ልዑል አስፋው ወሰን አስራተ ካሳ "ተደመሩ!" ድንቅነት በድንቅነሻዊነት!
ልዑል ዶር አስፋው - ወሰን አስራተ ካሳ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ለዓለም አቀፉ የሰላም የኖቢል ሽልማት መታጨታቸው ይግባል ሲሉ ቅናዊ፣ ሙሁራዊ፣ ታሪካዊ፣ ቃላቸውን ሰጡ። „በቃሌ ወደ እግዚአብሄር ጮኽሁ፣ ቃሌም ወደ እግዚአብሄር ነው፣ እርሱም አዳመጠኝ።“ (መዝሙር ምዕራፍ ፸፮ ቁጥር ፩) ከሥርጉተ ©ሥላሴ 16.07.2018 (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።) · መቅድም። ይህ ነው ዘመን እንዲህ ይከሳል። ዘመን ይናገራል፤ ዘመን ያምሳጥራል፤ ዘመን ይደመማል። ዘመን ተነባቢም አናባቢም። ዘመን እንዲህ ታሪክ ይሠራል። ዘመን ዕውነትን እንዲህ እያነጠረ ይሄዳል። ዘመን እንዲህ በነጠረው ዕውነት ላይ ቅኖችን እያበራከተ፤ በጎ አሳቦችን እያለመለመ ለህሊና ምቹነትን ሁኔታዎችን በራሱ ጊዜ ያማቻችል። ጊዜ ታሪክ ይሠራል!ዘመን ትውልድን በፍቅር እንዲህ ያለመልማል! ተመስገን! · መነሻ ምርኩዝ። https://www.youtube.com/watch?v=U-IOcXdppos awaze news · ታላቅሰው! ልዑል ዶር አስፋው-ወስን አስራተ ካሳን እኔ አጋጣሚ ሰጥቶኝ እኒህን የአገር እና የወገን፤ የታሪክ እና የትውፊት፤ የዕሴትና የትሩፋት ታላቅ ኢትዮጵያዊ የታሪክ ሳይንቲስት በአካልም አውቃቸዋለሁኝ። የተማሩ ብቻም ሳይሆን ጀርመንኛን ቋንቋን አወቁት ከምል በቁበት ብል የሚሻል ይሆናል። ባላፈው ሰሞናት የጠ / ሚር አብይ አህመድን የትግረኛ ቃና ሳነሳም አንስቻቸ...