የብአዴን የሥም ለውጥ የተስፋ ልጣጭ ነው።

የሥም መዋጮ ተስፋ ሙጣጭ - ልጣጭ።
„እንሆ በማትረቡበት በሃሰት ቃል ታምናችኋዋል።“
ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፯ ቁጥር ፰
ከሥርጉተ© ሥላሴ 01.10.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።


መሆን መቻል እና መሆን መፈለግ ልዩነት አላቸው። የባህርዳሩ  የአማራን ሥም የተሸከመው የብአዴን ጉባኤ ደንቡ ላይ የአባልነትን መስፈረት በሚመለከት ለውጥ እንደሌለው ገልጾልናል። "ደንቡን እና ፕሮራሙን የተቀበለ ማንኛውም ዜጋ አባል መሆን ይችላል፤ መሪ መሆን ይችላል ብሎናል።"

የዶር አንባቸው እና የዶር ገዱ አንዳራጋቸው የወጣቶችን ባህርዳር ወሎ ደብረታቦር ያነጋገሩበት፤ ያወያዩበት ድካማቸው አሳዘነኝ። የውነት አሳዘነኝ። የውርንጫ ድካም ነው። ለዚህ ፌክ ጉዞ ከመድከም በዝምታ መታደም በስንት ጣዕሙ። ስለዚህ ጉዳይ ከሆነ ስለምን ጊዚያቸውን ያባክናሉ? ይህችን መሰል ተረብ አደማ ላይ፤ ትግራይ ላይ፤ አሶሳ ላይ፤ አፋር ላይ፤ ቤንሻንጉል ላይ አትሞከርም። ማላጋጥ! 

የአማራ ዴሞክራሲያ ፓርቲ መባል ሥሙ ምን ያድርገለታል - ለአማራ። ዓርማውም ቢሆን አባይ የኢትዮጵያ ሃብት ነው። አማራነት  በማለት ሳይሆን በመሆን ሆኖ መገኘትን ይጠይቃል።

ከኢህአዴግ ጉባኤ የመጨረሻ ወሳኔ በኋዋላ በጠ/ ሚር አብይ አህመድ ቀጣይነት ላይ ተጽዕኖ ማሳደር ስላማልፈግል አንጠልጥዬ በቀጠሮ ዋናውን ፍሬ ነገር አሰነብተዋለሁኝ።  በጣም ሞጋች ጉዳዮች ይነሳሉ ዘግዬት ብለው። አሁን ግን አሳቸው እንዲቀጥሉ ስለምፈልግ በዝምታ መቆዬትን እምርጣለሁኝ።

የሆነ ሆኖ ትናንት የወያኔ ሃርነት ግርፍ የነበረው ብአዴን ሥሜን ቀዬርኩ ይለናል። ድሮም እኮ በአማራ ውስጥ አልነበራችሁም። አሁንም የላችሁም። ወዲፍትም አትኖሩም። ተልዕኮችሁ ምን ስለመሆኑ አሳምረን እናውቃለን። ችግሩ ደግሞም ሥሙ አልነበረም።

ችግሩ የአማራን ሥነ - ልቦና የሚያቀጭጭ የሚጫን፤ ተስፋንው የሚያደቅ አማራን የመነቅል፤ ከፖለቲካ - ከማህበራዊ ጉዳይ ከኤኮኖሚ ያገገለ ፖሊሲ ሲከተል ነው የነበረው ድርጅቱ። ይልቅ አሁን እንኳን ደስ አለዎት ልበላቸው ሄሮድስ መለስ ዜናዊን። ሌጋሲያቸውን ስላስቀጠሉላቸው።

የ66ቱ ሊሂቃን የሚስማሙበት፤ ተጣልተው የሚታረቁበት ወሳኙ ጉዳይ አማራ እስከ መቼውም በፖለቲካ አቅሙ ልክ ራሱን ሆኖ እንዳይወጣ ያሲሩት ረቂቅ ሚስጢር ነው። አሁን እማስተውልበት ሁኔታ አለ።

"አሁን ብአዴን ነባሮችን አራገፍ፤ ወያኔ ያወጣለትን ሥም ቀዬረ፤ ዓርማ ቀዬረ ሲባል አዳምጠን።" አሁንስ የማንን መንፈስ ተሸካሚ ነው የተሆነው? ዋናው አይዲሎጂው ነው እሱ አልተነካም። የ27 ዓመቱ መከራ ላይበቃ አሁን ሌላ መከራ ቻል ተብሏል - አማራ።

ዋናው ጉዳይ እኮ የአማራ ሊሂቃንን ከፖለቲካ ማራቅ ነው። ከማዕካላዊ መንግሥት ድርሽ እንዳይሉ በመንፈስ መፋቅ ነው። ብዙ ቃለ ምልልሶችን አዳምጣለሁኝ፤ ይገርመኛል በጣም። በአንድ ቀን ሁለት ሦስት ዜና ሲመጣ እና የሃላፊዎችን ሰብዕና ስመለከት እንዴት በባይታወርነት ይህ የአማራ ህዝብ እንደሚገረፍ አስተውላለሁኝ፤ እዬተቀጣ ነው ያለው። ራሱ ዜናው ሲመጣ ይቀጣል።
አማራ ብቻ አይደለም በኦርቶዶክስ ተዋህዶም ያነበረው ተጽዕኖ አሁን ያለውን የሥልጣን ተዋረድ እና ዕውቅ የሚባሉ የፖለቲካ ሊሂቃን ቦታዎች ሁሉ፤ የመንግሥት ሃላፊዎችን ሳይ አንድ ትውልድ መክኗል። አሯል። 

  • ·       ን አለ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ብትሉት።

ስለምን አዴፓ ተባለ? ለምን ኢዴፓ አይባልም። የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ማለት። በቃ! ሁሉን ኢትዮጵያዊ የሚቀበል ከሆነ የተሻለውም የሚመረጣው ይኸው ነው።  በአማራ ሥም የጉልት ችርቻሮ ሱቁን ቀብሮ እና ከርችሞ ብሄራዊ ፓርቲ መሆን ነው። በቃ። ከሳማያዊ ፓርቲ እናንተ በምን ትለያላችሁ? እናንተም ህብረ ብሄራዊ ናችሁ እነሱም ህብረ ብሄራዊ ናቸው። እንዲያውም እነሱ ተረጋጭ፤ ጨቋኝ ያልሆነ ነው። ግልጽና ቀጥተኛ ነው የ እናንተ ግን ቁልጭ ያለ ማባጨል ነው በልግጡ መንገድ በሪቂቁ ደግሞ Discriminationéé



ከቶ ማንን ነው የሚላግጡት? ማንን ነው የሚያሾፉበት? ዓርማ ምንትሶ ቅብጥሮስ ለአማራ ትውልድ አይጠቀመውም።

አማራ በአቅሙ ልክ፤ በሁለመናው ልክ ተሸፍኖ ተጠቅልሎ ሳይሆን በፈለቀው አቀሙ ልክ ቦታ እንዲያገኝ ማድረግ ነው ሊሆን የሚጋባው። የድርጅቱ ተልዕኮም ሊሆን የሚጋበው ይኸው ነው። ማነው እናንተን የፌድራል መንግሥት ቃሬዛ ተሸካሚ ያደረጋችሁ?

 በችግር ጊዜ ሲያሻግር የኖረ? እም!ያሻገር? ደንቄም! ማን ከውለታ ቆጥሮለት? አይደለም የሩቁ ጊዜ የዛሬውን ከአፍንጫችን ባለው ጊዜ እንኳን ያዬነውን አይተናል፤ የሰማነውንም ሰምተናል? ልግጫ!

አንዲት ሴት  አቅም ያላት የማታስፍር የፖቲካ ሊሂቅ አንኳን በ27 ዓመት ውስጥ መፍጠር አልተቻለም። አሁን ሰምተናል ብሄር አልባዋን ሊሂቅ፤ በራሳቸው ጊዜ የበቁትን ብአዴን ጉባኤ ላይ አንዲገኙ ተደርጎ የማዕከላዊ ምክር ቤት አባል አድርጋችሁ በድርጃታዊ ሥራ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስን  ለኢህአዴግ ጉባኤ ታማጣላችሁ።

ለሳቸው መቼም ፍርጃ ነው። አዲስ አበቤ ብሄረ አልቦ ነው። ያው ዲሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት እንዲህ ይገለጣል። አቶ ታከለ ኡማም በመሰል ሁኔታ ነው ኦዴፓ ላይ የተወከሉት፤ እሳቸውስ የነበሩበት፤ የሚያምኑበት ነው፤ አሁንም የ አፍሪካ መዲና አሰተዳደሪ ሆነው የ ኦሮሞወ ጣቶችን ሰብሰብው አነጋጋራሉ፤ መቼም ልበላቴው መንፈስ ውርዴ ነው ይህ።

የሆነ ሆኖ አሁን እንሂ ምስክኒ መራሂት ሊሂቅ ምን አድርጊ ተብለው ነው ይህ መከራ የተጫነባቸው? ፈረዳባቸው። 
  
ያሳዝናል 27 ዓመት ሙሉ አንድ ከዚህ ግባ የሚባል የልብ የሚያደርስ ሰው አልተፈጠረበትም። የሚያስዝነው፤ የሚያርመጠምጠው፤ ማህጸንን  የደም ዕንባ የሚያስለቅሰው ደግሞ ይኸው ነው። አሁን ሳጅን በረከት ደልደል በለው ደም መላሹን ውሳኔ ያጣጥሙ። የተከሉት ሙጀሌ ቀጥሎላቸዋል። የሾማቿው የጤና ጥበቃ ሚኒስተርም ይቀጥሉሏቸዋል ዘና ደልድል ብለው።

ወዮ የአማራ እናት! ሁልጊዜ ጠብንጃ ያዥ፤ ብርጭቆ ለቅላቂ ልጆሽ አንዲሆን ዘመን ከዘመን እንዲህ መሻገሩ ነው። ያልታደልሽ፤ አሁንም እንደ ኖርሽበት ጫን ተደል መከራ ተሸከሚ ተብለሻል። ለነገሩ የአንቺን ዕንባ ማን ከአጀንዳ አስገብቶት?

የአማራ ጥቅሞችን መብቶችን በማስከበረም ውሳኔ ላይም መከራው ይኸው ነው። ይሕው አዬን እኮ እነ አቦ በቀለ ገርባ ወሳኝ ቀን ሲመጣ መካራ ላይ አስቀምጠውን ወደ ራሳቸው አጀንዳ ሲገሰግሱ።

የሆነ ሆኖ እኔ ሥርጉተ እንጂ ደጅይጥኑ አይደለሁኝም። በሥሙ በሚጠራ ፓርቲ እንዴት ነው የምትቀልዱት? እንዴት ነው እምታላግጡት? እንዴት ነው እምታሳዝኑት? ማፈሪያ! ህብረ ብሄር ቢሆን እኔ ግድ የለኝም፤  ከኢትዮጵያዊነት በላይ ዕወቀት ስሌለ። በአማራ ሥም ግን አይነገድ።

27 ዓመት ያሳረዳችሁት፤ 27 ዓመት ከማናቸውም ብሄራዊ አገራዊ ጉዳይ ተነቅሎ፤ ከስሎ፤ በልዞ እንዲቀር መደረጉ አልበቃ ብሎ አሁን ቃሬዛ ሁነህ አሻግር ተብሏል። በሥሙ ቁጭ ብላችሁ ይህች ጉዳይ ሆና ይህችን የማስፈጸም አቅም የላችሁን። 

ምን አለ አዳራሹን ሙሉ ሰኔል እና ቹቻ ገዝታችሁ ብታከፋፍሉት ለጉባኤተኛችሁ በሙሉ ለድጋሚ የሙት ዓመት አከባበሩ። ኦዴፓ  የአፍሪካ መሪነታችን ኦሮሞ ያሳያል ነው ሞተው፤  አማራ በተቀበርክበት ጉድጓድ አፈር ተዘጋጅቷል እና በወሳንሳ ወስድን እንድፍንሃለን ነው የተባለው። ፌክ። ዛሬ አቶ ደመቀ መኮነን እንዲቀጥሉ እንፈልጋለን ስንል እኮ ዕድሉን አግኝተው ተፈትነው ሰላዬናቸው ናቸው። ለውጥ የሚባለው ነገር ሄዶ ሄዶ አማራን መቀበር ላይ ነው ዋነኛ ልትሜት ግቡ። 

ድርጅታዊ ሥራ ኑረንበታል አሁንም እምትመሩት በዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት ነው፤ መጪው ጊዜም ለአማራ ህይወት ጨለማ ነው። የተሻለ ዘመን ይመጣል ብዬ እኔ አላስብም።

ዓርማ ደንብ ፕሮግራም ለዛው ግርባ ውሃ ለሙሙላት ያገልግ። የ66ቱ ርዕዮት አማራን ያሸከመውን ቀንበር ይቀጥል ዘንድ አሁን በአዲስ ስልት እና ዘዴ በጥበብ ቻል ተብሎ ተፈርዶበታል - አማራ።

ድንኳኑን ጥሎ አማራ እዬዬ ይበል እንደ ለመደበት ለነገሩ ልብም አልፈጠረለትም። ለደመር ውሎ እንግዲህ ይቀጣጠር። ለዚህው ነውን ይህ ሁሉ ሽርጉድ? ይህ ሁሉ አጀብ እና ላይ እና ታች ዲኮሬሽን? አስፈላጊ አልነበረም። ለሎሌነት እና ለግርድና ምን የአሰሪና ሠራተኛ ውል በቂ ነበር።
ለሎሌነት እና ለግርድና ምን የአሰሪና ሠራተኛ ውል በቂ ነበር።
ለሎሌነት እና ለግርድና ምን የአሰሪና ሠራተኛ ውል በቂ ነበር።
ለሎሌነት እና ለግርድና ምን የአሰሪና ሠራተኛ ውል በቂ ነበር።

የአማራ ተጋድሎ አጠናከሮ መቀጠል ይገባል!

የኔዎቹ ኑሩልኝ።  

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።