ልጥፎች

ከጁላይ 24, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ወይ ፍርጃ? ጋዜጠኛ ካሳሁን ይልማ ደግሞ ይወርድብናል? አማራን በሙሉ "ኦነጋውያን" ብሎናል፤

ምስል
መቼ ይሆን ራስን ማዬት የምትማሩት? „የብስ ለዛፍ ባሕር ለማዕባል ተስጥታለችና  ሁለቱም ፈራሽ ነገር አስቡ አልሁት“ (መጸሐፈ ዕዝራ ሱታኤል ምዕራፍ ፪ ቁጥር ፲፱) ከሥርጉተ©ሥላሴ  23.07.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ) ·        መነሻ። የኦሮሞው ህወሓት እና የአማራው ኦነግ | ካሳሁን ይልማ http://www.zehabesha.com/amharic/archives/93107#comments ·        ሰሞኑን። ሰሞኑን አንድ ጹሑፍ የኢሳቱ ጋዜጠኛ አቶ ካሳሁን ይልማ አስነብቦናል። እርእሱ ዱላ ይባል፤ መዶሻ ይባል አይታወቅም። በቃ እልሁን እስኪበቃው ድረስ ነው የተወጣበት። ያጣው ነገር አለ ማለት ነው። የፖለቲካ ድርጅት እና ማህበረሰብም ጽንሰ ሃሳቡ ተደባልቆበታል። „የኦሮሞው ህውሃት እና  የአማራው ኦነግ“ ይለናል።  ለነገሩ ብረት መዝጊያ የሚሆን ምንትሶ ካለ ምን አለ? መንበር እንዳወጣ ነው… የሚታደለው።  የፖለቲካ ድርጅቱ ይህን እንኳን አንድ ፓርቲ እና አንድ ማህበረሰብ ወይንም ህዝብ ምን ማለት እንደሆነ አላስጠናውም። ምን አለ የቤተመንግሥት ሰውነት ይህችን እንኳን አጣርቶ ቢያስተምረው? ግን ምን ይሆናል ባቋራጭ ሰው ካሰበው የእግዜሩ አሸነፈ እና የሚሆነው ሆነ። ነገም ምን ሊሆን እንደሚችል አይታወቅም … ኦነግ የፖለቲካ ድርጅት ነው። አማራ ደግሞ ማህብረሰብ ነው። የራሱ ሥነ ልቦና፤ የራሱ ባህል፤ የራሱ ቋንቋ፤ የራሱ ወግ እና ልማድ፤ የእኔ የሚለው ማንነት  ወዘተ ያለው ...  አማራው ሁሉ ኦነግ ሆነ ነው የሚለን አቤቶው ጋዜጠኛ አቶ ካሳሁን ይልማ። ልክ የወያኔ ሃርነት ትግራይ አማራ የሆነ ሁሉ "ግንቦት 7 ነው አሸባሪም ነው" እንደሚለን ማለት ነው።