ወይ ፍርጃ? ጋዜጠኛ ካሳሁን ይልማ ደግሞ ይወርድብናል? አማራን በሙሉ "ኦነጋውያን" ብሎናል፤

መቼ ይሆን ራስን ማዬት የምትማሩት?

„የብስ ለዛፍ ባሕር ለማዕባል ተስጥታለችና
 ሁለቱም ፈራሽ ነገር አስቡ አልሁት“
(መጸሐፈ ዕዝራ ሱታኤል ምዕራፍ ፪ ቁጥር ፲፱)
ከሥርጉተ©ሥላሴ 
23.07.2018
(ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ)


  • ·       መነሻ።

የኦሮሞው ህወሓት እና የአማራው ኦነግ | ካሳሁን ይልማ
  • ·       ሰሞኑን።

ሰሞኑን አንድ ጹሑፍ የኢሳቱ ጋዜጠኛ አቶ ካሳሁን ይልማ አስነብቦናል። እርእሱ ዱላ ይባል፤ መዶሻ ይባል አይታወቅም። በቃ እልሁን እስኪበቃው ድረስ ነው የተወጣበት። ያጣው ነገር አለ ማለት ነው። የፖለቲካ ድርጅት እና ማህበረሰብም ጽንሰ ሃሳቡ ተደባልቆበታል። „የኦሮሞው ህውሃት እና  የአማራው ኦነግ“ ይለናል። 

ለነገሩ ብረት መዝጊያ የሚሆን ምንትሶ ካለ ምን አለ? መንበር እንዳወጣ ነው… የሚታደለው። የፖለቲካ ድርጅቱ ይህን እንኳን አንድ ፓርቲ እና አንድ ማህበረሰብ ወይንም ህዝብ ምን ማለት እንደሆነ አላስጠናውም። ምን አለ የቤተመንግሥት ሰውነት ይህችን እንኳን አጣርቶ ቢያስተምረው? ግን ምን ይሆናል ባቋራጭ ሰው ካሰበው የእግዜሩ አሸነፈ እና የሚሆነው ሆነ። ነገም ምን ሊሆን እንደሚችል አይታወቅም …

ኦነግ የፖለቲካ ድርጅት ነው። አማራ ደግሞ ማህብረሰብ ነው። የራሱ ሥነ ልቦና፤ የራሱ ባህል፤ የራሱ ቋንቋ፤ የራሱ ወግ እና ልማድ፤ የእኔ የሚለው ማንነት  ወዘተ ያለው ...  አማራው ሁሉ ኦነግ ሆነ ነው የሚለን አቤቶው ጋዜጠኛ አቶ ካሳሁን ይልማ። ልክ የወያኔ ሃርነት ትግራይ አማራ የሆነ ሁሉ "ግንቦት 7 ነው አሸባሪም ነው" እንደሚለን ማለት ነው።   

አርበኛ አንዳርጋቸው ጽጌን ገዳዩ ጎንደሬ ነበር ተመርጦ በድርጅታዊ ሥራ የጎንደርን ሥነ ልቦንን አቅዶ ለመቀጥቀጥ የተዘጋጀው፤ ወያኔ ደግሞ ማን ቢወልድ ማን ቢባል መልስ የለውም ግንቦት 7  አማራ ለዛውም በበዛ ሁኔታ የጎንደሬዎች ድርጅት ነው ሲለን። ያን ጊዜ ዜናው ሲሳራ የጎንደር አርበኛ አንዳርጋቸውን ጽጌን በገዳይነት የተጨመረው የዓለም ዓቀፉ ውርስና ቅርስ ፋሲል ግንብም የገዳዮች ባዕት ተብሎ ነበር። ከጎንደር የተፈጠረ ምን የማይከሰከስ፤ ምንስ የማይቀጠቀጥ አለና?  

አሁን ያን የሚመስል ቁርጥ ያለ ትንታኔ ነው እዬተሰጠን ያለው። አማራው ሁሉ በኦነግ ዓርማ ሥር ተጠቅልሎ ኦነጋውያን ተብለናል። ለጥ ብለን እናመሰግናለን¡ አለን ለኤክስ የቤተመንግሥቱ ተስፈኛ።
  • ·       ምንህ ተነክቶ ጌታው።

ስለ አንተ የቤተሰብ ንግሥና ውርስና ቅርስ አማራ ይሙት፤ አማራ ቀራንዮ ይዋል፤ አማራ ዕጣው ኦሾትዝ ይሁን። እናንተ ሞገድ ላይ አለን ትላላችሁ ወያኔ እዬተቀበለ ያርድላችሁዋል። ሠርግ እና ምላሹ ይሄው ነው። ውሉ የደም ቅልቅል እና የስቃይ ግጥግጥ ...  

ለመሆኑ በአንተ ቀዬ ላንተ ንግሥስና እንዲህ ዓይነት የጅምላ የክርስቶስ ስቃይ የተቀበለን አለን? ህሊና አለህን ይህን ህዝብ እንዲህ ላይ ታች አድርገህ ለመናገር? ለዛው ለአንተ ነፃነት ሞቶ ደሙን ከፍሎ ድርጅትህን ራሱ ነፃ ያወጣው የአማራ የህልውና ተጋድሎ ነው። እጅህን መሰስ አድርጎ ያወጣህም ደሙን የገበረበትን ከ35 ዓመት በላይ ያደራጀውን የ ኢትዮጵያ እርበኞች ግንባርን አስውጦ ነው።

ሌላው ግን ከአማራ ውጪ ኦህዴድ አንዲት ስንዝር አይንቀሳቀሳትም ነበር። ገዱ እሺ ባይል ይህ ድል ከህልም የሚያልፍ አልነበረም። ወደፊትም በዚህ አያያዙ አዲሱ ካቢኔ ነገረ አማራን እዬዘለለ የተጋድሎውን ዕውቅናውን እየነሳ ከሄደ አይቀጥልም። 

ሌላም ውጪ አገር ፕሮ ግንቦት 7 እስከ ሚዲያው፤ ካድሬዎቹ፤ የራሱ  የኦሮሞ ኔት ወርክ ሆነ አክቲቢስቱ አልነበረም ከጣና ኬኛ ጀምሮ እስከዚች ሰዓት ሌት እና ቀን የተፈለመው፤ የአማራ ልጆች ነን።

የኛ መከረኞችማ ይህ ነው ውሏቸው... ለዝብሪቱ በቀል ሰለባነታቸው። 

የታራሚዎች -ሰብአዊ አያያዝ ላይ የህግ ባለሙያ አስተያየቶች፡፡ በአማራ ቴሌቪዥን

የታራሚዎች -ሰብአዊ አያያዝ ክፍል-2 በአማራ ቴሌቪዥን

የታራሚዎች -ሰብአዊ አያያዝ ክፍል-1 በአማራ ቴሌቪዥን


ምን አለ ብትተውን እንደ አገር ልጅነት እንኳን መሞከሪያ ጣቢያ ስላደረጋችሁን ፈጣሪ ፍርዱን ይሰጥ ብለን፤ ዳኝነቱተን ለእሱ ሰጥተን ብንቀመጥ?

ምን አለ እኛን ከመከራችን ጋር እርስት ቢያደርጉን የግንቦት 7 ካድሬዎች ጋዜጠኛች እና ጸሐፊዎች? መቼ ነው ከራሳችን ላይ የሚወርዱት እነዚህ ሰዎች? የኦነግን መንፈስ መላ አማራ ህዝብ ወረሰ እንዴት ይባላል?

እንዴትስ ያለ ድፍረት እንዴትስ ያለ ነውር ነገር ነው? አማራ በሙሉ በኦነግ ደንብ፤ ፕሮግራም ይሰዬማል። እውነት መርዙ እንዴት አድርጎ ውስጣቸው ቢቀመጥ ነው እንዲህ ያል መከራ የሚያወርዱብን? ለነገሩ ከፍጥረተ ፕ/ መስፍን ወልደዬስ ምን ሊጠበቅ? 

የጥጋብ አለው ዓይነት፤ የትቢትም አለው ዓይነት፤ የማንህሎኛነትም አለው ዓይነት፤ የዚህ ሰውስ እጅግ በዛ። ከረፋም።

አማራን ማህበረሰብ ምን ቢደፍረው ነው እንዲህ አውርዶ የሚጠቀጥቀው? ምኑ ነው እንዲህ የሚያቀናጣቸው? ፈጣሪ ይመስገን እነኝህ ሰዎች እኮ ሥልጣን ይዘው ቢሆን ኖሮ አማራ ምን ሊሆን እንደሚችል ከዚህ በላይ ምስክር የለም። እንዴት አደርጎ ነው በጥርሱ ያያዘን። እዚህስ ማነው አገለጋዩ ያው አማራ አይደለምን?  

ባለፈው ጊዜ ኮ/ ደመቀ ዘውዴ ከእስር ሲለቀቁ እንዴት አካሉን አላጉደላችሁትም፤ እንዲህ ለመልቀቅ ከሆነ ስለምን አሳራችሁት የሚል አንድ ጹሑፍ አውጥቶ ነበር ዘሃበሻ ላይ አንብቤያለሁኝ። ለእነሱ መያዦነት አርበኞቻችን ሲለቀቁ በምን ያካክሰው ቁጭቱን። 

እሱማ ምኑ ተነክቶ? የቤ መንግሥቱ ባለሟል ስለሆነ ጎንደር ማገዶ ያቅርብለት እንጂ? ከዘመነ ኢህአፓ እስከ ግንቦት 7። ስለነገም ደግሞ አስከ ግንቦት 7 ሰማያዊ። ዘመን ይዞ እስከ ዘመን የጎንደር እናት የልጅ ልኳንዳ ቤት ትክፈትላቸው እንጂ። የጎደለበት የለ። እዛም መከራ እዚህም ተሰደን መከራ።

አሁን ደግሞ መከራውን ችሎ ለተሸከመ ህዝብ ይህም አስቀንቶት „የአማራው ኦነግ“ ይለናል። ለእሱ ነፍስ እራሱ አማራ ተሸክሞት የኖረው ዘላቂ የደም ግብር ነው ለዚህ ዛሬ ኢትዮጵያ ለሚለው ትንሳኤ የተደረሰው። ለእሱ ድርጅትም ባለወግ እና ባለማዕረግ ያደረገው አማራ ነው። ለጫካውም ሆነ ለቴሎፎኑም ትግል። ይታወቃል እኮ ዘመን ይዞ አስከ ዘመን የሰው ልጅ እስከ አገለገለ ድረስ እንጂ፤ ከዛ ባሻገር እንደ አሮጌ አካፋ እና ዶማ እንደሚወረውር … ተኑሮበታል። ይሉኝታም ማተብም እንደ ሌለ። 
  • ·       „የኦሮሞው ህውሃት።“

የእነ ለማና ዶክተር ዐቢይ ቅን እና ሀገራዊ መፍትሔ ያነገበ እንቅስቃሴ“ የሚገርመው በዚህ ሃሳብ ውስጥ የገዱን ቅን መንፈስ ማንሳትን አልደፈረም፤ ከአንድ ወንዝ መቀዳት እንዲሉ ... የጋብቻው ጉዞ ወደዬት እንደሚያመራ ግልጥ ነው።

የሆነ ሆኖ ተቀርኖው "ሆድ ያባውን ብቅል" እንዲሉ ነው። ባንድ በኩል እነ ዶር ለማ መግርሳ እና ዶር አብይ አህመድ "ቅን ጉዞ እያደረጉ ነው" ይለናል፤ በሌላ በኩል ደግሞ "የኦሮሞው ህውህት" ሲል ይወነጅላቸዋል። እንሱን ከማህበረሰቡ ወይ አግልሏል፤ ወይ ደግሞ እንሱም የህውህትን መንገድ ተከታዮች ናቸው ነው የሚለን። 

ይህም በራሱ የተፋለሰ ነው። ወይ ደግሞ እንደ ተለመደው የጋዜጠኛ መሳይ መኮነን ውስጠ ወይራ ዘይቤ ነው። ወያኔ ሃርነት ትግራይ ኦሮሞን ሁሉ "ኦነግ እና አሸባሪ" እንደሚለው መሆኑ ነው። አሁን የግንቦት 7ቱ ጋዜጠኛ አቶ ካሳሁን ይልማ የሚልን ይሄንኑ ነው።

ህውሃት ድርጅት ነው፤ ኦሮሞ ደግሞ ማህበረሰብ ነው። ያ ከእግሩ ሥር ወድቃችሁ ምን እንርዳችሁ? ምን እንዳርግላችሁ፤ ተወልድንበታል ብላችሁ ተንበርክካችሁ አቅም ስትለምኑት የነበረው ነው ኦሮሞ ማህረሰብ ማለት። ብቻ ይሄ ኢትዮጵያዊነት የሚለው መከራ ስንቱን ገመና ተሸክሞ ፍዳ ሲከፍል እንደኖረ ያሰዝነኛል። ወደፊትም ያለበት መከራ እንዲህ ልብ የሚያስጥልም አይደለም፤ ዘመን ይፈታው ይሆን?
  • ·       ሲያጣ የተጦመውን።

ዛሬም ያለበራው የግንቦት 7 ካድሬ እና ሚደያ ታግሎ ታግሎ አልቻለው ሲል በሩብ ልብ የአብይ መንፈስ ደጋፊም ተሁኖ፤ በአንድ ጹሁፍ ድጋፍ እንደገናም ስንጥቅ፤ በአንድ ቃለ ምልልስ ድጋፍ እንደ ገና ስንጥቅ። ወይ ለይቶለት አይቃወሙት፤ ወይ ለይቶላቸው አይደግፉት ወጋ ጠቀም በላ ጉዞ ይሄው ብራናም፤ ማይክም ይታመሳሉ። መንፈስም ሲተረተር ውሎ መሽቶ ይነጋል። አለመታደል!

ነገም የአብይን መንፈስ አሜሪካ ላይ በምን እና በምን ሁኔታ እንደሚስተናግድ የሚታይ ነው። የእሱን ድርጅት አስከ ካድሬዎቹ ምን ሲሰሩ እንደ ባጁ ልቦናው ያውቀዋል። የለማን እና የአብይን ፎቶ መለጠፍ እኮ ወንጀል ነበር። መቼም ይሄ አሊ አይባልም። የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስተር ነበር ብሎ ዜና ለመሥራትም ጭንቅ ነበር። 

ባለፉት ዓመታትም የኦሮሞን ንቅናቄ ስንት ጊዜ ቃለ ምልልስ ሲያደርግ የሲያተሉ የአማራ ተጋድሎ ጉባኤ ምኑም አልነበረም ለቤተ መነግስቱ ጋዜጠኛ። ተጋድሎ ምን ያህል ግለት በእሱ አቅም እንኳን እንደነበረበት ያውቀዋል። ለእሱ ድርጅት ደግሞ አማራ ሁለመናው ገብሯል። ይደገማል ባዶ እጅ ተይዞ ተሄዶ ለዛ "የትጥቅ ትግል" ለምትለዋ ተራራ ምኞት ለወግ የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር ለኩራት ያበቃ ነው። በውጪም ሌት ተቀን ደካሚው አማራ ነው። አማራ ከዛ እዬነገደ ከዚህ የነፃነት ተጋደሎ ምርጥ ጋዜጠኛ አይደለም። መንገዱም ፍቅሩም ... 

አሁን የአብይ መንፈስ በእናንተ ዘንድ "ቅን ነው" ተብሎ ሊታሰብ። ከትከት ነው፤ አርኬብህን ዘርግፈው እና አይደለም ስንኙ ድምጹን አጥፍተህ ብትመለከተው ምን ያህል የለማ መንፈስ ይነዝራችሁ እንደነበረ ማዬት ነው። አሁንም መረጃ በመጣ ቁጥር ምን እና ምን እዬተኮነ እንደሆን እኮ አስተርጓሚ አያስፈልግም። 

የተባጀውን ሁሉም ያውቀዋል። ዛሬም "እንዳያማም ጥራው እንዳይበላም ግፋው ጉዳይ" ያን በመረዝ የተለወሰ ውይይት፤ ያ በመርዝ የተለወሰ የብዕር ፍሰት እኮ ህሊና ያላቸው ኢትዮጵውያን ይታዘቡታል፤ ይመዝኑታል። ወደፊት ደግሞ አሳላፊ መሆናችሁን እናዳምጣለን፤ በደስታ ተዋጥንም እያነበብን ነው: ከዛም ቀጥሎ ሌላም መርዝም የተለመደ ነው። ስንቶቻችሁ ትሆኑ በአክሮባቲስትነት የሰለጠናችሁት?
  • ·       የራሷ ሲያራባት አይሆንምን? 

የኢሳቱ ጋዜጠኛ አቶ ካሳሁን ይልማ የአማራ ታታሪዎችን፤ ድርጅቶችን ይመክራል። ጠላት ግጭት አታብዙ በማለት። በመርህ ደረጃ ትክክል ነው። እኔም እጋራዋለሁ። ግን ኢትዮጵያዊ ይሉኝታ የሚባል ብሄል አለው ሌላ ዓለም ያልታደለው። 

እናም ግንቦት 7 ከተፈጠረ ጀምሮ ያልተጋጨው ድርጅት አለን? ያልተተናኮለው ግለሰብ አለን። የትኛው ድርጅት፤ የትኛው የልዩነት ሃሳብ፤ የትኛውን የሙያ ሊሂቅ ማለቴ የተለዬ ሃሳብ ያለውን፤ የትኛውን የተለዬ አቋም ያለውን ጋዜጠኛ እና የሰብዕዊ መብት ተሟጋች አቅርቦ፤ አወያይቶ ነው ድርጅቱ? ከዬትኞቹ ጋር ተሟግቶ? አሸንፎስ ተሸንፎስ? አስቁሙሉን ነው። ልመና። ሳይቻል ሲቀር ደግሞ ማህበራዊ መሠረትን ከሥር መሰረት በዘመቻ ንቅልቅል ማድረግ። በቃ ድሉ የተባጀው ክፍጥረት እስከ ... 

በቃ ይሄው ነው የፖለቲካ ድርጅቱም የተቋማቱም ዋና የግብ አውታር። አለንበት እኮ። እንመሰከርለን። ሲፈጠር ግንቦት 7 ከታች አስከ ላይ የሚበልጠውን አቅም ለመቀበል ፍርፋሪ ብልህነት አለውን? አቅም ብቅ ሲል ሲነቅል፤ ጦርነት ሲከፍት፤ ሲበትን ነው የኖረው። ወደፊትም ይሄው ነው። ከዛ ለመታረም ይቅርታውን አላዳመጥንም እና። የዲያስፖራው ንጉሥ ሆይ! እኮ እሱ ነው የነበረው ... አሁን ደግሞ ሁሉንም እንደበተነው ግንቦት ሰማያዊ ሊሆን ነው ...   

ለነገሩ የማይገፋው የለማ ገዱ መንፈስ ገትሮ ያዘ። አሁን እኮ የማይችለው ሆኖበት ነው ግንቦት 7። ለዛውም እስከዚችህ ደቂቃ ድረስ በመነጠል ፖለቲካ ነው ትጋቱ። ተፈጥሮው ይሄው ነው የአውራነቱ። ጊዜ እያለፈው እዬሄደ እንኳን ሰዎቹን ገርቶ መስመር ለማስያዝ አላስቻለውም። ተዛናፍ ምልከታዎችን ገርቶ ወጥ መንፈስ አምጦ ለመወልድ አልተቻለውም። ስለዚህ ሌላውም ይህን ቢደግመው አገር መሪው አውራው የሽገግር መንግሥት ቁንጮ ትንሳኤና ህይወት የተባለውን አሉታዊ አብነት መከተሉ የተገባ ነው፤ ተከተል አለቃህን ነው እና ...
  
እንደ ሹልክታ ጨወት።

የፓርቲውም ስብሰባ እያዳመጠነው ነው፤ ድርጅታችን ትኩረት ነሳን ብቻ ሳይሆን በሁሉም ነገር የሚያነስን ሥም እንደ አጀንዳ እዬተነሳ እግዚኦ የሚሉ አባሎች እንዳሏችሁ እናውቃለን፤ ለዛውም በብሄራዊ ደረጃ። ታችማ ተለምዷል። እኔን ስሰማ የሚገርመኝ መከከላኛው አፍሪካን ሊመራ የታሰበ መንፈስ አንድ አክቲቢስት ለዛውም ወጣት የፈለገውን ቢል ሙግቱን ችሎ ሆኖ መገኘት ነበር ከዛ ጋር አቲከራ ከመግጠም። ነገም እኮ አገር ለመምራት ሙግት ተፈርቶ አይሆንም። አሁን እሳት የላሰ ትውልድ ነው ያለው። 

ስለሆነም ጋዜጠኛ አቶ ካሳሁን ይልማ አንተም ከዘር ሐረግ ጣዖታዊ አምልኮ ውጣ እና ወደ ተቸረህ ክብራዊ መንበር ጋዜጠኛ ስለሚባለው ሙያዊ ምግባር ትንሽ ተማር ፊደል ቁጠር። ጠረባህ ሁሉንም ነው። አንተ በዛ ውስጥ ሰጥመህ ሌላውን ግን እእ። መጀመሪያ ድርጅትህንም ራስህን ድፈር እና ለማረም ሞከር። ስንት ህግ እንደምትተላለፍ እውቅ።

ስለ አማራ ተጋድሎ ለመተቸት እኮ እውቅና ሰጥቶ ነው። ከዚህ ተጋድሎ በሆዋለ ለነገሩ ብዙ ነገር ቀረ። ማንጠፍ፤ መጎዝጎዝ፤ ማንገት፤ ማሽቃበጥ ወዘተ …. ጊዜም ጥሩ ነው በጭምትነት ውስጥ ልዑል እግዚአብሄር ዝቅ ዝቅ ያሉትን ከፍ፤ ከፍ ያሉትንም ዝቅ አደረገ እና ዓይናችን ገድል አሳዬን። ተመስገን!

እትጌ ኤርትራም ልበ ብርሃን ወዳጅ ገጥሟት አጥታው ከነበረችው ደስታ ጋር በእልልታ ተገናኘች። ጥርስንም አዬነው። የስጋት ምንጭ በመሆን በግርግር ሥልጣን ሲታሰብም ግብጽም "በአላህ እስቲ ማልልኝ" ፍቅር እጬጌ ሆነ። ሌሎች የፖለቲካ ሚስጢሮችም ቢኖሩበትም። 

አሁን ከሰሞናቱ ደግሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ደግሞ ክብሯን በባዕቷ በእልፍኟ ሐዋሪያዊትነቷ ይረጋገጣል። የዚህ ሁሉ ቁንጫን እንኳንስ ይሄ ሌላም ያስብላል። አዎን! የአማራ ተጋድሎ „ደምህ ደሜ ነው" "ጣና ኬኛን" ወልዶ ለምቶ በገድ ድል መንበሩ ላይ ሆነ። ምን ያህል ዕድሉን ያገኘው ለውጥ ለአማራ ተጋድሎ ልቡን ይሰጣል? አይታወቅም። አማራ ላይ ሲሆን ዕድል ፊቷን ታዘራለች። ግን የዛኑ ካሳ ደግሞ እዮር በረቂቁ ያስታጥቃል።
  • ·       በላጩ ወገብን ታጠቅ!

ተእንግዲህ እድሜ ልክ ተጠግቶ፤ ተጠልሎ፤ የሆነ ነገር ተደግፎ ሳይሆን ሞጥሮ ራስን ችሎ ታግሎ ያው የታለመውን በታለመው መልክ መከውን የተግባር ልዑላን ጉዳይ ነው። አቋራጩ ባቋራጭ ተጎምዶ እህል ውሃው ውሃ የበላው ቅል ሆነ። 1500 ድምጽ እንኳን ጠፍቶ ሌላ ዛንጊባ ጠርዝ ላይ ስለመገኘቱ ተደምጧል። ነገም ቢሆን አልጋ ባልጋ የሚሆን አይመስልም። ስለዚህ ጠበቅ አድርጎ መታጠቅ በስንት ጣሙ ብለናል ... 

የአብይን መንፈስ የደገፈው አማራ ነው። ድምጹን ሰጥቶ ሥልጣነ መንግሥቱን ያደላደለውም አማራ ነው። ተጋድሎ እንኳንስ ለራሱ ለሁሉም ተርፎ ልዕልት ኢትዮጵያ ለወግ ለማዕረግ በቅታለች። አማራ ተንቆ፤ ተረግጦ የትም አይደረሰም መቼውንም ቢሆን። 

ይህ ከሰው ልጅ የበለጠ አቅም ኑሮ ሳይሆን ንጽህና እና ቅንነት የሰጠው ትሩፋት ነው ለአማራ። እርግጥ ነው ለተጋድሎው ዕውቅና የተገባውን ያህል ተሰጥቶታል ከምል አልታሰበበትም ማለቱ ይቀላል። የለማ ቡድን ጥድፊያ ላይ ነው የራሱን ቤት በተሟላ እልፍኝ ለማደራጀት ለመምራት በተስፋ ዝማሬ ላይ ነው። በጥንድም በትረ መንግሥቱን እዬመራ ነው። የገዱ ቡድን ደግሞ ጆንያ ሙሉ ቫልዬም ገዝቶ ለሽ ብሏል።
  • ·       የግለሰብ ነፃነት።

መቼም ድርጅትህ በግለሰብ ነፃነት ላይ የተመሰረተ መርህ እንዳለው ይታወቃል። ምን ያህል ድርጅቱ ውስጥ ወደ ተግባር ተሸጋጋሯል ለሚለው አባል ሆኖ ማዬት ነው። የሆነ ሆኖ አንድ በግለሰብ ነፃነት የሚያምን ድርጅት ሌላው ያለው መብትንም መንፈግ የተገባ አይደለም። ዛሬ ቢቀር ድንገት ነገ ቤተ መንግሥት ድርጅትህ ከገባ፤ ወፍ ካወጣችሁ ከአሁኑ መለማመድ ይበጃል።

ቢሆን ብሎ አለመለማመድ እኮ ነው አሁን ያወራጨው። እኔ ፕ/ አሳያስ አፈወርቂ መንግስታቸው ቢገለበጥ፤ ወይም ከወያኔ ሃርነት ትግራይ ጋር እርቀ ሳላም ቢያወርዱ፤ በድንገት አንድ ነገር ቢሆኑ ብላችሁ ሁሉ እሰቡ ስላችሁ ነበር። አሁን የሆነው ይሄው ነው።

በሌላ በኩል ሌላ አቅም ያለው በዬትም ጊዜ ሊፈጠር እንደሚችል ስላልተገመተ ነው አሁን ያለው ጭንቁ። የመርዶም አለው አይነት ተደራረበባችሁ። ብቁ የሚባሉ ጋዜጠኞች እራሳቸው ፈተና ውስጥ ናቸው። ከአመለኩት ጋር ማነጻጻር የማይቻለበት ሁኔታ መፈጠሩ ለማድመጥ አቅም አንሶ አይቻለሁኝ። ምንድን ነው ይሄ? አስቀድሞ ለማየት ዕድሉ አለመኖሩ ነው …

የሆነ ሆኖ በግልሰብ ደረጃ ሌላው መብት እንዳለው ሁሉ የአማራ ልጆችም ባለመብት ናቸው። የፈለጉትን መከተል፤ ያልፈለጉትን መሞገት ይችላሉ። ተከታይ ካላቸው ካገኙ ጉዳዩ የእነሱ ነው እንጂ የኢሳት ወይ ግንቦት 7  የእነሱን ፍላጎት የመምራት ሥልጣን መብትም የለውም። 

አንድ ሰው አንድ ድምጽ አይደለምን የምትሉን? የግልሰብ ነፃነት አይደለም የምትሉን? እኔንም እንድትመሩኝ አልፈቅድም። አቅም ሲኖራችሁ ራሳችሁን ችላችሁ በሁለት እግራችሁ ቁማችሁ፤ እንደ አንድ የፖለቲካ ድርጅት የራሳችሁ ተግባር እናንተኑ ሲገልጥ፤ እናንቱን ሲያበለጽግ፤ እናንተኑ ሲያስነብኝ ፕሮፖጋንዲስት አልፈልገም እራሴው ምራኝ፤ ንዳኝ እላለሁኝ … ዘመን ባሾለከ ቁጥር ደባል እዬተፈጠረ ታቱ ለሚበላው ግን ትምክህትን ማባክን ይሆንብኛል።

ዴሞክራሲ እኮ ይሄው ነው፤ ሁሉም ፍላጎቱን ይዞ ይመጣል በድምጽ አሸናፊው ገዢ ይሆናል። ስለዚህ መብታቸው ነው። ስለ አብይ መንፈስ እና እርምጃ መብረቅ የሆነው ለእናንት አንጂ እኛም ሞግተን እረታናችሁ እኮ። አንድ ለሺህ … አዎና! ያልተሸናፋችሁበት የብራና ዓወድ የለም። በዜሮ ነው የቀራችሁት።

ይልቅ አሁን በዚህ ህውከት በአማላጅ ደጋፊ ሆነችሁ በሦስት ቀለም የተዥጎረጎረ ቀለም ከምትታመሱ መሸነፋችሁን አውቃችሁ፤ ብጥበጣችሁን ተግ ብታደርጉት ጥሩ ነው ይበጃል። 

አሁን የዶር አብይ አህመድ ጠ/ ሚር ለግንቦት 7 ለኢሳት ተመችቶ ነው "ቅን ጉዞ" "የእኛ ወገን አብይ" የተባለለት? የዘመን የውስጥ በሽታ የሸለመ ጉዳይ ነው። እናንተ 4 ኪሎ ስታስቡ ጀግናው ኤርትራ ገብቶ ኤርትራንም አስደምሮ አሸልሞ ቁጭ አለ። ቅኖች እንዲህ ናቸው መንገዳቸው ራሱ የቀና ነው … መጨረሻውን ካሰመረላቸው፤ በልክም ለመያዝ ሰው የሚለውን ካዳመጡ ... ትእግስት ሲያልቅ ፍቅር እንደሚሰደድ የሂደት እርካብ ስለሆነ ... 

ዘመነ ቅኖች ነው … ቅንነት በቀናችሁ ጹሙ ጸልዩ ስገዱ ውደቁ ያው የተዋህዶም ልጅ ስለሆንክ ልጅ ጋዜጠኛ ካሳሁን ይልማ ድንግልዬን ለምናት መልካሙን መንገድ እንደትመራህ። 

ሌላ ደግሞ ፖለቲካ ስለሚባለው ፍልስፍና ትንሽ የፊደል ገበታ ግዛ። የፖለቲካ ሙያ ጎርፍ በቅል አይደለምና። ማህበረሰብ እና የፖለቲካ ድርጅት ማለት ይህን ያህል ዘመን ድርጅት አላስተማረህም እና …. 

ሌላው ግን ከአማራ ህዝብ ራስ ውረድ፤ ልክህንም እውቅ። ጎንደሮች "ልክን ማወቅ ከልክ ያደርሳል" ይላሉ። የዛሬ ሁለት ሦስት ዓመት እና ዛሬ ያለውን ልካችሁን እስቲ መዝኑት … ተው እዬተባላችሁ የሄዳችሁበት መንገድ ምን ያህል አክሳሪ እንደሆነ …

ዲታ በመንፈስ የነበረ ድርጅት ከኛው ጋር ተጋጨ ንጹህ መንፈስ እዮርን አቤት አለ ምላሹ ደግሞ የሆነው ሆነው። ምን አለ ዝም ብትሉ አሁን እንኳን። ያን ያህል በሌለ ተስፋ ሚሊዮን አስረግዶ እንዲህ ባዶ እጅ ሲቀር ልብ የሚያስነፋ ምንም የለም። 

… ብቻ ትእግስት ሲያልቅ ፍቅር የተሰደደው ቀድሞ ሆኖ ነው እንጂ በዛ በነበረው የተስፋ ሙቀት ቢሆንማ ኑሮ እኔ የውነት በሽተኛ ነበር የምሆነው።

 …. ነገ የማይገኝ ድርድር ተክቦ ተክቦ ባዶ እጅ። ሌላ ቦታ ሄደህ መለጠፍ፤ ሁልጊዜ ጥገኝነት …. ሁልጊዜ የተጣደ ፍለጋ፤ ሁልጊዜ የሞቀ ቤት ማሟሟቅ ብቻ ዕድሜ ለ2015 የፍንድ ራይዚንግ ስብበባችሁ፤ እስቀድሜ መወሰኔ ጠቀመኝ እንጂ አዘኔ የምር ነበር የሚሆነው። ስለምን? ዕድልም የነፈገችው ነፍስ ነው ግንቦት 7። መካሪ ስሌለው።

ብቻ ቁምነገሩ የዛሬው ጹሑፌ ከራሳችን ውረዱ …. ተውን ነው … በቃን ነው … የአብይን የለማ መንፈስ ቅናዊነት በሚመለከት ጨርቃችሁን ጥሎ አሳብዷችኋዋል፤ ይህን የሚደያችሁ ታዳሚ ሁሉ አሳምሮ ያውቀዋል። 

እኔን እራሱ ምነው ህልምሽ ሲለመልም፤ ለአዲስ ገቦች የሳተናው ብራና ለቀቅሽ ሁሉ የሚሉኝ አሉ። 

የአሁኑ "ቅኖች ናቸው" „ወደሽን ቆማጤ ንጉሥ ትማርቂ ነው“ ደግሞ እጃችሁን መሰስ አድርጋችሁ አውጡን አማላጅ ተሰዶ ሌላ ምን ሊባል ኗሯል …. ፉከራው እማ ያው ኔት ላይ ባክኖ ቀረ ከሰመ!

በድጋሚ ከአማራ ራስ ወረድ በሉ! አሁንም እኛ እንባ ውስጥ ነን። የአማራ እናት እንደ ሌላው አልደላትም። ሌላው የታደለው የድል አጥቢያ ወላድ የሆነችው ይድላት፤ ልጆቿ በአንድ ቀን ፉከራ ዕውቅና ይሰጣቸው። አማራ እናት፤ እህት፤ አክስት፤ ሚስት፤ የነፃነት አርበኛ  … እሷማ የተረሳች ምስክኔታ …
  • ·       በመጨረሻ።

ጀምለህ አማራን "ኦነጋውያን" አልክ። ሰፊውን ቅን ህዝብ አንዘግዝገህ የትሜና አዋርደክው፤ ለይተህ እነማን እንደሆኑ ብታብራራው እነሱም ቢሆኑ በሚያነሱት ነገር ውስጥ ፍሬ ነገር ሊኖረው ስለሚችል ግፍቼ ልሞግትህ እችል ነበር። እኔም እራሴ በቀጣይ ጹሁፎች የማነሳቸው ነጥቦች ስላሉኝ።

ቅን ስለሆንኩኝ በቅንነት የደገፍኩትን፤ የተሟገትኩለት የኦህዴድ መንፈስ ክፍተት ሲኖርበት በቅንነት ውስጤን ማሳዬት ግድ ይለኛል። ስለዚህም ቀጣይ ጹሁፌ ይሄው ይሆናል። 

ምክንያቱም አማራነቴን ከእንግዲህ የምሰርዘው አይደለምና። የማያቸው እጅግ የጎሉ ግድፈቶች አሉ። እዮባዊነት መልካም ስለሆነ ነው በመልካም ነገሮች ላይ ስተጋ የከርምኩት። ካቢኔው እዬተደላደለ ስለሆነ ሙግቱ ቀጣይ ነው … የሰፋ እጅግም ሊስተዋል የሚገቡ አመክንዮዎች ስላሉ።

„አማራነት ይከበር“
„እንከባበር“
 የኔዎቹ ማለፊያ ጊዜ ኑሩልኝም።


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።