እነ አዛኝ ቅቤ አንጓች።

እነ„አዛኝ ቅቤ አንጓች።“
ከሥርጉተ © ሥላሴ 24.06.2018 (ከገዳማዊቷ - ሲዊዘርላንድ።)

„እሳት በረድ ረሃብ ቸነፈር ይህ ሁሉ ሊበቀሉበት ተፈጠረ። የምድር እባቦች ጥርስ ጊንጥ እፉኝት ይህ ሁሉ ሊበቀሉት 
ተፈጠረ፤ ጦርም ሃጢያተኞችን ታጠፋቸው ዘንድ ተዘጋጀች። እሱ ግን በይቅርታው ደስ ያሰኛል፤ ያለመንም ፈቃድ 
ያዘጋጃል። ሁሉም የሚሞትበት  ዓት በደረሰ ጊዜ ከጊዜው አይልፍም። („መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፴፱ ቁጥር ፴፩“)

  • ይገርም?

እነ አዛኝ ቅቤ አንጓች ምን እና ምን እየሆኑ ይሆን፤ የሆነ ሆኖ ይህ የቃለ ወንጌል አምክንዮ ይህ ጥቅስ ለወያኔ ሃርነት ትግራይ ብቻ ሳይሆን በቅዱሱ አብይ መንፈስ ላይ አድሞ ቦንብ ሲወረውር የባጀው ከሊቅ አስከ ደቂቅ የማንፌስቶ ጣዕት አማልአኪውን ሁሉ ይመለከታል። ወደ ሌላው ከማንከባለል በፊት ራስን መግዛት ስለሚጠይቅ። ስለሆነም ድንቡልቡሉንም፤ ጠፍጣፈውንም፤ ዲያጎናሉንም፤  ልሙጡንም፤ ኮረኮንቹንም፤ ቡላማውንም ሁሉንም ያለበት ይበንበት ይሁን ተብሏል ... ዕውነትን መድፈር የ ዓለም አቀፉን አንጋፋ ጋዜጠኛ የብርቱውን የጋዜጣኛ አለምነህ ዋሴን ብሂል ልዋስ እና "የሞኞቹ" ጋዜጠኛ ተልዕኮ ነው። የወርቀት ጣዕት አምላኪ ላልሆነው የነጠረው ሃቅ ይኸው ነው ... የኢትዮጵያ እናቶች ዕንባ ለቀይ ምንጣፍ ምኞተኞች ሁሉ ጉዝጓዙ ነው ... 
  • ተዘርዘር።

ተመስገን ይባል ያደርግልን ልበል የቱ ይሻላል? ቃሉን ለመጻፍ እንደ ዕውነት እንደሚያርዳቸው ስንኩሎች ዛሬ ቸገረኝ። የኢትዮጵያ ህዝብ ፍቅር ባይሆን ኖሮ እንዲህ መሸቶ ይነጋ ነበርን? የጠፋው የፍቅርን ተፈጥሮ መርህ የሚመራ መሪ በሌለበት፤ ሙሴ በሌላበት በ አገር ውስጥ ይሁን በውጪ ራሱን ለራሱ ተፈጥሮ ዘብ ሆኖ የኖረ ህዝብ እኮ ነው የ ኢትዮጵያ ህዝብ ማለት። ለዛውም በተደሞ፤ በ አርምሞ፤ ውጪ አገር ይህ ዕድል ቢፈቀድ ማን እንደሚወገዝ ይታይ ነበር የቤተ ዘመዱ። አሁንማ በጅምላ መደገፍ እና መቃውም ቀረ እኮ፤ እንደ አላገጡ መኖርም የለም።

ለነገሩ በስንት ዘመናቸው አቡነ ማቲዎስም ክህነተ ሥልጣናቸው ከተሰወረበት ዱብ ብሎላቸው ስለሰማዕቱ ያሉትን ብለውናል - ትናንት። ከተሾሙ ጀምሮ የሚፈሰው ደም የጥንቸል ነበርን? ሌላም ሰሞኑን የሃይማኖት መሪዎች ህሙማንን ሲጎበኙም ተመልክቻለሁኝ፤ እያንዳንዱ የሃይማኖት መሪ ኢትዮጵያዊ ሰው የሚባለው ፍጡር፤ ሉላዊ ህምም የሚባለው ክስተተ ተፈጥሮ አሁን ነው የተፈጠረውን?
ሌላ ሚደያው፤ አክቲቢስቱ፤ ተንታኙ በታኙ፤ ጋዜጠኛው፤ ዕወቅ ነኝ ባዩ በተለይም የማንፌስቶ ጣዖት አምላኪው በዬከተማው የሚካሄደው ሰልፍ ፎቶ አስለጥፎ ዘመዶቹን ከማሰውጣት ጀምሮ እንኳን አተረፈህ መሪያችን እያለም ነው።

እኛ ደግሞ ለድል አጥቢያ አርበኞች፤ ለውሸት ማህብርተኞች እንኳን በውሸት ውዳሴ ከንቱ የጠቅላይ ሚሩ ካቢኔ ህዝብ የሚወደኝ ስለመሆኑ ዐውቅና ስጠኝ ተብሎ ከሥር ተንበርክኮ ለመለጠፍ እንደ ልማዳችሁ አበቃችሁ ነው የምንለው። የከንቱ ውዳሴ ዳሰኞች … ስንት ቀን ተጠቅላላችሁ ትዘልቁት ይሆን?

ዛሬ የእናንተን ሚደያን ያዬ ሰው። ስለምን ስለ አንንገት የሚባለው ተፈጥሮ እናንተን ይሉኝታ ቢሶችን ሳይ እና ሳዳምጥ እንደመንኖሩ እንደተፈጠረም ሁሉ አይገባኝም። ግን ከአንገት በላይ ሰው አለን? ምስሉን አይደለም እኔ የምለው? ምስልማ ጥሩ ሳዕሊስ በረቀቀ የተፈጥሮ ክህሎቱ ይካነው የለ።
?
ዕውን ሰቀቀኑ ከሳዘነን ስለምን ይሆን ረብሻ እንዲቀጥል ስንተጋ የነበረው? ስናማሟቅ፤ ስነቀጣጥል ስለምንስ ይሆን በህሊና ጉባኤ ታድሞ በኦህዲድ እና በመሪዎቹ ላይ አድመን የከረመነው? ያ ሁሉ ዱላ ቦንብ መሆኑን ረስተነው ይሆን? ያ ሁሉ የሰላም ህውከት ፈንጅ መሆን ዳብ ብሎን ይሆን?

ሌላው ቀርቶ የደቡቡ ብጥብጥ በወያኔ አቅም ብቻ የተኮለ ወይንስ እኛንም ይደርበን ብለነው ይሆን? ለመሆኑ መቼ ነው ድራማው የሚያበቃው? እንደ ሰው ሰው መሆንስ የምንችለው?
በዬትብያው ላይ ያለው አቅም ተቀንቶበት የፌስ ቡክ መተንፈሻ ቧንቧ ተቀንቶበት፤ የብርና መተንፈሻ ቧንቧ ተቀንቶበት አሳግደን፤ አንገት ቆርጠን አስቆርጠን፤ የክት እና የዘውትር በምንለይበት ዕውቅና፤ አገር ምድሩን አራጠን ገዝተን፤ በጭቆና እና በአፈና  እዬነዳን አሁን በፍቅር ጉባኤ ላይ ፎቶ አስለጥፍን ስንወጣ አናፍርም?አይቀፍም? ህሊናን አይጨቀጭቅም?

ለዛው ከለማ፤ ከገዱ፤ ከአብይ መንፈስ ጋር እኩል ስንሰለፍ መዳፈር አይሆነም? አናፍርም? አይስቀጥጠንም? አቅሜ አይደለም አይገባንም አንልም? ወዮ! ዋሽንግተን ብቅ ብትል የተደራጀ ቡድን ከግባ ግቢትህ ገብቶ የአሻውን እንሚያደርግ ይህን ቅደመ ሁኔታ ተቀበል እያልን ገና አየር ላይ ባለ መንፈስ ስነታመስ፤ የስሜን አሜሪካው የስፖርት ኮሜት ገና ቢቀበለው ብለን መመሪያውን ጥሶ የአብይን የመንፈስ ግብዣ ከተቀበ ካስተናገደ ዋ! ብሎ ጦር እና ሳንጃ ሲደነክር የከረመ እኩይ የቅናት መንፈስ፤ ትግርኛ፤ ኦሮምኛ ቋኝቋ ተነጋረ ብሎ ዛሩ ተነስቶበት ሲንደፋደፍ የከረመ ሴረኛ መንፈስ፤ ኢትዮጵያ በአብይ ካቢኔ ሳይሆን በበረከት ኮሜቴ ቅራሪ ነው የምትመራው በማለት የተስፋን መንፈስ ሲያርድ የከረመ ድውይ መንፈስ በዬሰከንዱ ስለሚበትነው ቅናዊ የፍቅር ጉዞ መንፈስ ቅጭጭ ሳይላው አሁንም አሁንም ተንታኝ በታኝ ሲኮን አያታፈርም?

ትንሽ እፈረት ይሉኝታ የሚባል ነገር ያልጠፈለት የጉድ ጎቶ አሁንም አንደበት አለኝ ብሎ ሲንጠራራ አንገት የት ነው? ህሊናስ ባድማህ የት ተባለ? አያድርገው እና የ አብይ መንፈስ አንድን ነገር ቢኖር እውን ሊከፋን፤ ልናዝን ኑረን ይሆን? ሞኞቹን ልታጃጃልን አትችሉም። ግን ፈጣሪ አምላክ ደግም ገደም ስለሆነ የዘመናት የተስፋችን አዱኛ አተርፎልናል። ይሄ ከተመስገን በላይ ነው። ሹመቱ በሁዳዴ ሌላው የመከራ ምጣት ቀን እና መልሱ በ ሰማዕታቱ በሐዋርያት ፆመ ሱባኤ መሆኑ የ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ትንግርተ ታምር ነው።
-
ነቃፊን አደራጀትህ ቃለምልስ ስታደርግ ከራርመህ አሁን ሞት አዲስ አባባን ጎበኛት አዘን፤ ተቃጠልን፤ ተቃጠልን፤ ደበን፤ እንኳንም መሪያችን ተረፈክልን ስትል ቅጭጭ አይልህም? ማተ ቢስ ሁሉ! የሰው ይቅር ፈጣሪ አይታዘብም? ፈጣሪ ቁጣውን አይልክም? የፈጣሪ ቁጥ እኮ ነው መንበር ላይ የተንጠልክበትን የውሸት ቡቶቶ ኩፍስ አውርዶ አፍርጦ ወንበር ብቻ አዳራሽ ሞልቶ የሚጠበቅህ። መጀመሪያ ንሥሃ ግባ፤ መጀመሪያ በማፍረስ ልብህ ውልቅ ካለበት የሴራ አረንቋ ራስህን አውጣ። ፍቅርን ከዛ በቁርሾ ከበከተ መንፈስ ጋር ማስተናገድ ዘመኑ እራሱ አልፈቀደለህም።

ብዕር ፈርተህ ስታሳግድ ውለህ እያደርክ፤ አንድ ነገር በተጻፈ ቁጥር የተለጠፈውን እንሳልኝ እያልክ በዬጓዳው ስትማጸን ውለህ እያደርክ ግን አንተ ምንድን ነህ? ማንስ ትባል? ምንስ ትባል? የግራጫ ገርጭራጫ ትባል ይሆን?

  • ግጣም አልቦሹ ሽርጉድ።

ቀድሞ ነገር ከአብይ የፍቅር ህይወት ጋር የሚገጥም ኮከብ የለህም፤ ልሁንም ብትል አያምርብህም፤ እኛን አዘግተህ ያስቀመጥቀው የፍቅርን ተፈጥሮ እና መርህ ተጻርህ ስለመሆን ማን እንዲነግርህ ትሻለህ፤ ያ በት/ ደረጃ/ በመንደር፤ በብልጠት፤ በ አርቲ ቡርቲ መስፈርትህ ያደረጃኸው የወረቀት ጣዕተህ ፈርሷል። ዕውነቱ ይሄው ነው።

በውሸት ድርድር ተንጠራርተህ ስትውድቅ፤ ስትፈርጥ ከርመህ አሁን ደግሞ አለሁ ነው። ሽሚያ፤ ሩጫ፤ ቀድሚ ምንትሶ ቅብጥርሶ እንቶ ፈንቶ። እራሱ ያን ገዳይ አውሬ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ስልጣኑን ቢስጥህ እኔ አንገቴ እሰጣለሁኝ አንተ ከዛ የተሻልክ፤ ያልነበርክም ልትሆንም የማትችል ስለመሆነህ። ለዛውም በደጋፊ ለመቆም እንኳን ፍቅርን አዋርደህ ስለኖርክ ተፈጥሮን ተዳፈረህ የኖርክ ስለሆንክ አትችለውም፤ አትመጥንም። ቢመርህም ሃቃዊ ኮሶው ይሄው ነው።

  • ቤተ አጓጉል

ይልቅ አቤቱ አጓጉል ልክህን አውቀህ ተቀመጥ። ልክህ ለዚህ የእዮር ልዕልና የቃል ቃና ዕውነት እና ትውፊት አይመጥንም። ከረባቱንም በፈጠረህ ተዎው፤ ገበርዲኑም በ እናትህ መቀነት ይዤሃለሁ ይቀርብህ፤ ካልልክ የሆነ ተራራ ላይ የተንተለጠለ ስለሆነ … አዛን ቅቤ አንጓችነት መቼውንም ጠረንህን አይቀይረውም። ተፈጥሮን ተጻረህ ቆመህ ሰውን እንደ ሮቦት ልብ ገጥመህ ስታስጨበጭብ የኖርክበት ዘመን አከተመ። ቢያንስ አሁን እፍረት ይኑርህ … ምነው ነጮቹ ፊት ነፈጉህ ወይንስ የገዙለህን ምንጣፍ ነጠቁህ …
  • ታጠቢነት ቢፈቅዱት!

የኔዎቹ ድሃን የማይወድ፤ ያልተማረን የሚጸዬፍ፤ አቅም የሚያሳድ የአውነት አንጡራ ጠላት፤ በውሸት የሰው ልጆችን ፍቅር ለዛውም ስደት ላይ ሲያታኩስ የከረመ የመርዝ ብልቂያጥ እንዴት እና እንዴት ብሎ ነው ኢትዮጵያን ያህል አገር ለመምራት ሰው ዜጋ ነው ብሎ መነሳት የሚችለው። ዜጋ እኮ ሰው ብቻ አይደለም። ኢትዮጵያዊ ፈረሱም፤ ተራራውም፤ ሸንተረሩም፤ አዝዕርቱም፤ ወቅታትም፤ አዬሩም፤ ዝናቡም፤ ወንዙም፤ ቡቃያውም፤ ዛፉም፤ ቁሳቁሱም፤ በርበሬውም ሽሮውም ዜጋ ነው። አይደለምን?

ስደት ላይ ስታሳድደን መከራችን ስታበላን ማህበራዊ መሰረታችን ስታሳጣን አቅማችን አፍለሰህ አሳድምህ አስገልልህ ብቻችን መለመላችን አስቀርትህ አንተ እንደ ሰው? አንተም እንደ ድርጅት? ኧረ በህግ? ይልቅ ላውንደሪ ይግዛ እና ሲነስቱን ከከረሙት ካድሬወችህ ጋር ተጠመቁ። የክትና የዘወትር የሚለወዬውም ማይክህ እንዲሁ ንሥሃ እንዲገባ ፍቀድለት፤ ከትከት ለነገሩ ባለስድስት ክንፍ ነህ ለካ አንተው በዛው ጠበል በለመድክበት ሽልክ ጣዖትህ ሰልሰው፤
  
በዛች በተቀደሰቸውን ዕልት በመጋቢት 24 ቀን 2010 ሐሴታዊ ዕለት እንኳኝ የዕውነት ደስ አላችሁ ተብለን ተውቅሰናል ተነቀሰናል። በደል ይረሳ መሰለህን? ትንሳኤ ተቀንቶብህ መርዞችህ መርዝ በተርት ተሰልፈው የማይኩ አልበቃ ብሎ ተስፋችን ሲያርዱ አንተ ተራራህ ላይ ተኮፈስህ ታዋጋለህ፤ ለነገሩ ከዬትኛው የውጊያ አውድ ተገኝተህ እውነትን የምትፈራ ፈሪ! ዛሬ ደግሞ ከነጅቡኖህ ፉከራ … ነገ ደግሞ አንዱ ሞቅ ካለው ላይ ጉብ ብለህ ዋጥ ስልቅ ወይ ደግሞ ትርትር …  አበስኩ ገበርኩ ስለ አንተ ይሉኝታ ቢሱ። እግዚዞ ስለግብዞች ... ብለናል ሞኞቹ … ታጠቢነት ከልሙጡነት አላቆ ቢማለድህ …

  • እርገት።

ናፍቆቶቼ ቅኖች የዕውነት አርበኞች ኑሩልኝ። ግን የኔዎቹ ከትከት ብላችሁ ለአይዋ ጅብኖ ትስቁበት ወይንስ ታዝኑለት  ወይንስ ጎንድ ተክለሃይማኖት ትምኙለት የእኔ ውዶች እንደ ምርጫችሁ ነው ቡፌው ተዘርግቷል …

ዕውነት ፍርድሽ መቼ ይሆን?
ዕትዬ እውነት አንቺስ መቼ ይሆን ቀን የሚወጣልሽ?


 መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።