የብአዴን የሥም ለውጥ የተስፋ ልጣጭ ነው።
የሥም መዋጮ ተስፋ ሙጣጭ - ልጣጭ። „እንሆ በማትረቡበት በሃሰት ቃል ታምናችኋዋል።“ ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፯ ቁጥር ፰ ከሥርጉተ© ሥላሴ 01.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። መሆን መቻል እና መሆን መፈለግ ልዩነት አላቸው። የባህርዳሩ የአማራን ሥም የተሸከመው የብአዴን ጉባኤ ደንቡ ላይ የ አባልነትን መስፈረት በሚመለከት ለውጥ እንደሌለው ገልጾልናል። "ደንቡን እና ፕሮራሙን የተቀበለ ማንኛውም ዜጋ አባል መሆን ይችላል፤ መሪ መሆን ይችላል ብሎናል።" የዶር አንባቸው እና የዶር ገዱ አንዳራጋቸው የወጣቶችን ባህርዳር ወሎ ደብረታቦር ያነጋገሩበት፤ ያወያዩበት ድካማቸው አሳዘነኝ። የውነት አሳዘነኝ። የውርንጫ ድካም ነው። ለዚህ ፌክ ጉዞ ከመድከም በዝምታ መታደም በስንት ጣዕሙ። ስለዚህ ጉዳይ ከሆነ ስለምን ጊዚያቸውን ያባክናሉ? ይህችን መሰል ተረብ አደማ ላይ፤ ትግራይ ላይ፤ አሶሳ ላይ፤ አፋር ላይ፤ ቤንሻንጉል ላይ አትሞከርም። ማላጋጥ! የአማራ ዴሞክራሲያ ፓርቲ መባል ሥሙ ምን ያድርገለታል - ለአማራ። ዓርማውም ቢሆን አባይ የኢትዮጵያ ሃብት ነው። አማራነት በማለት ሳይሆን በመሆን ሆኖ መገኘትን ይጠይቃል። ከኢህአዴግ ጉባኤ የመጨረሻ ወሳኔ በኋዋላ በጠ/ ሚር አብይ አህመድ ቀጣይነት ላይ ተ ጽዕኖ ማሳደር ስላማልፈግል አንጠልጥዬ በቀጠሮ ዋናውን ፍሬ ነገር አሰነብተዋለሁኝ። በጣም ሞጋች ጉዳዮች ይነሳሉ ዘግዬት ብለው። አሁን ግን አሳቸው እንዲቀጥሉ ስለምፈልግ በዝምታ መቆዬትን እምርጣለሁኝ። የሆነ ሆኖ ትናንት የወያኔ ሃርነት ግርፍ የነበረው ብአዴን ሥሜን ቀዬርኩ ይለናል። ድሮም እኮ በአማራ ውስጥ አልነበራችሁም። አሁንም የላችሁም። ወዲፍትም አትኖሩም። ተልዕኮችሁ...