የአላዛሯ ኢትዮጵያ ድንብልብል መከራ፡

ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ።
„ታላቅ ክንፍ እና ብዙ ላባም ያለው ሌላ ታላቅ ንስር ነበር፤ እነሆም
ያጠጣው ዘንድ ይህ ወይን ሥሩን ወደ እርሱ አዘነበለ አረጉንም
ከተተከለበት ከመደቡ ወደ እርሱ ሰደደ።“
ትንቢት ህዝቅኤል ፲፯ ቁጥር ፯ እስከ ፰
ከሥርጉተ©ሥላሴ
01.10.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።



  • ·      የገማናችን ብርከታው።  

ይግርም ነው። አቶ ጌታቸው አሳፋ ሱዳን ሄዱ የሚለው ነገር አያሳምነኝም እዛው ትግራይ ውስጥ ነው ያሉት ብዬ ጽፌ ነበር፤ አይደለምን? አሁን ይድነቃችሁ ብለው የወያኔ ሃርነት ትግራይ የምክር ቤት አባል ሆነው መመረጣቸው ብቻ ሳይሆን በቀጣዩ የኢህአዴግ ጉባኤም እንደሚታደሙም ተገልጧል። የማስፈራሪያ ትልቁ ዘንግ፤ የማንአለብኝነትም ተጋድሎ …
  
ለዚህም ነበር እኔ ችግሩ ሌቦች ተፈቱ ሳይሆን ለውጡ ሊቀለበስ ይችላል ብላችሁ እሰቡ ያልኩት"ጭንቁ ሌቦች አቅም አገኙ ነው"  ፤ አቅማቸውን አጠናከረው የወያኔ ሃርነት ትግራይ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ወይንም ሞት ብለው ተነስተዋል። እኛም ጉዝጓዝ ሆነን መባጀታችን መርሳት የለብንም። 

ኦዴፓ ውስጥም ማን ማንን እንደሚደግፍ አዲስ እጩ ያቅርቡ አያቅርቡ ገና ሰው ልብ ያላለው ጉዳይ ነው። ኦዴፓ ሙሉ ድምጹን ይዞ ይጋባል የሚል ዕድምታ አነባለሁኝ። ከሆነ ጥሩ ነው። 

ነገር ግን የአቶ ጃዋር መንፈስ ሌላ መሰናዶ የለውም ብሎ ማሰብ እራስን መርሳት ይመስለኛል። ሌላ ድልድይ ፈላጊዎች ናቸው። አፈንግጦ ለመውጣትም የተሰናዱበትን አመክንዮ ሊኖር ስለ መቻሉም ፈጣሪ ነው የሚያውቀው። ያ ባይሆን ወያኔ ሃርነት ትግራይ ይህን ያህል የልብ ልብ አያገኝም ነበር። 

ሌላው ወሳኙ የደቡብ ህዝቦች ፓርቲ ነው። ስበሰባው አላለቀም ምን የት ላይ አቋሙ እንዳለ ገና ነው። እንግዲህ ሴቶች ብልህነታቸው እና ጥበባቸው የሚፈተንበት ወቅት አሁን ነው። ሴቶች ለድምጽ አልባዎቹ እናቶች ዘብ መቆማቸው የሚረጋጋጠው አሁን ነው። ይህ ዘመን የሴቶች የአመራር ጥበብ ልቆ የሚታይበት መፈተኛው ነው።  የአንቀጽ 17ቱ የውጭአሌው ሚስጥርን ይረግጡታል ወይንስ ዳግሚያ ተንሳኤውን ያውጁታል? 

ዛሬ የኢትዮጵያ መከራ በቀጣይነት እንዲቀጥል መወሰን ያለ መወሰን ጉዳይ በወ/ሮ በሙፍሪያት ካሚል እጅ ነው። መክፈቻ ንግግራቸው ጭብጥ እውነት ለመናገር አስደግነጦኛል። ምክንያቱም መንፈሱ ከአብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ተለምዷዊ ጉዞ ፈቅ ያለ አልነበረም፤ 

በሌላ በኩል በእህት ፓርቲ በሚሏቸው በሦስቱም ጉባኤዎች መቀሌ፤ አዋሳ፤ ጅማ ላይ ወኪሎቻቸው ሴቶች መሆናቸውን ሳይ ደግሞ ደስ ብሎኛል። ሴቶችን ወደ ፊት ለማምጣት የትኛውም ቦታ ሃላፊነት ያገኘች ኢትዮጵያዊ ሴት ያልደፈረችውን የመጀመሪያ ምዕራፍ ከፋች ሆነው አግኝቻቸዋለሁኝ። አኩርተውኛል። ትልቁን የሴቶች አቅ የተዘጋበትብ በር አስከፍተዋል። 

ይህ በሴቶች ታሪክ ውስጥ እጬጌያችን ነው። ብዙዎቹ ቦታ ሲያገኙ ይቀናሉ የበለጣቸውን ተፎካካሪ ሆነው ሊወጡ ይችላሉ የሚባሉ ሴቶች እንዳይወጡ ይጫናሉ፤ ይጋፋሉ፤ በትንሿ መድረክ እንኳን ምስጋና ጉዳይ ሆኖ ለዛ አንኳን ያለውን መከራ ፓል እሳተፍ በነበርኩበት ጊዜ ያዬሁት ጉዳይ ነበር። ትክ ማዋጣት አልተለመደም እንዲያውም በር መዝጋታ እና ማዘጋት ... 
  • ·       ኤርምያስ ወአብይ። 

ሌላው የገረመኝ ነገር አንድ ወንድሜ እንደ ነገረኝ ከሆነ አቶ ኤርምያስ ለገሰ ዶር አብይ አህመድን እንደ „አብርሃም ሊንከን“ አያቸው ብሎኛል። ጸሐይ መሬት ወርዳ፤ እግር ኖሯት ስትራመድ የማዬት ያህል ነበር የተሰማኝ። በምን ቀመር ነው አሁን እሱ የዶር አብይ ደጋፊ ብቻ ሳይሆን ተሟጋች የሆነው በማንፈሴቶው አምልኮተ ዝንባሌ ወይንስ በእውነት ቀመር።

ማለቴ በእውነት ቀመርማ ዶር አብይ አህመድ ትናትም ነበሩ። በቀደመው ጊዜ „ህሊና“ በሚል ሞግቻዋለሁኝ። ጠ/ ሚር ሲሆኑ እንደ እብድ ካደረጋቸው ወገኖቼ ውስጥ አንዱ ነበር። በዶር አብይ አህመድ ጉዳይ ከሳጅን በረከት ስምዖን ለይቼ እኔ አላዬውም። እንዲያውም ትንሹ በረከት ብዬ ሁሉ ነበር። ፈጽሞ ዶር አብይ አህመድን ማዬትም፤ ማድመጥም የማይፈልጋቸው እንደ ነበር ነው እኔ የማውቀው። የ አሁኑ መረጃ እንደ ታምር ነው ያዬሁት። 

እንዲያውም ኢሳትን እርግፍ አድርጌ እንደተዎው የሆንኩት በዚህ ምክንያት ነው። መታመም አልፈልኩኝም። በማህል ያጣሁዋቸው ወንድሞቼ አሉ። ሌላ ሰው ቢሆን ግድ የለኝም እሱ ግን ጎርፍ የከመረው ፖለቲከኛ አይደለም፤ ብዙ ነገር ያውቃል፤ ፓለቲካን ከውስጡ ሆኖ የኖረ፤ መሬት ላይ የሠራበት ሰው ነው። ስለምን ለውጥ ፈልጎ ለውጡን ሲያብጠለጥል እንደ ነበር ግን ቢገባኝም አልገባህኝም ማለት እሻለሁኝ።

አንድ የፖለቲካ ሰው ማናቸውንም የፖለቲካ ሁኔታ ከራሱ ስሜት በርቀት ማዬት፤ ከራሱ ኢጎ በርቀት መተርጎም ይገባዋል። ይበልጠኛል ብሎ መድፈር አለበት። አቅሙ ሙሉ ግን አቅሙን የሚፈትን አቋም ውስጥ ያን ያህል ደፍሮ መግባት ለራሱ ታሪክ እና ለሰብዕናው ስላልተመቸኝ ነበር የሞገትኩትኝ።

አሁን መቼም እንኳን ለዚህ አበቃህ ነው የምለው፤ እንዲህ ዶር አብይ አህመድን ከድንቁ አብርሃም ሊንከን ጋር ካጠጋጋ … ደጋግሜ ሳዳምጠው አንቺ ትዝ አለሽኝ ብሎ ነው አንድ ወንድሜ የደወለልኝ። እሱ እንኳን አላምን ስላለ ነበር ደግሞ አዳምጦ አረጋግጦ የነገረኝ።  

ሰው ሆኖ መቆም ማለት አንደኛ ስው በከፋው  ሰዓት ከጎኑ መቆም፤ ሁለተኛ ብስል ከጥሬ መለዬት፤ እንክርዳድ ከስንዴ መለዬት ያስፍልጋል። ያን ጊዜ ቀርቶ አሁንም ያ ነፍስ መከረኛ ነው። በጠቅላላ ያን ያህል በቲም ለማ ላይ የነበረው ጠናና አቋም በፍጹም ሁኔታ ለውጥ ፈላጊ ነበር ለማለት አያስደፍር ስለነበር ነው በጣም ተጋፍቼ እንደዛ የጻፍኩት።

ያ ከጻፍኩኝ በኋዋላ እንኳን በስፋት ቀጥሎበት እንደ ነበር ጹሑፎቹን ሳተናው ላይ አነብ ነበር። ለዚህም ነበር „ቋንቋ ማወቅ ሊቀ ሊቃውንትንት እንጂ መወቀሻ ሊሆን አይጋባም“ የሚል ሌላ ጹሑፍ መጻፍ የተገደድኩት። በወ/ሮ አዜብ ውክልና ላይም እንዲሁ የትግራይ ህዝብ ጫና እና መርህን የጣሰ ሁኔታ ሲያነሳ እሱንም ከፓርቲ አደረጃጃት መርህ አንጻር ሞግቼው አሁን እዬሆነ ያለውን እያዬን ነው። ጉባኤው ወቅቱን ጠብቆ ነው የተካሄደው። ለወ/ሮ አዜብ መስፍን ተብሎ የተለዬ ነገር ሲከውን አላዬነም። በዛ ወቅት ከእሱ በፍጹም የማልጠብቃችው ነገሮችን ይጽፍ ይናገር ነበር። አሁን አላውቅም።

ብቻ የነበረው ዘመቻ እና ወከባ አገር ለመምራት ስለማትበቁ እዛው ተቀመጡ ዓይነት የነበረው የበዛ ግፊያ ብዙ መንፈስ እንደሚያሸፍት ስጽፍ ባጅቻለሁኝ። ይህው አሁን ወያኔ ሃርነት ትግራይ እንዲህ እንደ ገና ጥርስ አውጥቶ አይኑን በጥሬጬው አሽቶ ለበለጠ መከራ እና አሳር የሚከተለውን ርዕዮት አላስነካም በዛም እቀጥላለሁ እንዲል ያስቻለው በዚህ ምክንያት ነው። አልሚ ምግብ ፍሬሽ አዬር የመገብነው እኛው ነን።

ሰሞኑን አቶ በረከት ስምዖን እዛ ነበሩ። የሄዱበት ዋናው ይህን ሴራ ለማድራት ነው። ግን መቼ ይሆን እሳቸውን መሬት በቃኝ ብላ እንጦርጦስ እምትሸኝልን?
ጠላትን አለማወቅ፤ የሃይል አስላለፍ ፍልስፍንን አለመረዳት፤ የእኔ ብሎ ከውስጥ አለማጥናትም ብዙ አቅም ያሳጣል። 

እነሱ ትልቅ ሚዲያ አላቸው በዚህ እኛ ስንሰበስብ በዚህ እሱን ያህል ሰው ደግሞ ጉብ ብሎ ከላይ የሚፋርስ መልዕክት ይልክ ነበር። ያም አልበቃም ብሎ ብራናው ይጨናነቅ ነበር። ያ ልባም ሳተናው ባይፈቅድ ኖሮ ዛሬ ላለው እርሾም ባልተበቃም ነበር፤ የሰው ልጅ ምንጊዜም ከእውነት ጋር ነው መቆም  ያለበት። ለምን የእናት ልጅ አይሆንም። የሚበልጥ፤ ብቁ፤ ሰብዕናው የተሟላ፤ ከሆነ ቅደመኝ ማለትን ያስፈልጋል።  
  • ·       ሳዲቅ ወአብይ።

ሌላው የጋዜጠኛ ሳዲቅ ጉዳይ ነው። እባክህ አልጣህ እያልኩ ስማጸነው ነበር። እሱ ደግሞ አሁን አንድ ዝግጅት ይዞ ብቅ ብሏል። ህብር እና ቢቢኤን ዜና በመደበኛ የምከታታላቸው ነበሩ። 

በዶር አብይ ምክንያት ነው እርግፍ አድርጌ ነበር የተውኳቸው። ሰሞኑን የተሻለ ትግል ስለሚያደርጉ ግን እያዳመጥኳቸው ነው። በመዳፋችን የከዛ የ አብይ መንፈስ አቅም በላይ ቢኖር ምንም አለንበረም። በ10 ዓመትም ተኪ ለማግኘት እኔ አልጠብቅም። ብዙ ነገር በ አብይ መንፈስ ውስጥ አለው - ከ እኛ ስለተፈጠረ፤ ካለዘመኑም ስለተፈጠረ ብቻ ነው።

የሆነ ሆኖ ሩቁን ለማግኘት ከቅርብ ያሉ አጋጣሚዎችን በአግባቡ መያዝ እና አቅም ለዛ መለገስ እጅግ ወሳኝ በነበረበት ወቅት ነው ተቃራኒ ሃሳብ ያላቸውን ተንታኞች እያቀረቡ ሲያስተጋቡ የነበረው። ቅን መንፈስ እኮ የገብያ ሸቀጥ አይደለም። በፍጹም። 

አንድን ሰው ወደ ተፈለገው አቅጣጫ ለማምጣት ብዙ ጥረት ይጠይቃል። ለማብቃት ደግሞ የመዋለ ዕድሜ ልክ ሥራ ነው። የዶር አብይ አህመድ ትልቁ ጸጋ ሰው ማምጣት ብቻ ሳይሆን ማብቃትም ተልዕኳቸው ነው። ይህን ብልህነታቸው ገና ሰው ያለዬው የተከደነ ሚሰጢር ነው። ስስታም አይደሉም እውቀትን ለማሸጋገርም። ከዛ በላይ ወደር የለሽ የሃሳብ ልቅና እና የ አዲስ ሃሳብ ጸጋ ባለቤት ናቸው።  ይህም በትሁት መንፈስን በገፍ ማቅናት ከልብ የሌላውን ሰብዕና በፍጹም ቅንነት በማቅረብ ጭምር ነው።

ያን ጊዜ በጊዜያዊ ወጀብ ዘላቂ ጥቅም መስተጓጓል አልነበረበትም። አሁን እማዬው ውሃ ቅዳ ውሃ መለስ ነው። የበተንከውን ለመሰብሰብ ደግሞ እንደ ገና ሌላ ኢነርጂ ማቃጣል። በረዶ አድርገህ አሳስረህ ከጥቅም ውጪ ካደረከው ወዲያ። አቶ ጃዋር መሃመድ ፕ/ ህዝቃዬል ጋቢሳ ማነው ሰፊ ሽፋን ሲሰጣቸው የነበረው?

ቢቢኤን ኦቦ ለማ መገርሳ ወደፊት ሲመጡ ይህን ሰራ።

"News Analysis: Hidden Truth About Lemma Megersa"


ከሁለት መቶ ሺህ በላይ ሰው አዳምጦታል። ኦቦ ለማ መገርሳ መንፈሳቸው ቢያንስ ለዛ ወቅት ያስፍለገናል ብሎ አለመሳብ ነበር። ሃላፊነት የጎደለው የራሳችን ገመና ነበር።

ቀጠለ ዶር አብይ አህመድ ወደ ፊት ሲመጡ ደግሞ ይህን ሰራ። አሁን የምናዬው ትርምስ የዛ ቦንብ ትርምስ ነው። „በኦሮሞ ዘንድ ተቀባይነት የለውም፤ ሰብዕናው ያልተሟላ ነው፤ ልምድ የለውም፤ ለማ ወደፊት ካልመጣ ይፍረከረካል“

ኦቦ ለማ መግርሳ ዕውቅና እያገኙ፤ ተቀባይነት እዬአገኙ ሲመጡ ቢቢኤን ይህን ሠራ።

ሕወሓት ለማ መገርሳን ለጠቅላይ ሚኒስተርነት ለምን አልፈለገችውም?

 – ጀዋር መሐመድ ያብራራል | ከሳዲቅ አህመድ ጋር ተወያይቷል


ሰኔ 16፤ ሐምሌ19 የቆሞስ ኢንጂነር ስመኘው ህልፈት፤ በተለያዩ ቦታዎች ያሉ ግጭቶች ዋናው ወያኔ ሃርነት ትግራይ ቢሆንም የጃዋርውያን የኦነጋውያን አስተምህሮ የሚከተሉ ወገኖችም ውጤት ነው። እኛም በሚዲያችን አግዘናቸዋል።

ራሱ ኦህዴድ ውስጥ ይህ ዘገባ ብዙ ስንጥቅ ይፈጥራል። ዛሬም ያለው የቀጣይ የጠ/ ሚር ምርጫ ጭንቅ ከዛ የመነጨ ነው። እራሳችን ጥርት ያለ አቋም፤ ጥርት ያለ የለውጥ ፍልስፍና፤ ጥርት ያለ መንገድ ተከታዮች አይደለንም፤ አልነበርንም።
ዛሬ ደግሞ ይህን ይለናል ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ። መልካም ነው ግን በዚህ መጽናት ያስፈልጋል። የሰው ልጅ መንፈስ የእጅ ዳንቴል አይደለም። 

አብሶ አዬር ላይ ከሆነ ይህን የተስተካካለውን አቋም ለማድመጥ ያልታደሉት በቀደመው መንፈስ እንደ ተበከሉ ሊኖሩበት ሊሆኑበት የፈቀዱ ወገኖችም ሊኖሩ ይችላሉ። ዕድሉ ያላቸውም ይህን የ አሁኑን አቋም ማድመጥ ቢችሉ እንኳኝ በቀደመው አቋመቸው ሊጸኑና እና ይህኛው ማሻሻያ ላያሳምናቸው ይችላል። ምክንያቱም ሙግቱ የፊት ለፊት አይደለም። የ አዬር ላይ ነውና። ራስህ ያፈረስከውን ቤት ደግሞ ያንኑ ለመስራት አቅም ማፈሰስ? 

የአብይን ቅያስ መቀልበስ? ሳዲቅ አህመድ
  • ·       ትናንት የነበረው አብይ ነው ዛሬም ያለው ወደፊትም የሚኖረው።

ምን ሌላ አብይ እኮ አይደለም ድሮም የምታውቁት አብይ ነው ዛሬ ያለው። ዶር አብይ አህመድ ስለመቀጠል ብቻ አይደለም ኢትዮጵያ ስለመቀጠሏ ራሱ አሁን ሰፊ መከራ ነው ያለው።

አሁንም ቀውሶችን ተከትሎ ይውረድ የሚሉ መንፈሶች እንዳሉ ስለማውቅ እና በኦዴፓ በኩልም የተጠቀለለ ያልተገለጠ የራስ ገመና ጉዳይ አለ። ኢትዮጵያዊነትን ለማስጠጋት ያልፈቀዱ እንዳሉ ትንቢት ገላጭ አያስፍልግም። ኦዴፓ ድምጹን ለዶር አብይ አህመድ ይስጥ ወይንም ራሳቸው ያዘጋጁት አዲስ እጩ ይኑር አልታወቀም። እኔ አለ ብዬ አስባለሁኝ። 

ድሉ፤ ክብሩ፤ ፍቅሩ፤ መታመኑ ለድርጅቱ ለኦዴፓ ነበር፤ ያ ከሰማይ የወረደ የፍቅር መና ለኦሮሞ ህዝብ መሆኑ ያልጋባቸው ወገኖች አሁንም የተተረተረ ስሜት እንዳላቸው በወፍ በረር እረዳለሁኝ እኔ። ፍቅሩ ግን ለ ኢትዮጵያዊነት የተሰጠ ያም የፈጠረው ሞገድ ነው። 

እነሱ ግን ምንጩን ዘለው ሌላ ዓለም ውስጥ ናቸው ያሉት። በዚህ ላይ ነገረ ሚስጢረ ፈጣሪም/አላህም ዋጋ የሰጡት አልመሰለኝም። ቁጣ ከወረደ ከሰው ሰራሹ መከራ በላይ ነው። የእኛ መታመስ ነው ባልተለመደ ሁኔታ በዬወሩ የመሬት መራድ የሚታዬው በዚህውም ነው። የሰንደቁ በእንጅባራ የመታዬቱ ጉዳይም ሌላው እዮራዊ ሚስጢር ነው። 

የሚጠቀመው ነገር መንፈስ ሳይከፈል ታሪክን አሳልፎ ላለመሰጠት በአንድ ድምጽ ትውልድ ከቶውንም ሊተካው የማይችለውን የአብይ መንፈስ ሌጋሲ ማሰቀጠል ነው ለኦዴፓ የሚጠቅመው። በዚህ ዙሪያ የሚነሱ ያልተለመሱ ግልጽ ያልሆኑም የላተደፈሩ አምክኖያዊ የዶር አብይ አህመድ አቋሞች አሉ።

እነሱ ግን አሁን ካለው አገር የማስቀጠል ጉዳይ ጋር ሲመዘኑ የሚበልጠው ነገር አፍሪካን አንቱ ያሰኘው አቅምን ደግፎ መውጣቱ የበለጠውን እጅ ይይዛል። ሌሎች ፍላጎቶች በመረዳዳት በስክነት የሚኬድባቸው ናቸው።

ሌላው ቀርቶ ዶር አብይ አህመድ በዶር ለማ መገርሳ ቢቀዬሩ እንኳን ያን ገናና የህዝብ ፍቅር ኦዴፓ መልሼ አገኛለሁ ብሎ አያስበው። ብዙ ሰው ከፖለቲካ ትግል ራሱን ያገላል። አብይ እኮ አሁን የሁሉም ቤተሰብ ነው።  የእኛ ብቻ አይደለም የአፍሪካውያንም። የማይደንቃቸው ግድ የማይሰጣቸው ሲዊዞች እንኳን ስማቸውን ጠርተው "ካንስለር አብይ" ብለው ይጠይቁኛል።  

አዲሱ የኦዴፓ የሥም ግርፍ አዴፓም አቶ ደመቀ መኮነን የማስቀጠል ርምጃ መውሰድ አለበት። ሁለቱ ተስማምተው መስራታቸው በራሱ አንድ ትልቅ እፎይታ ነው። አቶ ደመቀ መኮነን ቅናት የለባቸውም። የግል ዝና እና ክብር አይፈልጉም። ዝቅ ብለው ለመሥራት አቅም አላቸው። አስተምረዋልም። አቶ ደመቀ መኮነን ውስጥ ለውስጥ እንደ እባብ አይሄዱም። በሥልጣኑ ቅንጣት ፍላጎት የላቸውም። 

የእኔ ቅኖች --- የሆነ ሆኖ ይህን የተለጠፉ ሊንኮችን በአስተውሎት ከቀደመው ጋር እዩት። ተንታኞች ጋባዦች አንባቢዎች ሁሉ ራሳችሁን እያስገማታችሁ ነው። የመጣው ሁሉ የሚቀመጥበት መጸዳጃ ቤት እንጂ የሰው ህሊና አይደለም።

ውዶቼ --- ለመወሰን፤ ለማመዛዘን ይህን የተለጠፈውን ከልብ ሆኖ ማዳመጥ በውሃ ቅዳ ውሃ መልስ ወጀብ ከመወዛወዝ እንድናለን። ትውልዱንን መሪ እንዳያጣ፤ ወጀብ የጥቃት ሰለባ እንዳይሆን ከማድረግ እንቆጠባለን። የተነካ ነገር የለም። ይልቁንም የጎሸ ያልጠራ ደም አለ። የጎሸ የበቀል ዛር አለ። ጎማማ የምቀኝነት እና የቅናት ጉምም አና ብሏል።

የዶር አብይ አህመድ ታማኝነት አደጋ ውስጥ የሚያገባው እሳቸውም አቶ ደመቀ መኮነን ከቦታቸው የተነሱ እንደሆነ ነው። ምክንያቱም በውስጡ ብዙ ነገሮች አሉበት። ቀድመው ቦታው ላይ ስለነበሩ የመረጃ ዲታ ናቸው። ሾላ በድፍን ሆነው የባጁ ገማናቸው ደግሞ አሉ። ቅናት ኤድስ ነው። ምቀኝነትም የጭንቅላት ኩንታሮት፤ ሴረኝነትም ልብአልቦሽ ሰብዕና።

ትውልዱ በዥንጉርጉር የዲያቢሎስ ቀመር ቁማርተኞች እና አክሮባቲስቶች ባክኖ እንዳይቀር አድብ ይኑረን - በትህትና። ጀብጅበን አድንቀን ሥማቸውን ጣሪያ ላይ አውጥትን የምንቆልላቸው ሰዎች እንኳንስ ለኢትዮጵያ ለአፍሪካም ከፍ ሲል ለሉላዊ ዓለምም የጭንቅ ወጥመድ አማራቾች ናቸው። ሚዲያ ትውልድ አንዳይባክን በሃብቱ በተፈጥሮ ቅንነት ውስጥ እንዲቀረጽ ነው መትጋት የሚኖርበት።

እናስተውል። በነፃነት ተጋድሎ ውስጥ ያሉት አሁን መዳፍ ላይ ነው ያሉት የውጮዎችም ተፎካካሪዎች አንድ ሳይቀር ልቅምቅም ብለው አገር ገብተዋል ይህ ሊጨንቀን ይገባል። እንጸልይም። 

ህዝቡም ይወክለኛል ያለውን ደስ ብሎ ተቀብሏል ያ ሁሉ ቤተሰብ ለበለሃስብ እንዳይሰጥ ከልቦና ሆኖ በተደሞ መምከር እና ቁርጥ ያለ አቋም መያዝ ያስፈልጋል።

ኦነጋውያን ራሱ ለጥቂት ጊዜ ነው የሚስማሙት ወለጋውያን፤ ሸዋዊያን አረሲያውያን፤ ባሌዋን ሆነው አቅጣጫቸውን ወደ ከፋ ማዞራቸው አይቀሬ ነው። ከፋ አንድ ነፍስ በዘመኗ አፈራች ኢንጂነር ሳይንቲስ ቅጣው እጅጉን እሱን አጣች አሁንም አንድ እንደ ወልዴ ሊሂቅ አላት አደጋ ላይ ናት። ሚስጢሩ ይህው ነው። ይገለጥ መዝገቡ ይነበብ ማለት ይህው ነው።

በዚህ ዘመን ብልህ ሆኖ የማዬው የጎጃም ሰው ነው። ጎጃም ቅኔ ነው። የጎጃምን ያህል ወዳጅ እና ጠላቱን የለዬ፤ የሃይል አሰላለፉ የገባው ጥንቁቅ ብልህ ህዝብ አላዬሁም።
  • ·       ተጨማሪ ማገናዘቢያዎች።

Hiber Special: Sadik Ahmed on Dr Abiy Ahmed & TPLF

"ተስፋና ስጋት በጠቅላይ ሚኒስቴሩ ሹመት – ከሳዲቅ አህመድ"

https://www.zehabesha.com/amharic/archives/89683

"ይድረስ ለሳዲቅ አህመድ እያየን እንራመድ !! እያስተዋልን እንተንፍስ !!"

የሙስሊሙ መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር ተገናኝቶ ተወያየ! July 4, 2018

  • ·       በመጨረሻ እኔ ይህን ጻፍኩኝ።

እነ ቢቢኤን "ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል።" ከዚህ በፊትም በሌላ እርእስ ጽፌአለሁኝ አብሶ ክብርት ወ/ሮ አና ጉምዝ "ቃል ብቻ በቂ አይደለም" ማለታቸውን አስታክኬ። ብቻ በእኛ ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ ገማና ትውልዱ መሬት ላይ ያለው ታመሰ። ጤባ ጢባ የምንጫወተው ሁላችንም በእናታችን መሃጸን አቀዳድ ላይ ነው።

አንኳንስ ፍጹም ወደር የለሽ አቅም እና ክህሎት መዳፍ ላይ እያለ ይሻላል የሚባል ነገር ከኖረ በዛ መግፋት፤ ያን ማጠናከር ቢጠቅም እንጂ አይጎዳም።
ማነው አቶ ጃዋርን የበለጠ አቅም የሰጠው ቢቢኤን እና ህብር አለነበሩንም? እሱ ለታማኝነት ከኦሮምያ ሚዲያ ውጪ በሌሎችም ያለውን እውቅና ለማመሳከር ነበር የሚጠቀምበት።

እሱ ቃለ ምልልስ የሚያደርገው በቀጥታ ለተከታዮቹ ነው። ሁሉምንም ገዝቻለሁ ተቆጣጥሪያለሁ ነው የሚለው። ደግሞም እውነቱ ነው። ሌላው ህብር የፕ/ ህዝቃኤል ጋቢሳ ድምጽ ነው የነበረው።

አሁን የሳቸው እና የፕ/ አባሳን ቃለ ምልልስ የሰማ ሰው እንዴት እሳቸውን አቅፎ ኢትዮጵያ ነኝ ሊል ይቻለዋል?! „ኢትዮጵያ ረቂቅ ሚስጢር ናት“ በሊቀ ሊቃውነቱ የታሪክ ሙሁር ፕ/ ሃይሌ ላሪቦ ተባለች ብለው ነበር ያን ያህል ሲጦፉ የነበሩት።

አማራ የለም ብለዋል ፕሮፌሱሩ። እኛ ግን  ከኢትዮጵያዊነት በላይ ስላልሆነብን ዝም ነው ያልነው። እንዲያውም እሳቸውን ወግኖ አክቲቢስት አቶ አቻምየለህ ታምሩ ይቅርታ እንዲጠዬቁ ጽፎ ነበር። እሱ እንግዲህ የተጋድሎው ራሱ አክቲቢስት ነው  - የአማራ። ግን ኢትዮጵያ በለጠችበት። ከእሷ በላይ እኮ ፈጣሪ ብቻ ነው ያለን ለኢትዮጵውያን። በሥሟ የሚቀኑ? ህም! ዕድሜ ለኦዴፓ አሁን እንደታቦት ከብክቦ ይዟቸዋል።

„ኢትዮጵያ ረቂቅ ሚስጢር ናት“ ኢትዮጵያዊ የሆነ ሁሉ በዛ ውስጥ እኔም አለሁ የማለት ዕሳቤ አልነበረንም? ኦሮሞ ኢትዮጵያዊ አይደለምን? ልባችን ገልጠው ቢዩት ምንኛ መልካም በሆነ በነበረ፤ እንዴት በውስጣችን ተደላድለው  ።

ኢትዮጵያ ሚስጥርነቷ እኮ የህዝቧ ልቅና ነው። ኢትዮጵያ የሚለውን ሥያሜ ልክ እንደ ጣሊያን ይፈሩታል ኦነጋውያን። ያርዳቸዋል። ይህን የሰማ፤ የመረመመረ ሚዲያ  ድምጽ፤ አንደበት ለእነሱ መሆን ሳስበው እራሱ አፍራለሁኝ። ዛሬ ላይ ዘመን ጥሩ ነው የዘራውን እያጨደ ነው …

እኔ ከኢትዮጵያ በላይ ማንም ምንም ክብር የለኝም። በቁሜ እያለሁኝ ጥቃቷን ማውጣት ካልቸልኩ ስሞት እንዴት ነው ኢትዮጵያዊ ተብዬ እምሞተው። በቁሜ እያለሁ ክጃታለሁ። ጥቃቷን እኮ ማውጣት እምችለው በመዳፌ ባለው አቅም መወሰን መቁረጥ ስንችል ብቻ ነው።

እውነት ለመናገር አልገባንም ስለምን እንደምንታገል እንጂ ትናንት አፍርሰን ሚሊዮን መንፈስ አሁን ደግሞ ከጎን "ነኝ" ስንል ነገም ደግሞ "አይደለንም" ስላለማለታችን ምን እርግጠኛ የሚያደር ነገር አለ። እንጽና። በመዳፋችን ያለውን እኮ እናውቀዋለን። 

እኔ ምን አለኝ ብለን እንሰብ? እኛ የለለን ክህሎት በሌላ ጸድቆ ማዬት አለመፍቀድ መቼም አለመታደል ነው፤ በአካባቢዬ ያሉትስ ምን ተወዳደሪ የሚያደርጋቸው አቅም አለ ብሎ ማጥናት ያስፈልጋል። 

ወዘተረፈ የአላዛሯ ኢትዮጵያ ችግሩ ሁሉ ይትነን ቢባል፤ ሌላው ቀርቶ አንድ ሰው ሰሌላው ጥንካሬ መመስከር እኮ ለእኛ ብርቃችን ነው? አይደል? ይህ ሁሉ መከራ እኮ አብይን ሰው ወደደው ነው። ይብቃኝ።

ዕውነትን የወገነ ብቻ የተፈጥሮው ጌታ ነው!
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።  

 




አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።