረቱን እዬነቃቀልክ አንተ ደግሞ አቤቶ እንቶኔ አዲስ የውህድት በለው የጥምረት፤ የጥምረት በለው የቅብጥርሴ ምንትሶ ታዳቅላለህ፤ እናማ አዳቅለህ ደግሞ ከች ነው። መቼስ ማተብ ብሎ ነገር አልሰራለህ፤ አልፈጠረለህ፤ አልኖረበህ ለነገሩ ከአንተ በውሸት ድሪቶ ከተጠቀለልከው የቦንዳ ጥቅል ምን ጥሎት ሚዛን እና ማተብ ህሊናና ችሎት ዘው ሲል። እነ አቤቱ ልብጦ አሁን አደጋ በደረስ ደቂቃ አንተ ነህ የተጎዳን ለማዬት ሆስቢታል የምትሄደው? ድንቄም። ከስንት ሞት የተረፉ፤ ከእስር የተረፉ፤ ሰው የማይችለውን መከራ ተሸከመው ራሳቸውን ቆጥበው እና ከድነው የኖሩ ወገኖችህ ለጭብጨባህ እና ለሽብሸባህ ስታዘግም ትዝ ብለውህ የት አውቀው እና? እስቲ ተጠዬቅ። ቀድሞ ነገር የኤርትራ የነፃነት ቀን አንድም ቀን አለመታደመህ ተጠይቅ ተብለህ እኮ አታውቅም ቀኗ ስትደርስ በዬዓመቱ ሹልክ ነው አቤቱ ሹልክቶ? ...

እነ አዛኝ ቅቤ አንጓች።

ምስል
እነ„አዛኝ ቅቤ አንጓች።“ ከሥርጉተ  ©  ሥላሴ 24.06.2018 (ከገዳማዊቷ - ሲዊዘርላንድ።) „እሳት በረድ ረሃብ ቸነፈር ይህ ሁሉ ሊበቀሉበት ተፈጠረ። የምድር እባቦች ጥርስ ጊንጥ እፉኝት ይህ ሁሉ ሊበቀሉት  ተፈጠረ፤  ጦርም ሃጢያተኞችን ታጠፋቸው ዘንድ ተዘጋጀች። እሱ ግን በይቅርታው ደስ ያሰኛል፤ ያለመንም ፈቃድ  ያዘጋጃል።  ሁሉም የሚሞትበት  ዓት በደረሰ ጊዜ ከጊዜው አይልፍም። („መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፴፱ ቁጥር ፴፩“) ይገርም? እነ አዛኝ ቅቤ አንጓች ምን እና ምን እየሆኑ ይሆን፤ የሆነ ሆኖ ይህ የቃለ ወንጌል አምክንዮ ይህ ጥቅስ ለወያኔ ሃርነት ትግራይ ብቻ ሳይሆን በቅዱሱ አብይ መንፈስ ላይ አድሞ ቦንብ ሲወረውር የባጀው ከሊቅ አስከ ደቂቅ የማንፌስቶ ጣዕት አማልአኪውን ሁሉ ይመለከታል። ወደ ሌላው ከማንከባለል በፊት ራስን መግዛት ስለሚጠይቅ። ስለሆነም ድንቡልቡሉንም፤ ጠፍጣፈውንም፤ ዲያጎናሉንም፤  ልሙጡንም፤ ኮረኮንቹንም፤ ቡላማውንም ሁሉንም ያለበት ይበንበት ይሁን ተብሏል ... ዕውነትን መድፈር የ ዓለም አቀፉን አንጋፋ ጋዜጠኛ የብርቱውን የጋዜጣኛ አለምነህ ዋሴን ብሂል ልዋስ እና "የሞኞቹ" ጋዜጠኛ ተልዕኮ ነው። የወርቀት ጣዕት አምላኪ ላልሆነው የነጠረው ሃቅ ይኸው ነው ... የኢትዮጵያ እናቶች ዕንባ ለቀይ ምንጣፍ ምኞተኞች ሁሉ ጉዝጓዙ ነው ...  ተዘርዘር። ተመስገን ይባል ያደርግልን ልበል የቱ ይሻላል? ቃሉን ለመጻፍ እንደ ዕውነት እንደሚያርዳቸው ስንኩሎች ዛሬ ቸገረኝ። የኢትዮጵያ ህዝብ ፍቅር ባይሆን ኖሮ እንዲህ መሸቶ ይነጋ ነበርን? የጠፋው የፍቅርን ተፈጥሮ መርህ የሚመራ መሪ በሌለበት፤ ሙሴ በሌላበት በ አገር ውስጥ ይሁ...