የኔ ሰው ተፋቶ።


   
   ቃ

ከሥርጉተ© ሥላሴ 24.06.2018 (ተፍቅርተ ሲዊዝ)

„የጣሪያችን መዋቀሪያ ዛፍ ነው።“
(መሃልዬ ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፲፯)



ሲመጡ ሲሄዱ ሊያመልጡ ሊልጡ
የመለበጥ ቁሮ በል ተላላጦ
በመሸቢያ ድሮት እንትኑ ተቁላልቶ
በምንትሶ ቅብጥርስ እንቶ ፈንቶ ደርቶ
በግልበጣው ሌጦ ችካል ተቸክሎ
በመቸኰል ኩሉ ፍጥርጥር ተቆላልቶ
ተዚያም ተዚህ ሆኖ፤ የኔሰው ተፋቶ
በክር ዝምዝማ ሙጥኝ መሰላል ተባጅቶ
በከረክር አቅበት ማቃተት ተድሮ
በበረዶ ክምር ባሎን ተደርድሮ
በሚዛን ሲለካ ምና ተምን ተላክቶ?
  • ሥጦታ ለቅብርጥስ ማህበር።
  • ተጣፈ በአሁኒቱ ደቂቅ ተሰጠ ለእንቶ ፈንቶ ማህበር።

  • የኔዎቹ ግጥም ካሰኛችሁ … እነሆ

ናፍቀሽኝ አገሬ።

አፈሬ ነው መስመሬ(23 06 2018)



ኑሩልኝ እነ እማ // አባ ቅንዬ።
መሸቢያ ጊዜ።



አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።