የደም ስንቁ።
የደም ስንቁ።
ከሥርጉተ© ሥላሴ 24.06.2018 ( ተማንጠግቦሽ ሲዊዝ)
"የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ።"
(መክብብብ ምዕራፍ ፲፪ ቁጥር ፩)
የሰው ስጋ ስንቁ፤ የሰው ደም አጥንቱ
የሰው ደም ንጋቱ፤ የሰው ደም ርስቱ
የሰው ደም ጥሪቱ፤ የሰው ደም ሐሤቱ።
የሰው ደም ኩራቱ፤ የሰው ደም ልክፍቱ
የሰው ደም አለቅቱ፤ የሰው ደም ጥረቱ
የሰው ደም ጉሮሮው፤ የገዳይ ክርፋቱ።
ዋ! አዲስ አባባ የአንቺ ቀን ውለቱ
ጸሐይሽ ደመና በሲዖል ሽንፈቱ
ሲኦሎች፤ በጋራ በስፋት በፍቅር ሸፈቱ።
ሰው ለማለት ሆኖ እንዲህ፤ በአውሬነት ተስልቶ
መኖር ባባዶኖት ዳምኖ ታጣፈቶ
ለደም ጠማኝ ጥሪት ፍቅር ተሰውቶ።
- ተጣፈ በአሁኒት ደቂቃ 17.35
- ሥጦታ ለደም ጥማት ርስተኞች ለእነ ማህበረ ደራጎን።
- የኔዎቹ ግጥም ካሰኛችሁ … እነሆ
ናፍቀሽኝ አገሬ።
አፈሬ ነው መስመሬ(23 06 2018)
ኑሩልኝ እነ እማ // አባ ቅንዬ።
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ