ምን ተማን?

ምን ተማን?
ከሥርጉተ© ሥላሴ 24.06.2018 (ተፍቅርተ ሲዊዝ)
„ትእግስት ታላቁን ሃጢአት ጸጥ ያደርጋል እና …“
  
(መጽሐፈ መክብብ ምዕራፍ ፲ ቁጥር ፲፬)


ምን ሲሉ ሲሆኑት ምን ይሁንም ሲሉት
ምን ልብልም ሲሉት ልብልን ሲስሉት
ምን ይሆናል ሲሉ ሊሉት ሊሰልሉት
ምን ተሆነ ብለው አባብለው ሊቀልቡት
በበቀለው አፈር አለበቅልም ሊያዋልዱት
በበቀለው ፍሬ አልኖርም ሊያቃቡት
በበቀለው ትንኝ ዘር ገብያ ሊያማርቱት
ኮተት እንቶኔ በወጉ ሊልጡት።

ከውስጥ በመላውም መላላ አጉርቶ
ቀን ሲመሽ ሲነጋ ኩላሊት ተጎታቶ
መጎተት ሲባዛ ገመዱ ተሰልቶ
በስሌት ልግመኛ ቀን ከሌት ተሴርቶ
መውደቅ ተደርድሮ ውድቅት ተፈታቶ
በመፈታት ቀምር መጋባት ተቃኝቶ
በልብ አልባ ኩፍኝ ፒኒስል ተውግቶ
በውጋት ማህበር ማን ተማን ተለይቶ?

  • ተጣፈ በአሁኒት … ተደቂቃ 24.06.2018 ተሲዊዚሻ።
  • ሥጦታ ለነምኖ።  
  • የኔዎቹ ግጥም ካሰኛችሁ … እነሆ

ናፍቀሽኝ አገሬ።

አፈሬ ነው መስመሬ(23 06 2018)


ኑሩልኝ እነ እማ /// አባ ቅንዬ።

መሸቢያ ጊዜ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።