መባቻው አባተ ለመሰንበቻው … ተመስገን አሜኑ!

ዕይታ።
„ይሁዲም ሦስት ወይንም አራት ዓምድ 
ያህል ባነበበ ቁጥር ንጉሡ በካራ ቀደደው፤
ክርታሱም በምድጃ ውስጥ ለላው እሳት 
ፈጽሞ እስኪቃጠል ድረስ በምድጃው
 ውስጥ ወደ አለው እሳት ጣለው።“

(ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ 36 ቁጥር 23)
ከሥርጉተ© ሥላሴ
16.07.2018
(ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።)

  • ·       በር።

በትናንቱ የሚሊዬነም አዳራሽ ዝግጅት ላይ ጠቢቡ ቴወድሮስ ተገኝቶ ነበር። ከዛ በመገኘቱ እና ባቀረባቸው ዝግጅቶች ላይ አንዳንድ አስተያዬቶች ይሰጣሉ። ያ መብት ነው። ሁሉም የተሰማውን መግለጽ። ስለዚህም እኔም የተሰማኝን መግለጽ እሻለሁኝ። በዚህ ቀንበጥ ባለቅኔ ላይ ብዙ መከራዎች አልፈዋል። መከራዎቹ ኢትዮጵያ ተሸክማ ከኖረችው መከራ እንደ አገር ባይሆንም እንደ ግለሰብ ግን የማያንስ መከራ ሲፈራረቅበት የኖረ የጥበብ ሰው ነው። እንደ ሌሎች ተሰዶ አይደለም መከራውን ያስተናገደው „አልሄድ አለኝ እግሬ“ በማለት እዛው ሆኖ መከራዋን ተመግቦ ነው የኖረው። በፈታናውም ሰለጠነበት።

ሌሎች የጥበብ ሰዎች እንደ እሱ የጠና ነገር ገጥሟቸው አያውቅም። ሊኖር ቢችል የሚታገዙበት የመንፈስ ሃብት አጥተው አያውቁም፤ ብረት መዝጊያ የሚሆን ሰው እንደ ማለት። ይህ የጥበብ ሰው ግን ከፍ ባለው ፈጣሪ ዝቅ ሲል የትዳር አጋሩ እና ቤተሰቦቹ በስፋት አድናቂዎቹ ካልሆኑ በስተቀር ሁነኛ የእኔ የሚለው የሚመካበት ባለሥልጣን የለውም። እንዲህ ዓይነት ቀንጣ ሰዎች በዚህ መሰል የጥበብ መድረክ ሲመጡ ከጎናቸው ሰው ከሌለ ፈተናው እጅግ ግዙፍ ነው።

አንድ ሰው ሌላ ደጋፊ ትክሻ የሆነ ሰው ከሌለው የማናቸውም ጥቃት ሰለባ መሆኑ የታወቀ ነው። ይህን በእኔ ህይወት ያዬሁት ነው። ወደ ትግል ዓለም ስገባ በድንገት ነበር። ነገር ግን ንቃቴ እና ጉዳዮችን በፍጥነት ለመያዝ፤ ለመለማመድ አደረገው የነበረው ቅልጥፍና እና ጥረት፤ በምላክባቸው ቦታዎች የሚሰጡኝ ምስክርነቶች ወጥነት አቅም ካላቸው የፖለቲካ ሊሂቃን ዓይን እንደገባ አደረገኝ እና እድገቴ እጅግ ፈጣን ሆነ። 

ግን ብረት መዝጊያ የሆነ የሥጋ ዘመድ አልነበረኝም። እርግጥ ነው አባቴ አበይ የህሊና ጥሞናዊ ብልህለነት ስለነበረው ምክሩ ዘሊቅ ነበር። ነገር ግን ከፖለቲካ ሊሂቃን ወገን ሰው አልነበረኝም። ብቻ አለቆቼ የብረት መዝጊያ ሆኑሉኝ። ስለዚህ በእኔ ቅልጥፍናዊ ዕድገት እና ብቃት የተሳሉ ማጭዶች ሁሉ ማርተው እንዲቀሩ ሆነዋል። እርግጥ ነው እኔን ማጥቃት ያልቻሉ በአባቴ ላይ በተለመደው የፖለቲካ ሴራ ፈጽመው የአባቴ ነፍስ በነፍስ ገዳዮች እጅ ወድቆ እሱም እንደወጣ ቀርቶ ድል አግኝተዋል። ነገር ግን ሥርዓቱም ብዙም ሳይቆይ ፈረሰ፤ እነሱም ፈረሱ ሁላችንም አብረን ፈረስን።  

የሆነ ሆኖ በዛን ዘመን ለነበረኝ ትጋት፣ ጠባቂ፣ ተንከባካቢ የፖለቲካ ሊሂቃን ስለነበሩ በእኔ ላይ የነበሩ ዘመቻዎች ሁሉ ከሽፈዋል። እንዲያውም ሁሉም ነገር ከፈራረሰ በ ኋዋላ ቢሮችን ሲቃጠል ሰው እሳት ውስጥ እዬገባ ፎቶየን አውጥቶ ለቤተሰቦቼ ሰጥቷቸዋል። የስም ዝረዝርም እንደ ወንጀለኛ በዬህዝብ አደባባይ ሲለጠፍ ሥሜን ሰው እራሱ እዬሄደ በምላጭ ቀዶ ያወጣው ነበር። ድሮም እኔ ይሄው ነው አቋሜ። ዕውነት ነው ብዬ በማምንበት ጉዳይ መትጋት። በቃ። 

ያን የሚያውቅ የጎንደር ህዝብ ከተገባው በላይ ለመንፈሴ እንክብካቤ አድርጎልኝል። ጫካ ስገባም፤ በምህረት ገብቼ በድጋሚ ስታሰርም፤ በቁም እስር ስፈታም። ለዚህም ነው ደግሜ ህዝቤን ላለማሰቃዬት አንድም የፖለቲካ ድርጅት አባል ለመሆን ሳልፈቅድ የኖርኩት።

አሁን ደግሞ ከተሰደድኩኝ ብዙ ነገር ነው የምጥረው ግን ሁነኛ ሰው የለኝም ብረት መዝጊያ የሚሆን ወንድም የለኝም፤ እኔ በተገኘሁባቸው ዓውዶች ሁሉ ያሉ መረጃዎችን ሲያስጠፋ፤ ያገኘ ሲረግጠኝ፤ ያገኝ ብሎክድ ሲያስደረግኝ፤ ያገኘ ሲያስወግዘኝ፤ ያገኘ ሥሜን ሲያስጠፋ፤ ያገኘ ፈጣሪ በሰጠኝ መክሊት ላይ ማዕቀብ አስጥሎ በግዞት አንድኖር አስፈርዶብኝ በዚህ መልክ ሁሉም አቅሜ ተቀብሮ አፍ ባለው መቃብር ይኖራል። በከንቱ ፈሶ ... 

የጠቢቡ ቴወድሮስ የሚለዬው ጸሐፊ ብቻ ሳይሆን ዜመኛም በመሆኑ ለህዝቡ አደባባይ የሚወጣበት መንገዱ ከእኔ የቀለለ ስለሆነ ህዝብ ገብ፤ ዓይነ ገብ የሆነ የህዝብ ፍቅር አቅሙን የፈለገ ቢቀናቀኑት፤ በመነግሥት ደረጃ ቢያዋክቡት፤ ሌሎችም እንደ እሱ ሥማቸው ገኖ የወጡት በስልት ቢፈታተኑትም በፈረቃ ሊያሸንፉት አልቻሉም።
  • ·       መከራ የማያጣው መከረኛ። 


በዬተገኘበት ቦታ ሁሉ ስንክስር እዬተነቀሰ የማይባለው የለም። ለምሳሌ የባህርዳሩ ኮንሰርት ላይ እጅግ በጣም የሚገርሙ ጉዳዮች ተነስተው ነበር „ትዕቢተኛ፤ ሰዓት የማያከብር፤ ይቅርታ ያልጠዬቀ“ ወዘተ የሚል። ትዕቢተኛ ለሚለው ሰብዕናው አፈጣጠሩ ስክነት እና ንጉሣዊ ሥነ - ምግባርን የተከተለ ስለሆነ ከዛ ውጪ ልሁን ቢል አያምርበትም። በፍጹም። ቅሌትም መክለፍለፍም፤ መንቦጫረቀም ሊያመርበት ከቶውንም አይችልም። የተፈጠረው ለታቦትነት ነውና!

በሌላ በኩል ርቱ አንደበት ከማስተዋል ጋር ስላላውም ስክነቱ ሰብዕናው አጉልቶ ስለሚያወጣው ከብስጭት፤ ከንዴት፤ ከቁጣ ሁሉ በፍጹም የራቀ አንድ ሙሉ የአገር መሪ ሊኖረው የሚገባ ስብዕና ስላለው ይሄ እንደ ትዕቢት ይታይበታል። ግን በሰብዕና አፈጣጠር ላይ ጠላቅ ያሉ ግንዛቤዎችን ለመመርምር የአስተሳሰብ ድህንት የፈጠሩት ችግር ይመስለኛል እሱን እንደ ትእቢተኛ እንዲታይ የሚያደርጉት። እሱ ግን እንደ እነሱ ስሜታዊ አይደለም። ብዙውን ነገር አይቶ ነው እንዳለዬ የማያልፈው። በትናንት ዝግጅት ላይ ስለ ዜግነት አመሳጥሮታል። በአጽህኖት ተናግሯል።

ሰዓት ማክበርን በሚመለከት እኔም እምጋራው ነው፤ እኔ በህይወቴ ሙሉ አንዲት ደቂቃ ሰዓት አሳልፌ አላውቅም። ስለምን? በሰዓት ውስጥ ለመኖር የፈቀዱ ሰብዕናዎች መብት የመጣስ ያህል ስለሚሰማኝ። እንዲያውም እኔ ቀድሜ ነው የምገኘው። አንዳንድ ጊዜ አዘጋጆች ሳይሰናዱ ሁሉ እደርሳለሁኝ። ስለዚህ ይህን ማስተካከል ቢኖርበት መልካም ነው። ሁለት ጊዜ ስለሰማሁኝ። አንድ ጊዜ በባህርዳሩ ኮንሰርት ሌላ ጊዜ በአሜሪካኑ የሽልማት ዝግጅት። 

በተረፈ የትናንትናው ግን በሮቹ መዘጋታቸው የደህንነት ጉዳይ ነው። መሆንም ነበረበት። ከእንግዲህ ብርቱ ጥንቃቄ ያስፈለጋል። በአቋራጭ በር መግባት ባለመቻሉ ረጅም ጉዞ መጓዙን ተናግሯል። ይህ አጋጣሚዎች የፈጠሩት እንጂ የባላቅኔው ችግር አይደለም። ስለሆነም ይቅርታ የሚያስጠይቀው አይኖርም።

ወደ አዳራሹ በመግባት በሕዝብ መሃል አቋርጬ ለመሄድ ረዘም ያለ ጊዜወስዶብኛል”- ቴዎድሮ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) 
ሌላው መድረክ ላይ ዝግጅትን ለማቅረብ መሰናዶ ያስፈልጋል፤ ሲናርዮ ቀድሞ ሊደረግበት ይገባል። በንግግር ጥበብ ውስጥ መሰናዶ የመጀመሪያው የመርህ ጉዳይ ነው። ሙዚቃም ዜማዊ ንግግር ነውና።

ባልተዘጋጀበት፤ ባልተሰናዳበት፤ ባልተጋበዘበት መድረክ ምን እና ምኑ ተወቃሽ እንደሚያደርገው ግራ ይገባል። ራሱ ድምጽ ማጉያው ሰፊ የሆነ የሳቦታጅ ሴራ የተስተዋለበት ነው። በትክክል አይሰማም ነበር። ጠቅላላ ዝግጅቱ ሁሉም ከአዳራሽ ውጪ እንጂ ውስጥ አይመስልም ነበር። 

የድምጽ ጥራት በከፍተኛ ደረጃ ነበረው። መብራት አለመጥፋቱ እኔ እራሱ ገርሞኛል፤ ምክንያቱም ሴራ ከትሞ በኖረበት አገር የሚጠበቁ እንደዚህ ዓይነት ጉዳዮች ስለሚኖሩ ለወደፊቱ እንዲያውም ተጠባባቂ ጄኔሬተር ማዘጋጀት ያስፈልጋል። መበራት ቢጣፋ ኖሮስ ምን ሊኮን ነበርና … 

ሌላው ኢትዮጵያዊነትን በሚመለከት ፊደል መቁጠር ያልጀመረው ፊደል ቢቆጥር እንጂ እሱ ለኢትዮጵያዊነት እጬጌ ነው፤ በዛ ላይ ፓን አፊረካንሲትም ነው። በዛ ላይ ፈርሃ እግዚአብሄር ያለው በማንኛውም ዓይነት ፖለቲካ ድርጅት ልብ እንዲገጠምለት የማይፈቀድ ጠፈፍ ያለ፤ ክውን ያለ፤ የፈጣሪ ስጦታ ነው ለእኛም ለአፍሪካም።

በመንፈሱ ውስጥ ያለው ፍቅር ከነተፈጥሮው ነው፤ እንዲያውም ለእኔ ኢትዮጵያዊ ጥበበኛ ቴወድሮስ ካሳሁን የፍቅር ተፈጥሯዊ መርህ እክተቢስት ነው ባይ ነኝ። እንግዲህ አደባባይ ከወጡት ማለቴ ነው። አንዳንዶቹ እሱን የቀደሙ ሊኖሩ ይችላሉ ግን መድረኩን ካለገኙ ልናውቃቸው አንችልም። ለምሳሌ ዶር አብይ አህመድ የፍቅር ተፈጥሯዊ አቅም እንዳላቸው ወደ መድረክ በይፋ ከመጡ በ ኋዋላ ነው ብዙ ሰው የተረዳው፤ ነገር ግን በተደጋጋሚ እንደወሳሁት ለእኔ የፍቅር አነስተኛ ፕሮጀክት ኢትዮጵያ ላይ በዚህ ሙያ እዬሠሩ ያሉ ስለመሆናቸው እሳቸውንም ዶር ምህረት ደበበንም ቀደም ብዬ ነበር ያገኘሁት መረጃውን። የጽናቴም የሙገቴም መሰረቱ ይሄው ነው። እጅግ የበራ ተስፋ እና ብሩህ ዘመን ነው እኔ የምጠብቀው።
  • ·       የተመለደ የሳንክ ጥንስስ ዋና።

ዛሬ የጋዜጠኛ አቶ መሳይ መኮነን አንድ ጹሑፉን ዘሃበሻ ላይ አግኝቼ አንብቤዋለሁኝ። እምጋራቸው ቢኖሩኝም እማልጋራቸውም አሉ። በጠ/ ሚር አብይ አህመድ ጉዞ ከወስጡ አልተቀበለም ይህ ዋነኛው ችግሩ ነው። ስለዚህ አጋጣሚዎችን ፈልጎ ብዙ ደክሟል፤ ጉዞውን ለማክሰል። ምክንያቱም የእሱ የህሊና እጮኛ ስለነበረው። እኛ ደግሞ የህሊና እጮኛዎችን የሚበልጥ ከመጣ ነገም ቢሆን ለተሻለው መመስከራችን ግድ ይላል። ሰው ድርጊቱ እንጂ ወንበሩ አይደለም እና የሚከበረው። ከዚህ ሌላ የሥልጣን የ ዕወቅና ቅርጥምጣሚ መቃረምም ስላልተፈጠርነበት። በራሳችን ተደሞ ውስጥ ነው የበቀለነው፤ የጸደቀነውም። ቅልውጥ የሚያስኬድ ምንም ነገር የለም። ዕውነት ያለው ሲመጣም ልባችን ከፍተን እንኳን ደህና መጣህ ለማለት የማሃያ ዳረንጎት አያግደነም ... 

ለምሳሌ እሱ እና ሌሎችን በግል የሚታተሩትን እኩል አላያቸውም። ስለምን? አሱም እንደሌሎቹ ጋዜጠኛ ነው። ግን ግንቦት 7 አሸናፊ ሆኖ እንዲወጣ ሲያልም የኖረ፤ ግን ለዛውም የነፃነት ጋዜጠኛ። ስለዚህ የየእሱ ፕሮ ፋይል የአንድ ፓርቲ ሊቀመንበር ፎቶ ነው። ለእሱ ከአንድ የፖለቲካ ድርጅት ሊቀመንበር ይልቅ ኢትዮጵያ ትበልጣለች። የልጁን፤ የባለቤቱን፤ የራሱን ቢያደርግ ጉዳዬ አይደለም፤ የመሪ ፎቶ ግን ለአንድ የነፃነት ጋዜጠኛ አይመቸኝም። ሌሎች ደግሞ ከዚህ ውጪ የሆነ ምልከታ ነው ያላቸው። በሁለቱ መካካል ልዩነት አለው። ለጋዜጠኛ አቶ መሳይ መኮነን ኢትዮጵያ ማለት ግንቦት 7 ብቻ ነው። 

መሪ ማለትም የግንቦት 7 ሊቀመንበር ማለት ነው። ከዚህ ውጪ ከመጣ መንፈሱ ሊያስተናገደው አይፍቅድም። ይሄ ትልቁ ችግር ስለሆነ ነው ሲያምሰን የከረመው። አድናቂዎቹ፤ ደጋፊዎቹ ሁሉ ሲታወኩ የባጁት በዚህ መስክ ነው። ፍቅር ተጠቅልሎ ወደ አንድ አቅጣጫ ሲሄድ አሰጋውና ባለ በሌለ ሃይሉ ታገለው፤ ሞገተው ግን አልተቻለውም፤ ንጹሃን ህይወታቸውን ገበሩለት፤ ዓለምም ተደመመበት።

ዛሬ ከጠቢቡ ቴወድሮስ ጋር ያነሳቸው ነጥቦች ሚዛናዊነት ለማምጣት ሳይሆን በውስጡ ያመቀውን ነገር ለማሳዬት ነው። ያ ሁሉ የህዝብ ፍሰሃ አናውቶታል። ስለዚህ የታመቀውን ጉዳይ ማስተንፈሻ አስፈለገው እና እንደ ማካሄጃ እንደ ተለመደው አንዲት ሰበዝ መዘዘ ...

ቴዲ የማኒፌስቶ አንበል አይደለም። የቴዲ አንበልነት ኢትዮጵያዊነት ባለፈም አፍሪካዊነት ነው። የአብዩ መንፈስም ይኸው ነው። ከጋዜጠኛ አቶ መሳይ መኮነን ጋር እምስማማው በትናንቱ ዝግጅት ጠቢቡ ቴወድሮስ ካሳሁን ሊወቀስ አይገባም የሚለውን ነው። ታዳሚው ያልገባው የእድምታ ሚስጢር ያስተለላፈው መልክት እጅግ ከባድ ነበር  "የኢትዮጵያ ህዝብ“ ነው ያለው። 

ይህ በራሱ ትልቅ የፖለቲካ ግንብን የናደ ነው። „ህዝቦች“ „ዘጠኝ አገሮች“ የሚለውን የጣሊያን ቅኝት ከመሰረቱ ንዶታል። ሌሎችም ያነሳቸው ጉዳዮች የውስጡን ቁስለት እና ዜጋው በዜግነት በለመኖር ውስጥ የኖረበትን የጨለማ ዘመን በአጭር በግልጽ ግን በቅኔ የገለጸበት ሁኔታ ነው። 

ለነገሩ ይህ ጥበበኛ ተንባይም ነብይም ነው። ዓይነት የወጣላት ተናጋሪም ነው።  የትናንቱ ለዛሬ እርሾ አድርሶናል የዛሬው ደግሞ ለነገ እርሾ ያደርሰናል ይህን በመርህ ደረጃ ብንስማማበት የተገባ ነው። ዕድሉን ማግኘቱ ግን እጅግ አስደሳች እና ለእኔ መንፈስ ቅርብ የነበረ ጥሩ አጋጣሚ ነው።

ኮንሰርቱንማ ባህርዳር ላይ እኮ አይተናዋል። ከሙዚቃው ይልቅ በታገደበት መድረክ የሁለት ደቂቃ ዕድል ማግኘቱ ነው ብልሁ ጉዳይ። እኛ ከዚህ ማን ያደርሰናል፤ ትኬት ገዝተን ለገባንበት የቴያትር ዝጅግት በእስር ነው ትውናውን የተመለከትነው፤ ስብሰባዎችን ስንታደም እማ ያው የእንጦረጦስ ያህል ነው። ተሜ እራበኝ የሚለው ይሄንኑ ነው።  

በፕላስተር አፋችን አሸገን ሄደን እንዲያም ሲል ተገላምጠን፤ በክፉ ዓይን ተገርፈን፤ እንዲያም ሲል በአሽሙር መድረክ ላይ ተደብድበን እያነባን ነው ቤታችን የምንገባው እዚህ በስደት አገር … ያው እነ አቶ ወንድም ጋዜጠኛ አቶ መሳይ መኮነን በሚመሩት በኢሳት ፈንድራይዘንግ ዝግጅት … መናገር? አይታሰብም! እንደ ቦንዳ ተጠቅልሎ ሄዶ ተጠቀልሎ መመለስ። ጥቁር ግዞት!

  • ·       ያቺ ደቂቃ የነፃነት ዋዜማ ናት።   

ዋዜማ! ጠቢቡ ቴወድሮስ ካሳሁን የተፈጠረበትን መልዕክት አስተላልፏል። ስለ ኤርትራም እሱ የቀደመ ነው። የሁለቱ የብሥራት ዕለት መገኘቱ በራሱ ከበቂ በላይ ነው። እሄዳለሁ ሁሉ ብሎ ነበር። ለዛውም በዛን ጊዜ፤ ሊደፈር በማይችለው መንፈስ ውስጥ። ባልተሰናዳ መንፈስ ቢሄድ ሊያገጥም የሚችለው አደጋ ከባድ ነበር። በቁርሾ፤ በጠብ፤ በቂም፤ በበቀል፤ በጦርነት ውደመት ውስጥ አብሬ እጋያለሁ ብሎ ነበር ያሰበው።

ያ ጊዜውም ወቅቱም አልነበረም። ምክንያቱም የመጀመሪያው ገፈት ቀማሽ መሆን የሚገባቸው የሁለቱ መንግሥታት መሪዎች ስለነበሩ። ከእንግዲህ ግን እንዳሻው ቢሄድ ቴዲ ትናንትም ዛሬም ወደፊትም የኢትዮ ኤርትራ ነው። ለዛ ለጣረለት ዕለት መገኘቱ በራሱ የድል ዙፋን ነው ጠቢቡ ቴወድሮስ በዬሰልፉ ፎቶዬን ለጥፉልኝ ብሎ ለማንም ምንም አያመለክትም፤ ጉርሻም ድርጎም አይቆርጥም። የኮራ የተደላደለ የራሱ ንጉሥ ነው። የመንፈስም ሃብታችን ነው! ያኮራል! ወንዳታ!
  • ·       ውድድር።

ሌላው ጋዜጠኛ መሳይ መኮነን አርቲስት አቶ ታማኝ በዬነን አንስቷል። አርቲስት ታማኝ በዬነ በደርግ ጊዜም አገልጋይ ነበር፤ በዘመነ ግንቦት 7 ዘመንም ንቁ መሪና አገልጋይ ነው፤ በዘመነ አብይ ደግሞ ዕንባውን ገባሪ ነው፤ ነገ ደግሞ ማይክ እና እሱ ምን እና ምን እንደሚሆኑ እንጠብቃለን። ኤርትራን በሚመለከት መገንጠሏም ተቃውሟል፤ ሆነም ግን እንደገና „የነፃነት ሃይሎችን“ ማስጠገቷን ደግፎ ተነስቷል። ይሄን ሁላችንም ያደረግነው ነው።

አሁን ደግሞ ወደ ሰላም ሲመጡ በእሱ በተቀነቀነለት ድርጅት በግንቦት 7 አቅም እና ክህሎት ባለመሆኑ የሚሰማውን ስሜት ባላውቅም የሚከፋ ይሆናል ብዬ ግን አላስብም። አዳምጬው አለውቅም ከ2015 ጀምሮ። ወደፊትም አቅም የለኝም እሱን ለማድመጥ። እኔ እኔ እንጂ ሌላ አይደለም። ሥርጉተም የራሷ መንገድ አላት። የራሷም ጌታ ናት። አንድም ቀን ከዚህ ሲመጣ አረግርጌለት አላውቅም። ተግባሩን ግን ቀድሼለታለሁኝ፤ የምሄድው እሱ ናፍቆኝ ሳይሆን ነፃነት የራባቸው ስደተኛ ወገኖቼ ካንፕ ተቀምጠው ቅኖች የሚያደርጉትን ተሳትፎ ለታሪክ ለማቆዬት ብቻ ነው። በራሴ ወጪ ... በራሴ ጊዜ ... 
  • ·       ኢትዮጵያዊነት እና ታማኝነት።

ኢትዮጵያዊነት ላይ አርቲስት ታማኝ በዬነ አይታማም። በዚህም አንድ ጹሁፍ ጽፌ ነበር። ቢበዛ እንጂ የሚያንስ ጉዳይ የለበትም። ደክሟልም። ግን በማህል የሚመዘንበት ብዙ ጉዳዮች አሉበት። 

ኢትዮጵያዊነትን ለግንቦት 7 ብቻ ድል የማድረጉ ምልከታው ግን የጥበብ ቤተኝነቱን ዓውደ ክብር ይፈታተነዋል። እዮራዊ መክሊቱንም። ዛሬ አገር ቤት ፈተናው ይሄው ነው። ጠፈፍ ብለው የቆዩት እና ሌሎችን ቅይጦችን በመንፈስ እኩል እንዳልተሰተናገዱም። ትናንት አይተናል። እነኛ ድምጽ ማውጣት እንኳን አልተቻላቸውም፤ ደፍረው ከህዝብ ፊት ለመቆም አልተቻላቸውም። ህዝብ ማንዘርዘሪያ ወንፊት አለውና።

አማራም ሰው ነው። ተጋድሎውም የሰውነት ተጋድሎ ነው። ትግሉም  የኢትዮጵያዊነት ተጋድሎ ነው። ኢትዮጵያዊነት ውስጥ የአማራ ተጋድሎ አለበት። ጠቢቡ ቴወድሮስ „ጎንደር ጎንደር፤ ጧፍ አስከ ማርን“ ያመጠባት ጥልቅ ጥበባዊ የታገድሎ ውሎ እዮራዊ ነበር። ታጋድሎውን በበለጸገ ክህሎቱ እና መክሊቱ መንበር ላይ አውሎታል። ለዛውም እስከ አሁን ባሊህ ባይ ለሌለው ተከድኖ ለተቀመጠ ለድል ላበቃ ገናና መንፈስ። 

አርቲስት ቀቶ ታማኝ በዬነ ደግሞ „በነፃነት ሃይሉ እና በጎንደር ማህበር“ ነበር ሲባክን የነበረው። ስለዚህ ኢትዮጵያዊነትን በመቀበል እና በመቀጠል እረገድ፤ ኢትዮጵያዊነት በማያያዝ እረገድ ክፈተት አለበት። እንግዲህ ከዚህ ሲዊዝ ሲመጣ ወደ ሦስት ጊዜ ተገኘቼ አይቸዋለሁኝ። ከዚህ የመጣው ወደ አምስት ጊዜ ነበር። እኔ የተገኘሁት ወደ ሦስት ጊዜ ነበር።  

ብዙ ነገሮች በውስጡ አሉበት። ኢትዮጵያን መውደድ ማለት አንተ ወደ ኢትዮጵያውያን መሄድ እንጂ አንተ ተኮፍሰህ እነሱ ወደ አንተ እንዲመጡ ማሰብ ማለት አይደለም። ይህም ብቻ ሳይሆን በአቀራረብ፤ በአነጋገር ያገኘውን ሽርክት መረጃ እንዳለ መድረክ ላይ በማቅረብ ሳያሹ፤ ሳያጣጥሙ፤ ሳያምዛዝኑ ተጨማሪ ስደትን በተጨማሪ ለተከፉ፤ ለታመሙ፤ ለብቸኞች መጋበዝ እጅግ የሚዘገንን ገጠመኝ ነው። ለሴት እህት ሲሆን ደግሞ ይጎመዝዛል ... መራራ ነው ... 

መከፋትን፤ ተጨማሪ ጥቁር ልብስ ገዝቶልን እንዲሄድ አይደለም ገንዘባችን ሆጭ አድርገን የምንሄደው። የሚያደምጠው ክፉ ነገር ሲኖር በግልጥ መጠዬቅ እና ማረጋገጥ ይገባል። እኔ ስለምጸፈው የእሱን ፈቀድ ልጠይቅ አልችልም። እሱም አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ እኔም አንዲት ኢትዮጵያዊት ዜጋ። እሱ ፈቃድ ይጠይቅ መሃያ ስላለው እኔ ሥርጉተ ሥላሴ ግን ነፃነቴን የማላስደፈር የራሴ ጌታ ነኝ። ከተፈጥርኩ ጀምሮ ለማንም እና ለምንም አጎብድጄ የማላውቅ፤ ለማንም እና ለምንም የምልነጠፍ፤ ለዬትኛውም አካል ከፍ እና ዝቅ ልል አልተፈጠርኩኝም።

እሱ በሥልጣኑ ማድረግ የሚችለውን ሊያደርግ ቢችልም እኔን ዘግቶ ማስቀመጥ የማይቻል ስለመሆኑ ግን አልተዋወቅነም ነበር … እኔም አንዲት ሴት እህቱ ነኝ ሌላው ቢቀር … ብቻ ኢትዮጵያዊነት መመዘኛው መስፈርቱ ባላቸው እና በደመቀላቸው ሳይሆን በሌላቸው እና ጊዜ ፊቱን ባዞረባቸውም ጭምር ነው … ከቴዲ ጋር የነበረውንም ሁኔታ ዓለም ያውቀዋል … ምን እሰጣ እገባ ውስጥ እንደነበረ …

ኢትዮጵያዊነት እትዮጵያዊ ወገንህ ብስል ከቀሊል፤ የፓርቲ አባል እና አባል ያልሆነው፤ የኢሳት አባል የሆነውን እና ያልሆነውን ሁሉንም በፍቅር ማስተናገድ ማለት ነው። በደንበር እና በክልል፤ በወሰን ሰርተህ ኢትዮጵያዊነት አልቃለሁ ብትል የፖለቲካ ድርጅቶች የወደቁመበት መሠረታዊ ምክንያት ይሄ ነው። አንተም አብረህ ነው የምተወድቀው። ግን አክሮባቲስቲነቱ እጅ ያወጣል።

በሌላ በኩል አንድ የጥበብ ሰው የትኛውንም የፖለቲካ ድርጅት መጠለያ ሊያደርገው አይገባም። የፖለቲካ ድርጅቶች ሊጠለሉ ይችላሉ በታዋቂ ሰዎች ዘንድ። ለምሳሌ የሰብዕዊ መብት ተሟጋቹ አትሌት ሊለሳ ፈይሳን ማዬት ነው። ለተጋበዘበት ቦታ በክብር ተገኘ ከዛ ቅንጣቢ መንፈሱን አልሸለመም።

አርቲስት አቶ ታማኝ በዬነ ግን ያን ጥሶ የሁሉም ነኝ ብሎ መውጣት ይገባዋል። አልተቻለውም። አርቲስት አቶ ታማኝ በዬን የግንቦት 7 ወይንም የኢሳት ብቻ ሳይሆን፤ የህብርም፤ የጸጋዬ ራዲዮም፤ የአዋዜ ራዲዮም፤ የቢቢ ኤንም የመ ኢሶንም፤ የሸንጎም፤ የመአህድም የሌሎችም መሆን ይኖርበታል እንጂ አንድን ብቻ የትንሳዔ አድማስ አደርጎ ማዬት አይገባውም ነበር።

ለሁሉም ማዕከላዊ የሆነ የተሰጠውን መክሊት እኩል ለማገልገል መጠቀም ነበረበት። አርቲስት ታማኝ በዬን ይህን አሸነፎ መውጣት አልተቻለውም። እኔ ከጋዜጠኛ መሳይ መኮነን ለይቼ እሱን የማይበት ሚዛን የለኝም። ካድሬው ምን ይሥራ የጥበብ ሰው የካድሬን ሥራ ተክቶ ከሰራ? ከዚህ የተለዬ ሰብዕና በአርቲስት ታማኝ በዬነ አላዬሁም። ስለዚህ ከቴዲ አፍሮ ጋር ማተካከል አልችልም። ቴዲ ለሁሉም እኩል ነው። ለሚወዱትም ለሚጠሉትም። „ፍቅር ያሸንፋል“ ነው የሚለው። „መደመር“ ሲልም ከልቡ ከእውነቱ እንጂ ለግል ዝና እና ለቀጣይ የክብር ቁርጥራጭ መላሾነት አይደለም። ሰብዕናቸው የተለያዬ ነው። 
  • ·       ሰውን ማዕከል የማድረግ።

ጠቢቡ ቴወድሮስ የፍቅር ነው ንጉሡ ስለዚህ ሰውን እና ተፈጥሮን ማዕከል ያደረገ ነው። ስለዚህ በኢትዮጵያዊነት አንባሳደርነት የጠቢቡ ቴወድሮስ ማዕረግ ከማንም ከምንም በላይ ነው። ኢትዮጵያዊነትን በፖለቲካ ድርጅት ማንፌሰቶ ካሊም ተጀቡኖ ማዬት ከሥልጣን ጋር የተቆራኘ ፍቅር እንጂ የሰው የጥበብ ፍቅር አድርጌ አልወስደውም። በሌላ በኩል በመሪ ደረጃ ኢትዮጵያዊነትን ከፍ ወደ አለ ደረጃ አሸጋግሮታል የምለው „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ ይህ ሞገዳዊ ዕሳቤ ዛሬ ያለውን መንፈስ አዋልዶታል።

አብይ ማለት „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ ማለት ነው። ያሸነፈውም፤ ድል ያደረገውም፤ ፍቅር በገፍ የዘነበለትም  „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ ነው። የተወደደውም፤ የተፈቀረውም፤ የተከበረውም "ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው።" ከማንም ቀድሞ ደግሞ ህሊናን በንጹህ መንፈስ ማጸጃ mindset ኢትዮጵያ ላይ የመሰረተ ነው የአብዩ መንፈስ።

ውጪ አገር እንደ ተበት እኮ ነው ያለነው … ጥላችን ኮቴያችን እዬታደነ አስወግዶ አንያቸው እዬተባልን ነው የኖርነው። ይህን ማን እያሰፈጸመው እንዳለ አሳምረን እናውቃለን፤ እና ከጠቢቡ ቴወድሮስ ጋር ለማለካካት እጅግ ብዙ የተከደኑ ነገሮች አሉበት። በዝምታችን ወስጥ ይዘናቸው ብናልፍ መልካም ነው … እንጂ ብዙ ገመናቸዎች ነው ያሉት።

ቀድሞ ነገር ተጨማሪ ጀግና፤ ተጨማሪ ተወዳጅ እንዲፈጠር ይፈለጋልን? ጎንደር ከአርቲስት አቶ ታማኝ በዬነ እና ከሥጋ ወንድሙ ውጪ ሌላ ጀግና ሰው እንዲወጣበት፤ እንዲበቅልባት፤ እንዲታይባት ይፈቀዳልን? ተውን የቻልነው ብዙ ገመና ስላለ …

እግዚአብሄር ይመሰገን የሐምሌ 5/ የ2010 ክብረ በዓል ላይ ጎንደር መሬት ላይ የጀግና - የብቁ - የንጹህ  - የጥንቁቅ - የብልህ የማስተዋል ጌታ የረዳት አውሮፕላን አብራሪ ሃይለመድህን ፎቶ በክብር ነበር። እሱ እንኳን ተዳፍኖ እንዲቀር ስንት ተሰርቶበታል … ይህ ነው ኢትዮጵያዊነት? ይህ ነው ለነፃነት መታገል ማለት? ይህ ነው ኢትዮጵያን መውደድ ነውን? አይደለም!

  • ·       ጊዜ ወንፊቱ ከወፊቱ።

አሁን ደግሞ ዘመን ጥሩ ነው ሁሉን እያዬን ነው፤ ማመን ከዬት እንደሚጣድ። ትናንት የማን? ዛሬ የማን? የሚለውን እናያለን እንሰማለን፤ የእውነት ሰዎች ግን አምልኮታችን ዕውነት ነው። ሰዎች ሊወድቁም ሊነሱም ይችላሉ፤ ሲወድቁም ሲነሱም አብሮ ላለመወደቅ እና ላለመነሳት ከነጠረው ዕውነት ጋር መሰለፍ ብልህነት ብቻ ሳይሆን ሙሉ ህሊናዊነትም። የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች በተለይ አውራ ነን የሚሉት ሲያጠፉ፤ ግድፈት ሲፈጽሙም የጥብብ ሰዎች ሊገሯቸው ይገባል። ሊያስተካክሏቸው ይገባል። ከግለሰቦች ሥም እና ዝና ይልቅ ማንም የማያገኘውን መክሊት የሰጠው የፈጣሪ የጠቢብነት ማዕረግ እና ክብር ለሚዛናዊ አቋም እና ውሳኔ ይበልጣል።

ያ የአማራ ታገድሎ አድማጭ ባያገኝ ገድሉ የሚባል መንፈስ ባይፈጠርለት ኖሮ ዛሬ ተዘርዝሮ የማያልቅ የዚህ ሁሉ ሐሤት ባለቤት መሆን ባልተቻለ ነበር። መሪነት ፉካራ አይደለም። መሪነት ብቃት ነው። መሪነት ጥበብ ነው። መሪነት ቀድሞ መገኝት ነው። መሪነት ሳይሸራርፉ ኢትዮጵያን መውደድ ነውመሪነት ዕውነት ነው። አርቲስትነትም ዕውነተኝነት እንጂ ሰው አምላኪነት አይደለም። አርቲስትነት ፋክት አምላኪነት እንጂ የፖለቲካ ማንፌስቶ ጣዖት አማላኪነት አይደለም!
  • ·       ጋዜጠኛ አቶ መሳይ መኮነን እንዲህ ይለናል … 


„አዲስ ከመጣ ባለውለታ ጋር ጭልጥ ብሎ የመክነፍና ሌላውን የማኮሰስ አባዜ ለሀገር አይበጅም::“

አዲስ የመጡ የኢትዮጵያ ባለውለታ አይደሉም ዶር አብይ አህመድ። ሎቱ ስብሃት! ማህከነ! ተሳህነ! ከዚህ ቀደም ማንም ያልሠራውን ቀውስ የፈቱ እና፤ የአገራቸውን የደህንነት ማዕከል የመሠረቱ የአማራር ጥበብ ጀግና ናቸው። ስለ ኢትዮጵያ ነው ራውናዳ የዘመቱት። ይህ ሊያቅለሸልሽ ቢችልም ግን ግድ ነው … ነገን ያዬ … ትናንትም እዬተዘገበ ነው እስኪበቃ ድረስ 
  • በሌላ በኩል


ጠቢቡ ቴወድሮስ ካሳሁንም ማንኮሰስ እራስን ማዋረድ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያዊነትን መዳፈር ነው። አቅሙ ማን አለውና የእሱ አፍሪካዊነት ከኢትዮጵያዊነት ጋር ያላቸውን መስተጋብራዊ ህይወት ለመዳኘት፤ ቀድሞ ማን ችሎታ አለውና? ይቻላልን? በመሪ ደረጃም ቢሆን ዶር አብይ አህመድ፤ በጥበብ ደረጃም ጠቢቡ ቴወድሮስ ካሳሁን ሁለቱም ባለቅኔ እና ሁለቱም ፓን አፍሪካኒስት ናቸው። የቴዲ አፍሮ ፈንም ናቸው ብዬ አስባለሁኝ ዶር አብይ አህመድ።

„ይሄ በዱላ ቅብብሎሽ“ አዲስ ጨዋታ ከ97 ጀምሮ ተሞከረ እኮ ግን የመሪነት ክህሎቱ፤ አቅሙ፤ ጥበቡ ከሌላ የሰው ሊኳንዳ ቤት ከመክፈት ውጪ የተገኘው ትርፍ የለም። የታዬው በአዲስ ሥም መንቆጥቆጥ፤ ማሸብረቅ እንደ ትናንቱም ዛሬም። 

ሌላው ግን ዶር አብይ አህመድም ቢሆኑ ሳይመቹ ሲቀሩ ደግሞ የሚሳሳላቸው የለም፤ አሁንም ቢሆን ይሄ ትክክል አይደለም ብለን እንሞግታቸዋለን። እሳቸው ከሌሎች መሪዎች የሚለዩት ቆንጥጡኝ የሚሉ በአፍ ወለምታ ለገጠመው ግድፍት ይቅርታ ዝቅ ብለው የሚጠይቁ ቅዱስ ናቸው። እንደ ሌሎቹ እንደ አዬናቸው የማንህሎኝነት በሽተኛ አይደሉም። ሰውን አስወግደው፤ አልዬው የሚሉም አይደሉም፤ ንግሩን፤ ሞግቱን ነው የሚሉት … ፈሪ አይደሉም! ደፋር እና ልበ ሙሉም ናቸው! ተጠያቂነትን የሚሸሹም አይደሉም፤ በፍጹም። ውሃ በቀጠነም በውሸት ጀልባ ቅዘፉ አቅዝፉኝ የሚሉም አይደሉም ... ወደፊትም ... 
  
ሌላ የመሪነት ጥበብ እና ክህሎት ነው እያዬን ያለነው። በዚህ ውስጥ አልኖርንም። እንዴት አንዲት ስንኝ ስለድክመት ከተጻፈ ማን ከቤቱ ያድራል፤ ማን ሰላማዊ ማህበራዊ ኑሮውን ይመራል፤ እዬኖርነበት እኮ ነው፤ አውራ የተባለው ሚዲያ እና ፓርቲ እንዴት እንደሚያሰደደድን … ማን መስካሪ አለና ከእኛ በላይ፤ ይሄ እኔ ብቻ ሳይሆን ማዕከላዊ አቋም ይዞ በፀጥታ የተቀመጠው ሁሉም ሰው የሚጋራው ነው … ስለዚህ መጀመሪያ ቤትን ማጽዳት ነው … እነ አቶ ጋዜጠኛ መሳይ መኮነን
ቢያንስ አሁን … 

ለዚህም እኔ በ2006 ሰፊ የሆኑ ጹሁፎችን ጽፌያለሁ፤ ትእግስት ሲያልቅ ፍቅር እንደሚያልቀ፤ በማድመጥ እና አቅምን በማስቀጥል ደረጃ ሊደርስ የሚችለውን አደጋ በስፋት ከህይወት ተመክሮቼ ሳልሰስት ጽፌያለሁኝ በሳተናው ብራና ላይ። ከእናንተ ውጪ ኢትዮጵያዊ እና ከእናንተ ውጪ ስለ ኢትዮጵያ ተቆርቋሪ ስሌለ ልታደምጡ ፈቃደኞች አልሆነችሁም። የ እናንተ መንገድ ትክክለኛ የትንሳኤ መንገድ ነበር፤ ግን ዕውነት ለማነገር የሞት መንገድ ነበር በብዙ ሁኔታ እዚህ ያለን ስደተኛ የተከፋን የታመመን እያሳደደክ ኢትዮጵያዊነት? ይመራል ... ልብስ አይችለው የለም አሁን በቅርቢ ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር በተመሰጠረ ሁኔታም ከአብን ጋር ይህን ተሸክማችሁ ተጫጎሉ ... 
  • አዲስ አባባ ሆይ!

ይኸው ጸጥ ብሎ የኖረው የሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች መናህሪያ የሆነው አዲስ አበባ ወደ ፈቀደው የፍቅር አውድ እዬተደመረ ነው። ጥሪውን እኮ ተልለፎለት ነበር በተለያዬ ጊዘ ከጆሮው አላንጠለጠለውም ነበር። ከጉዳይ አልጣፈላችሁም።

 … መስዋዕትነቱን የገበረው ለልቡ መንፈስ ብቻ ነው … ይሄ እናንተ እንደምታስቡት የለብ ለብ ጉዞ መስሏችሁዋል፤ እርግጥ ነው ለሃሳብ ተጠማኞቸ፤ ከሞቀው ለሚጣዱት ስጋት ሊሆን ይችላል። የራሱ የጠራ አፍሪካዊ ምናብ ላለው ዕድሜ ልኩንም በሁሉም ዘርፍ ዝግጁ ለሆነ ሰብዕና ግን እንዲያውም አልተጀመረም ገናአይደለም ኢትዮጵያ አፍሪካንም ታያላችሁ ብቻ ዕድሜ ሁላችንም ይስጠን

በክራንቻ የቆመ አቅም አይደለም የአብዩ መንፈስ፤ ራሱን የቻለ በዕውቀት እና በጥበብ፤ በጽናት እና በክህሎት፤ ብብቃት እና በብልህነት ላይ የታነፀ አቅም ነው። ስለዚህ የወረት ግርግር ወይንም ጎርፍ የቆለለው የምሥራች አይደለም። በውስጡ የበቀለ፤ የጸደቀ ሃሳብ ያለው ክስተት ነው። 

ለአፍሪካ ለራሷ ክስተት ነው። ለዓለምም ለራሱ ክስተት ነው። አንድ አፍሪካዊ ኢትዮጵያዊ በአጭር ጊዜ ረጅም ትልሙን እንዲህ በቅደም ተከተል ምልዕትን ሲያስደደምም፤ የሚዲያ አምደኛ ሲሆን ማዬት በራሱ ታላቅ የድል መባቻ ነው። ጥቁርነትን እራሱ እድገና የወለደ አዲስ ዘመን ነው፤

 በዚህ ሂደት የእናንተ የብራና እና የማይክ ህውከት ደግሞ በለመደበት ይቀጥል ግን ወጀቡን አልፎ አብዩ ለድል ኢትዮጵያን አፍሪካን እንደሚያበቃት ልብ ልክ ነው። አንድ ሰው ብቻ ይመስላል መንፈሱ ከሥሩ ያለው የማይነቃነቅ መሠረት አለው።  ለኢትዮጵያ ወርቃማ ጊዜዋ ነው! 

ስለዚህም ንጹሃን፤ ቅኖች በጸሎት ያግዙታል ፍቅር ርቦ እና ሲሶ ስሌለው ሁለመናችን እንሰጠዋለን። ለሌሎችም ቢሆን ባከበርናቸው ልክ ቢገኙ ፕሮፖጋንዲስት አንሻም፤ እኛ … ካድሬዎች ስላልሆን …  ልንስማማ ያልቻልነው አቅም ያለበትን ቦታ ኢትዮጵያዊነትን ሰንቀን ሚዛናዊ ማድረግ ካለመቻል የመጣ ነው። ሌለውማ በዱላ ቅብብል የተገኘውን ሲሳይ አይሆኑ አድርጎ ጭቃው ወስጥ ሲላነቆጥ ራሱንም ሳያወጣ አሞራው በረረ ቅሉም ተሰበረ ...  

  • ·       ክወና እንደ መውጫ በር …

ያው ኢትዮጵያዊነትን በሚመከለት ማንም ሰጪም ማንም ነሺም አይደለም። እያንዳንዱ ዜጋ ብዙ ተዋግቶለታል፤ ብዙዎችም ተሰውተውለታል። ሌሎች ደግሞ በመስፈርት በመሸንሸን ተዋግተውታል። 

የሆነ ሆኖ ስለ ኢትዮጵያዊነተ ተቆርቋሪነት ቢያሰመስግን እንጂ የሚያስወቅስ አይደለም፤ ቢያሰከብር እንጂ የሚያዋርድ አይሆንም ስለዚህ የኢሳቱ ጋዜጠኛ አቶ መሳይ መኮነን ዛሬ ምርር ያለ ጹሑፍ ነው የጻፈው። ለጠ/ ሚር አብይ አህመድ የተሰጠው ፍቅር ስለ ኢትዮጵያዊነት ስለመሆኑ አልተገነዘበውም፤ ሊገነዘበውም አይፈቅደውም። ለግላቸው እንደተሰጠ ችሮታ አድርጎ ነው ያዬው። በሌላ በኩል ምቾትና ድሎት ሳያምራቸው ሙሉ ሳምንቱን ሌትና ቀን ነው የሚባትሉት ... 

ይህን ያህል ካንገበገበው ስለ አርቲስት አቶ ታማኝ በዬነ ካቃጠለው፤ ስለ ጠቢቡ ቴወድሮስ ካሳሁን ትችት ውስጡ እንዲህ እርር ድብን እንዲል ካደረገው ስለምን አውሮፓ ህብረት ላይ በአውራ ፓርቲነት ግንቦት ሰባት ቀን ወሳኝ እና ተሳታፊዎችን አቅራቢ መሆኑን ስለሚያውቅ ለግንቦት 7 የቀረበ ልዩ ምርጥ ጋዜጠኛም ስለሆነ አርቲስት ታማኝ በዬነ እና ጠቢቡ ቴወድሮስ ካሳሁን ኢትዮጵያዊነት ወካይ ናቸው እና ስለምን አልተጋበዙም ብሎ አልሞገተም?

አዲስ ፍቅረኛ ለማግኘት ድርጅቱ ከሚኳትን። ይህ የውስጥ ስቃይ እና ተቆርቋሪነት ከልቡ ከሆነ። … መናጆ ለማድረግ ካልሆነ … የውስጥ ቃጠሎ ከሌለበት …. ይህ በእጁ የነበረ ጉዳይ ነው … ሊያሰወስነው የሚችለው።

የሆነ ሆኖ ከሰሞናቱ የታዬው አይሳካም የተባለው የአልጀርሱ ውሳኔ ተግባራዊ ፈጣን ምላሽ እና ዕድምታው ተቀናቃኙ ከሚችለው በላይ ነው። ያው ሰው አይችለው የለም ሆኖ ነው ተቁሞ የሚኬደው። የፍጥነቱ፤ የህዝቡ ምላሽ፤ ያሰገኘው ፖለቲካዊ ትርፍ እና ተስፋው ግሩም ድንቅ፤ ዕጹብ ድንቅ ነው። መባቻው አባተ ለመሰንበቻው … ተመስገን አሜኑ!ነገ አዲስ ቀን ኢትዮጵያን፤ ኤርትራን፤ አፈሪካ ቀንድን፤ መከካለኛው ምስራቅ አፊካን፤ መላ አፍሪካን ይጠበቃቸዋል። አፍሪካ አንገት የማይደፋበት ባለድርብ ጭንቅላ ሙሴ በበተረ አሮን በትር ክህሎቱ የላቀ ተስጧታል። ግደፈት ግን መላክ ስላልሆነ እንዲኖር እንሻለን። ሰው ነዋ ...   
  • ·       ምርኩዝ።


http://ethioaddis.blogspot.com/2007/07/interview-with-teddy-afro-tedros_02.html
ኢትዮጵያዊነት የማንፌስቶ ተጠማኝ አይደለም!
የኔዎቹ ኑሩልኝ።

መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።