አይሆኑ ሆነ

አይሆኑ ሆነ የፓናማው ባለቀይ ማልያ፤  

ከሥርጉተ ሥላሴ 24.06.2018 (ከውቢት ሲዊዚና።)
„ዳዊት በእግዚአብሄር አመነ፤ በሱ አምኗልና መጠጊያ ሆነው፤
ከንጉሡ ከሳዖልም እጅ አዳነው። መጽሐፈ መቃብያ ቀዳማዊ“
                     (ምዕራፍ ፳፩ ቁጥር ፩)


ዛሬ ትንሽ ነፋሻ ትንሽ የተመጠነ ብርሃናማ ዕለት ነው። ያው የትናንትናው ደመመን ለቀቅ ቢያደርገኝም፤ ግን ጨርሶ አልተለቃለቀም። ትናንት ዝግት አድርጌው የዋልኩት አሁን ከፈት አድርጌ ሳይ ENG // PAN ግጥሚያ ላይ ነበሩ።

 መቼም በመደለቅ ሠርግ እና መልስ የሚያሰኛት ድንቡልቡሊት ዛሬ እስኪበቃት ይወቃታል የተፈጠረችበት ባዕት። እልልታዋን እዬኮመኮመች ከአንዱ ወደ አንዱ ስታሽካካ የመጀመሪያው የዎህታ ክፍለ ጊዜ 5 ለምንም በሆነ ውጤት ተሸኘ ጉድ አልን እኔ እና ዓይኔ… ጤባ ጢቦ አይነት ነበር ...

ህም ስንል ቆያተን ከእረፍት መልስ 45 1/ 2// 3/ እዬአለ መደመር ሲደመር ሌላ 6ኛው ድል ከች። ያው ጠይም በብዛት በርከት ብሎ በታዬበት የሁለቱ ቡድን የዛሬ እልፍኝ እንግሊዞች የጠይም ዕንቋችን ቤተ መንግሥት ገብታ የምሥራቹን መላክ አለብን ብለው ሞጥረው እዬተጉ ነው።

በዚህ ዓመት የፍቅርን የመቻቻል አብነት በመሆን ጠልፈው እልልልልል አስኝተውናል። የዛሬንስ ማን ክፉ ብሎት ብዬ ተግቼ ተከታተልኩት። እጄ ይጥፋል ግን ዓይኔ ሜዳው ላይ ጠላዋ እንዳመረላት ሴት ወክ እንዲህ ይላል፤

እኔስ ጠላዬ አምሮ የለ ለነገሩ። የሞገትኩለት የፍሪካዊነት ሐዋርያ የአፍሪካ የሰላም እጬጌ ሆኖ ኢትዮጵያን ቦግ አድርጎ የለ፤ ብርሃኑ የፍቅራዊነት ንጉሥነቱ ለቁጥር በሚያታክት ደግነቱ እና ምህረቱ የረገጠው ድርቆሽ ሁሉ ሲለመልም እዬታዬ ነው እንደ አሮን በትር።

ውስጠ ንጹህ የፖለቲካ ሊሂቅ ኢትዮጵያ ስጥቷት ዘመነ መጽናነት በምህረት እና በፍቅር እዬወረበው ነው። ፈተና ያለ የነበረ ቢሆን አሁን የበለጠ ሊያጠነክረው እንደሚችል ተስፋዬ ሙሉ ነው። መንፈሱ አብዝቶ ቅን ሰለሆነም ትንሽዬ እንዲጠራጠር ዕድሉን አግኝቷል።

ስለዚህ ጠንቃቃ ይሆናል። ይሄም አለ ለካንስ ድንግልዬ የእኔ ኪዳነምህረት በዕለተ ቀኗ ነግራዋለች።

እነፓናማ ዘግየት ብለው ለማስተዛዘኛ አንዲት አስቆጠሩ እና 6 ለ 1 በሆነ ውጤት ጠሐይ አይጠልቅብሽም የተባላቸው አገረ ለንደን ፍንክንክ ብሎ ቀጣዩን የሠርግ እና የምልስ ቀጠሮ በሐሤት ቆጣጣሯል።

ፍቅር ከነተፈጥሮው ከተፈጠረበት ጋር ስለሆነ እትዬ ድንብዩልቡልም ዛሬ አዲስ ፍቅረኛ አላማረኝም ብላ ወደ ባዕቷ አዳላታ በእትብተኞቼ ስደልቅ፤ ስተወቃ ከብለል እያለች ስትፈነዳደቅ የበለጠ ድምቅ፤ የበለጠ ፍክት፤ የበለጠ ሐሤት አገኛለሁኝ ብላ ፍልቅልቅ ብላላች ሳቋ ዱሏ፤ ፍቅሯ ዱላ፤ ተስፋዋ ዱላ በቃ ለዱላ የተፈጠረች ፍቅርተ።

የእኛ የፍቅራዊነት መንፈስም አሸናፊነቱ አይቀሬ ነው። ምን ፈተናው፤ ምን ብክነቱ፤ ምን መባተሉ ቢበረክትም ድሉ ሳይታለም የተፈታ ነው። የጀርባ አጥነቱ የሚሊየኖች ድምጥም ማህተሙን ተረገጡ በደሙ አክብሮ ድሉን በዕንባም በቁርጠኝነትም ውሎ ላይ አዋውሏል።

የፍቅራዊነት ዋና መለያው ሲኖሩበት ብቻ ያስውባል።
ስፖርት የሐሴት ህሊና ነው!


ኑሩልኝ የኔዎቹ ... መሸቢያ ጊዜ።  

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።