ልብጥ ልብስ በሽበሽ።
የሥም ቅያሬ የማንነት ልብጥ ልብስ በሽበሽ።
ከሥርጉተ© ሥላሴ 24.06.2018 (ከድንቂት ሲዊዚት።)
„ምር ብለህ አልቅሰለት፤ አጽንተህም እዘንለት እንደ አገሩም ግዕዝ አንድ ቀን ሁለት ቀን
- መቅድም።
እንጠብቃል ከእነ እንቶ ፎንቶ ከሞቀው እዬሄደ ከሚጣደው መንፈስ አዲስ ሥያሜ። አሁን ይህን ጊዜ ስሌት በስሌት ነው። እስከ አሁን እንኳን አተረፈልን ስልክም ተደውሎ ይሆናል? አይተፈር? ከረባትህን አዥጎርጉረህ በወደቀው ፖለቲካህ ውስጥ ነገ ደግሞ ጠጋ ብለህ ወይ ውጠህ ወይ በትንህ ስታምስ ትገኛለህ። የተፈጠርክበት ከወዴት ሲለቅ …
- ሆድ ዕቃ።
አንዱን ተፎካካሪ ከሌላው ጋር እያሳመስክ እና በደቦ ሴራ እያራከስክ ማህበራዊ መሰረቱን እዬነቃቀልክ አንተ ደግሞ አቤቶ እንቶኔ አዲስ የውህድት በለው የጥምረት፤ የጥምረት በለው የቅብጥርሴ ምንትሶ ታዳቅላለህ፤ እናማ አዳቅለህ ደግሞ ከች ነው። መቼስ ማተብ ብሎ ነገር አልሰራለህ፤ አልፈጠረለህ፤ አልኖረበህ ለነገሩ ከአንተ በውሸት ድሪቶ ከተጠቀለልከው የቦንዳ ጥቅል ምን ጥሎት ሚዛን እና ማተብ ህሊናና ችሎት ዘው ሲል።
- እነ አቤቱ ልብጦ
አሁን አደጋ በደረስ ደቂቃ አንተ ነህ የተጎዳን ለማዬት ሆስቢታል የምትሄደው? ድንቄም። ከስንት ሞት የተረፉ፤ ከእስር የተረፉ፤ ሰው የማይችለውን መከራ ተሸከመው ራሳቸውን ቆጥበው እና ከድነው የኖሩ ወገኖችህ ለጭብጨባህ እና ለሽብሸባህ ስታዘግም ትዝ ብለውህ የት አውቀው እና?
- እስቲ ተጠዬቅ።
ቀድሞ ነገር የኤርትራ የነፃነት ቀን አንድም ቀን አለመታደመህ ተጠይቅ ተብለህ እኮ አታውቅም ቀኗ ስትደርስ በዬዓመቱ ሹልክ ነው አቤቱ ሹልክቶ?
መቼ ነው እያወረደ በዬዘመኑ ከሚፈርጥህ ከሚያንዘላልጠው ስውር የልግመኛ ፖለቲካ ስነሰለትህ በጥሰህ ወጥተህ ተዝቆ በማያልቀው የዕውቀት የሊቀ ሊቃውንት ሳይንትስትነት መክሊትህ ደምቀህ እምታዳምቀን? ግን መቼ? መቼም ሳይንስ እና እውነት ደርብ እና ምድር ሳይሆኑ ሴል እና ደም ናቸው።
የእውነት መንበር ህግጋት ጋር እርቀ ሰላሙ የሚወርደው ከቶ መቼ ይሆን? አሁን ደግሞ ፎቶውን ላክለት ለጎንደር „የነፃነት ሃይልህን“ አባወራ። መሳቂያ! …
- ኡኡ! የእፍረት ያለህ!
ኡኡ! የእፍረት ያለህ! ብለንልሃል። መንፈሱን ለመግዛት ግን እንደማትችል አስረግጬ እነግርሃለሁኝ። ሥርጉተ እኮ አደራጁ ናት። ሙሉ ወርዱን ወይንም ጃኖውን ሳይሆን የባዕቷን ልበ ህሊናውን ታውቀዋለች መድረክ ጠማኝ በመሆን ሳይሆን ወገቧን በድርብ መቀንት ጠበቅ አድርጋ የዳዝን አቀበት እና ቁልቁለት የጫቆን፤ የአዳኝ አገር፤ የዳዋን፤ የመጋን የስንቱ ይጠቀሳል ወጥታ ወርዳ የአደራጀች ናት። ለዚህ ነው ዳንኪራ የማያሰኛት… ልቅልቅ እና ልብጥን የምትጸዬፈውም ተረገጡ ይሄው ነው።
ድንቄም! እቴ የአማራ ተጋድሎ አርበኛ አለንልህ¡ አርኬብህን እዬው ፈትሸው፤ ጎንደር አንተን ከእንግዲህ ሊቀበል? አትሞክረው። ውልቅልቁን ነው የምናወጣዋ። የወረቀት አምላኪ ማህበርተኛህ እንደ ተኮፈሰ ተክብሮ ቢቀመጥ ይሻለዋል። ያለኝ ይበቃኛል ብሎ።
እዚህ እኮ እሰረኛ ጀግና አንበሳ አለን። ደጉ ቅዱሱ ብቁው ጠባቃ ሼክስፔር ፈይሳ መጥተው ጉዳዩን የእኔ ያሉለት የአንተውን ማህበርተኛ ትውር ሲል በመንፈሱ እኛ ግን አላዬነም፤ አልሰማነም። እዚህ ሲፎከር ሲዘከር ቀይ ምንጣፍ ሲነጠፍ በተረሳ ዙር ዘለበት በዘለበት ለማያያዝ ተብ እና ቸብ ሲባልለት ከትከት ብለን ስቀንበት ቁሞ እዬደሰኮረ ረግጠንለት ወጥተናል፤ ሃራም ተብሎም ...ለስተዘላዓለሙ ... ተፈረመበት።
ይልቅ ለአዲሱ ሥያሜህ መንፈሱ ቢጠጋህ „ኦ“ አስቀድም እና „አ“ን ለጥቅ እና፤ „ለ“ን አክል አና በአናባ አዋውለው፤ ያው መጣጋጋት መገፋፋት ክፍልህ ስለሆን። መቀነስ ሲቀነስ ሲጠጋጋ ይሆናል ምንም እንደሚሉት …
„ቀልድ እና ቁም ነገር“ አለ አቤ ቶኬቻው ይሄ ሥያሜ ትክክል ነበር ከሚዲያህ ከቤተ መንግሥቱ ጉብ ማለቱ። ውይ እኔን፤ ይቅርታ የቤተመነግሥቱ ሚደያ ለካ ህልም እልም ህልም እልም ሆኖ ቀርቷል፤ ብቻ ለዛ ዘመን አንቱ መባሉ ትክክል ነበር እንደ „ዕለታዊነት“ ሥም በመቀዬር በማፏጨት የሚሆን ነገር የለም። ድፈረው ቁጭ ብሎ ማሰብን። ድፈረው ህዝብን ማደራጀት በሸቀጥ ህግ አለመገዛቱን።
በሰው አሳብ እዬተንጠላጠሉ ምንትሶ ቅብጥርሶ ከምትለን። ህህህ ምን „አብረን መስራት?“ በዬትኛው ፖሊሲህ? ለዛውም አሁን ዘመኑ የግልጥነት ይሉታል። „ቂጥ ገልቦ እራስ ተከናንቦ“ ቀረ እኮ። በደም ንግድ ሥምን ማንገሥ የለም። ሥምን ማቀሰስ የለም። መናጆነት ቀረ „አሟራው በረረ ቅሉም ተሰበረ“ የሚል አዲስ ቅኔያዊ ክልፑን ላንተው ለአክሮባቲስቱ ሻላልሞ ብሎ መጪ ብሏልኝ እንቱኑ ዘመን … ተመስገን! ባትነካክን "ዝምታ ወርቅ ነው" ብለን ብንቀመጥ አይሻልህምን? ጎንደርን አማራን ረሳ ተወት አድርገው። ድሮም እኮ ተስሚን ወዲያ ማዶ ነው መንግሥት እምፈጥረው ብለህናል እኮ እና ታለወገነህ እንዴት ተብሎ፤ ለዚህም ነው ባተወለደ አንጀት ሞገድ ላይ ሥጋዎቻችን ስታዘለዝል የከራረምከው። ሌላውም በድል ማግስት ... ምን እና ምን እንደተሆነ ታይቷል።
- እኔ ግን ስለዛሬ
እነ ግን እስቲ ተጠመድ ይባል። ዝንፍ የሚል አማራ ከመጣ ደግሞ ይነገረዋል። ሰንሰለታችን ወፍ ዘራሽ ሳይሆን ተፈጥሯዊ እና መሬት የረገጠ ነው። …
ቃብቲያ ተጨፍጭፎ ቢሆን ኖረ አንተ ከዬትኛው መደብ ትምደብ ይሆን፤ „ከምህርት? ከፍቅር? ከይቅርታ?“ አትሰበው! ወያኔ ሃርነት ትግራይ እኮ መሬቱ ላይ ስላለ ብቻ ነው።
አንተ እኮ ያን ቅን ለቀን ያደረሰህን ህዝብ አሳልፍህ ለበላህስብ የሰጠህ ድርብ አንጀት ነህ። ህጻነትን፤ ነፍሰጡር እናቶችን ስለምን ይሆን ያላዘንክላቸው? የእትብትህ ቤተኛ ስላልሆኑ? „በሞኝ ደንደስ በርበሬ ተወደስ።“
አማራ ተጋድሎ መሪ አለው ልቅላቂ ፍርፋሪ እንጥፍጣፊ አያሻውም ልጥፍ ቅብጥርሶ ክፍሉ አይደለም። የኮራ ደልደል ያለ ልቡ ሙሉ ጀግና/ ጀግኒት ወኔው ያልሾከበት/ ያልሾለከባት ደርባባ/ ደርባቢት መሪ አለው።
አማራ ተጋድሎ መሪ አለው ልቅላቂ ፍርፋሪ እንጥፍጣፊ አያሻውም ልጥፍ ቅብጥርሶ ክፍሉ አይደለም። የኮራ ደልደል ያለ ልቡ ሙሉ ጀግና/ ጀግኒት ወኔው ያልሾከበት/ ያልሾለከባት ደርባባ/ ደርባቢት መሪ አለው።
የአማራ የተጋድሎ ልዕልና በመሬቱ አለ የአንተ „የነጻነት ሃይል“ ታንቡርህ ደግሞ ተንበርክኮ ለምኖ ፎቶ ለጥፉልኝ ይማጸን... የተኖረ የመንፈስ ጥሪት የለም። ወና!
- የእኔ ዓለሞቼ እስቲ ይከውን
ይሄ አባሎቻቸው በግፍ እና በማን አለብኝነት ተዝርፎ አገርቤትም ዕውቅና እንዳያገኙ ታድሞባቸው ግን የእውነት አርበኞች ለነበሩ፤ ግጥሜም የልቤም ለነበሩት ሁልጊዜም ድፍረታቸው እና ልባዊነታቸው ለሚመናፍቁኝ ለሲዊዝ የአንድነት የድጋፍ ድርጅት አንዳንድ ቴክኒካዊ ነገሮችን አስተካክለው ሸጠው እንዲጠቀሙበት በሚል ውሰዱት ብያቸው ግን ሳይችሉ ቀርተው የተቀመጠ የግጥም ሥብስብ ነው።
ሁልጊዜም እንደምለው ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ስለሆነ በትናንትናውም ዕለትም አብክሬ እዬተነጋርኩኝ ሰሚ አጥቼ ያ አደጋ ቢፈጠረም፤ የኢትዮጵያ እናቶች ዕንባ አሁም ለማቆም አለመቻሉ ቢያርመጠምጠኝም ግን ኢትዮጵያዊነት በፍቅር ነጥሮ የወጣበት ቀን ስለነበር ጭንቅ ላይ ስለነበርኩ ሌት ቁጭ ብዬ አድሬ ነበር ፖስት ያደረኩት አዳምጡልኝ የእኔ የቅንነት ወተቶች።
ማስተካከያ አልስፈለገውም። በነበረው ከእነ ተጠፈጥሮ መቅረቡ ዘመኑን በባህሬው ስለሚገልጸው።
ማስተካከያ አልስፈለገውም። በነበረው ከእነ ተጠፈጥሮ መቅረቡ ዘመኑን በባህሬው ስለሚገልጸው።
ሁሎቹም ግጥሞች በሦስቱ የሥነ ግጥም መጻሐፍቶቼ „በተስፋ፤ በመክሊት እና በውል“ ውስጥ ያሉ ናቸው። ያው እና አቤቶ የድል አጥቢያ አርበኞች አሳግደውት ስቶር ያሞቃሉ ... ከዘመዳ ዘመዱ ቀሪ አራት መጸሐፍት ጋር እንደ ፈረደባቸው
ግጥሞቹ … በዲዛይን የተሠሩ ሥነ ግጥሞችም ናቸው። በዓለም አቀፍ ደረጃ አዲስ የአሰራር ፈጣራ ነበር ዕድሜ ለእንቶ ፈንቶ ጓጓላሞች - በእነሰ ምክንያት ታሽገው ቀሩ ...
ግጥሞቹ … በዲዛይን የተሠሩ ሥነ ግጥሞችም ናቸው። በዓለም አቀፍ ደረጃ አዲስ የአሰራር ፈጣራ ነበር ዕድሜ ለእንቶ ፈንቶ ጓጓላሞች - በእነሰ ምክንያት ታሽገው ቀሩ ...
"አፈሬ ነው መስመሬ"(23 06 2018)
ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።
ኦህዴድ ጭንቅላት ብቻ ሳይሆን ብቁ አዕምሮ አለው።
ኑሩልኝ የእኔ ልባሞች።
መሸቢያ ጊዜ።
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ