ልዑል አስፋው ወሰን አስራተ ካሳ "ተደመሩ!" ድንቅነት በድንቅነሻዊነት!

ልዑል ዶር አስፋው-ወሰን አስራተ ካሳ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ለዓለም አቀፉ የሰላም የኖቢል ሽልማት መታጨታቸው ይግባል ሲሉ ቅናዊ፣ ሙሁራዊ፣ ታሪካዊ፣ ቃላቸውን ሰጡ።

„በቃሌ ወደ እግዚአብሄር ጮኽሁ፣
ቃሌም ወደ እግዚአብሄር ነው፣
እርሱም አዳመጠኝ።“
(መዝሙር ምዕራፍ ፸፮ ቁጥር ፩)
ከሥርጉተ ©ሥላሴ 16.07.2018
(ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።)



  • ·       መቅድም።

ይህ ነው ዘመን እንዲህ ይከሳል። ዘመን ይናገራል፤ ዘመን ያምሳጥራል፤ ዘመን ይደመማል። ዘመን ተነባቢም አናባቢም። ዘመን እንዲህ ታሪክ ይሠራል። ዘመን ዕውነትን እንዲህ እያነጠረ ይሄዳል። ዘመን እንዲህ በነጠረው ዕውነት ላይ ቅኖችን እያበራከተ፤ በጎ አሳቦችን እያለመለመ ለህሊና ምቹነትን ሁኔታዎችን በራሱ ጊዜ ያማቻችል። ጊዜ ታሪክ ይሠራል!ዘመን ትውልድን በፍቅር እንዲህ ያለመልማል! ተመስገን!
  • ·       መነሻ ምርኩዝ።

https://www.youtube.com/watch?v=U-IOcXdppos
awaze news
  • ·       ታላቅሰው!

ልዑል ዶር አስፋው-ወስን አስራተ ካሳን እኔ አጋጣሚ ሰጥቶኝ እኒህን የአገር እና የወገን፤ የታሪክ እና የትውፊት፤ የዕሴትና የትሩፋት ታላቅ ኢትዮጵያዊ የታሪክ ሳይንቲስት በአካልም አውቃቸዋለሁኝ። የተማሩ ብቻም ሳይሆን ጀርመንኛን ቋንቋን አወቁት ከምል በቁበት ብል የሚሻል ይሆናል። ባላፈው ሰሞናት የጠ/ ሚር አብይ አህመድን የትግረኛ ቃና ሳነሳም አንስቻቸው ነበር፤ በተጨማሪም የኮ/ ጎሹ ወልዴ የሰጡትን ድጋፍ ስጽፍም አንስቼው ነበር ኮ/ ጎሹ ወልዴ የእንግለዚኛ ቋንቋ ለዛዊ የብቃት ደረጃቸውን ስገልጽ።

ጀርመንኛን ቋንቋን ከተፈጠሩት በላይ ነው የምርምር የፍልስፍና አቅሙን አጎልብተው የሚናገሩት። ቃናው፤ ዜማው፤ ምቱ፤ ማራኪነቱ፤ ስበቱ እጅግ ፍጹም ልዩ ነው። ያው ጀርመንኛ የሚደፈር ቋንቋ አይደለም። ተደክሞ ተደክሞ ሲታክት ያው ማቆም ነው። በጅ አይልም። ሞገደኛ ነው። ከባድ ነው። ምን ያህል ብሩህ ጭንቅላት ቢኖራቸው እንደዛ እንደ ተጠበቡት ይደንቃል። መጸሐፍም ጽፈዋል በጀርመንኛ።

ለእኒህ የታሪክ ሳይንቲስት እና ቋንቋውን በማዘመን ታላቅ አስተዋፆ ያበረከቱት ልዑል ዶር አስፋው አስራተ ካሳ ጀርመኖች ሆኑ ሲዊዞች እጅግ የተለዬ አክብሮት አላቸው። በተላያዩ ሁነቶች ተጋባዥም እንግዳ ናቸው። አንድ ጊዜ ዓለም አቀፍ የስዕል፤ የቅርሳ ቅርስ ኤግዚቢሽን ይከፉቱ ነበር። ምሽት ላይ ነበር ዝግጅቱ። እና ከዚያ ላይ የመክፈቻ ንግግር በጀርምንኛ ቋንቋ ያደረጉት፤ በተጨማሪም ያን የሉላዊውን ረቂቅ የጥበብ ኤግዚቢሽን የከፈቱት ክቡርነታቸው ነበሩ።

ትዝ ይለኛል አንድ ጠቢብ ኢትዮጵያዊ በባህላዊ ትልቅ ሙቀጫ ላይ የፊደል ገበታ ሠርቶ ሁሉ አቅርቦ ነበር። በዛ የሥነ ጥብበ ድንቅ ትዕይንት ላይ ኢትጵዮጵያም ታዳሚ ነበረች። እና ሳያቸው ከወገኖቻቸው የጥበብ ተግባር ሲደርሱ ተግ ብለው፤ ጊዜ ሰጥተው በጥሞናና እና በእኔያዊነት  ውስጥነት በማስተዋል ሲቃኙት አስተውያለሁኝ። ኢትዮጵያ ህሊናቸው እና ውስጣቸው ናት። ብዙዎች የጥበቡ ባለቤቶች ሳይገኙ ሥራቸውን ብቻ ነበር የላኩት የነበረው።

ነገር ግን ጥበብ ራሷን ራሷ ስለምትገልጥ፤ ራሷ አንግዶቿን በፍቅር ወግ „እንኳን ደህና መጡልኝ“ ስለምትል የጥበቡ ባለቤቶች ሁሎችም ባይገኙም ሁለመናው ገላጭ ነበር። የጥበብ ርቁቅነት አስተናባሪም፤ ተንታኝም ሳያስፈልገው በራሱ ጊዜ የሰማይ ጸጋውን በበረከት ፍሰሃን ለህሊና ሰማይን  ያዘንበዋል፤ ለመንፈስ ስንቅነቱንም በገፍ ይቸራል።

እና በዛን ወቅት ረዘም ላለ ጊዜ በማስተዋላቸው ውስጥ ያላቸውን ልቅና ብቻ ሳይሆን ለሥነ - ጥበብ ያላቸውን ልቅም ያለ ፍቅር፤ የመንፈስ ቤተኝነት፤ እንዲሁም ሥነ - ጥበብ በክቡርነታቸው ውስጥ ያለውን ቦታ እና ድርሻ በውል ለማዬት ችያለሁኝ። ስለዚህም ልዑሉ ጥበብ እና ጠቢባን ክፍላቸው እንደሆኑም ተረድቻለሁኝ።

ሌላው አንድ ጠንከር ያለ የወጣቶች ድርጅት ነበር፤ መጀመሪያ የመአህድ ነበር ኋዋላ ግን ወደ ህብረ ብሄራዊነት ምንፈስ ደረጃ አድጎ ነበር። እኔ አማካሪያቸው ነበርኩኝ ለወጣቶቹ። ያ የወጣቶች ድርጅት በርካታ ፕሮጀክቶችን አቅዶ ይከውን ስለነበር አንዱ በዬጊዜው ለወጣቶች ኮንፈረንስ ማዘጋጀት ነበር። በአንድ ወቅት ለተካሄደው ኮንፈረንስ በርካታ ሊሂቃን ተጋብዘው ነበር። ከተጋበዙት ሊሂቃን ማህል ልዑል ዶር አስፋው ወሰን አስራተ ካሳ አንዱ ነበሩ። እርእሱየኢትዮጵያ ታሪክ እና የወጣቱ ድርሻ“ የሚል ነበር።

ይመጣሉ ብለን በፍጹም አላሰብንም ነበር። ለወጣቶች የተለዬ ልዩ እንክብካቤ ያደርጋሉ፤ የውጪ አገር የትምህርት ዕድልም እንዲሳካላቸው ያስደርጉ ነበር። እርዕሱን ከተሳሰትኩኝ እታረማለሁኝ ከይቅርታ ጋርውርሰ ኢትዮጵያየሚባል የሌላ አገር ሊሂቃን ሙሁራን ሁሉ የሚያስተናግድ ልላዊ ድርጅት ነበራቸው።

የሆነ ሆኖ ያን የወጣቶችን ግብዥ ፈቅደው እና አክብረው በቦታው ካለፕሮቶኮል፤ ከላ ጣጣ ምንጣጣ ተገኝተው እጅግ የሚመስጥ፤ እጅግም ውስጥን የሚፈትሽ፤ እጅግም ሩቅ ምናብ የነበረው ትምህርት ሰጥተው ነበር። አላውቅም ዛሬ እንጂ ያን ጊዜ በዝክረ ፎቶ ተግባሩን ለታሪክ በሚያመች መልኩ ሠርተነው ነበር። እንደዚህ ኢትዮጵያ ሙሴ ሲኖራት እርሾ የሚሆኑ የወጣቶች ተግባራት ውጪ አገርም በተሟላ ሰነዳዊ ጥንቅር ተዘጋጅቶ ነበር። እርግጥ አድካሚ ነበር ግን ተሳክቶልን ነበር። ስብሰባ እጅግ አመርቂ እና ውጤታማ ነበር ብዙ ማህበረሰባዊ ጉዳዮችን ይከውንም ነበር።
  • ·       አራቱ የአዲስ ኪዳን ወንጌላውያን በልዑል ዶር አስፋው ወሰን አስራተ ካሳ ዕይታ።


ኢትዮጵያ ባላችበት አዲስ ዘመን ላይ ልዑል ዶር አስፋው ወሰን አስራተ ካሳ የነፃነት ትግሉ እንደ አራቱ አዲስ ወንጌላውያን የተመራ ነው ሲሉ አመሳጥረውታል። ይህ ዘመን ኢትዮጵያ ከሚጠፉት አገሮች ተርታ ከነበረችበት ወጥታ ነፍስ የዘራባት፤ ኢትዮጵያ ከ43 ዓመት የጭነቅ ዘመን ወጥታ ታይቶም ተሰምቶም በማይታወቅ ሁኔታ የዓለምን ቀልብ የሳበ ለውጥ ላይ ትገኛለችም ብለዋል።

ይህ ለውጥ አፍሪካ የፍቅር መሪ አገኘች በሚልም የውጪ ጋዜጠኞችን አድናቆት የተቸረው ስለመሆኑ ገልጠው፤ አላዛሯ ኢትዮጵያ አዲስ ዘመን ላይ ትገኛለች ብለዋል። የዚህ የለውጡ ወንጌላውያንም ዶር አብይ አህመድ፤ አቶ ደመቀ መኮነን፤ ዶር ለማ መገርሳ እና ዶር ገዱ አንዳርጋቸው ሲሆኑ እንደ አራቱ የአዲስ ኪዳን ወንጌላውያን አርበኞች ነው የማያቸው በማለት አመሳጥረውልናል።

እራሱ አገለላጹ እና ዕድምታው ረቀቅ ያለ ቅኔዊ ነው። አራቱ ወንጌላውያን የተሰጣቸውን መንፈስ ቅዱስ በሱባኤ ተቀብለው ወንጌልን ለማስፋፋት የጣሩት ጥረት እና የተገኘው ውጤት በመንፈስ ቅዱስ ሃይል እና ቅባዕ የተከወነ ነው።

ዛሬም ዘመኑ በዚህ ልቅና ሊቃኝ ይገባዋል ነው የዕድምታው ሚስጢር። መንፈሱ ኢትዮጵያዊነት በዘመናት ፆም ጸሎት ሰጊድ መሰላልነት የፈጣሪን የልዑል እግዚአብሄርን ደጅ አንኳኩቶ አራት የኢትዮጰያዊነት ሐዋርያት ተላኩ ነው የሚሉት ሊቀ ሊዋውነቱ ልዑሉ።

ለነገሩ መስዋዕትነትም ተከፈለበት ሁለት ወደ ጽርዕረ አርያሙ ሥላሴ፤ አካል የጎደላባቸው እና በተለያዬ ሁኔታ ጉዳት የደረሰባችው ወደ 154 ሰማዕት ሁሉ አሉበት። ትክክልም ነው ገለፃው፤ ካቢኔውም እዛው ላይ እንዲቀር ሞት ተፈርዶበት ነበር ትልሙ፤ የፈጣሪ ጥበብ ነው ያተረፋቸው። የዚህ ዘመን ሥጦታም ምርቃት ነው ላወቀበት፤ ከፈጣሪ ጋር ለተጋ ሰው። 

ይህ ያራቱ የአዲስ ኪዳን ወንጌላውያን ነገረ ሚስጠር ጥልቅ የግንዘቤ አድማስ ነው። ከዚህ ተደሞ ጋር የ እዮርን ሽልማታዊ ዘመን ያያዙበት ክህሎት በጣም በጥበብ እና በመንፈስ ሃይል የተገለጸም ነው አንደ ሥርጉተ ዕድምታ። ይህ ሥጦታ የሰው ሳይሆን እዮራዊ ስለመሆኑ ነው ልዑሉ በአጽህኖት የገለጹት።ኢትዮጵያን በቃሽ ብሏታል ፈጠሪ“ ነው የሚሉት።

ሌሎች ጉዳዮች ከበኽረ ጉዳዮ ኢትዮጵያን ከማዳን በታች ናቸው ነው የሚሉት። ስለማናቸውም ነገር ሲጠዬቁ ሌግዠሪ ነው፤ ኢትዮጵያ ላይ ከፍ ያለው ችግር ይህ ዞጋዊ እሳቤ፤ የመከከለኛው ምስራቅ አፍሪካ የቀውስ ቀጣናነት፤ እና ህዝብ የእኔ የሚለው ራፊ መሬት የማግኘት ጉዳይ ነው። ለዚህም ከዛ ጨለማ ወጥተን አሁን ባለው ሁኔታ የሚደነቅ ደረጃ ላይ ተደርሷል። ቀሪው ሥርዓት ሲዘረጋ ዝግ ተብሎ፤ በአደብ የሚከውን ነው ለዚህም ጥሞና ያስፈልጋል በማለት ነው የሚመክሩት።
ይህ ዕድል የማይገኝ ስለሆነ፤ እንዳያመልጠን ልንጠነቀለቅለት ይገባል ይላሉ የታሪክ ሳይንቲስቱ። አብረንም ልንጣደፍ ይገባል።

 ሁለማናቸን ልንገብርለት ይገባል። አዲሱ የአብይ ካቤኔ ጋር ከጎኑ ልንቆም ይገባል፤ ልንጠብቀው፤ ልንከባከበው ይገባል ነው የሚሉት እኒህ የታሪክ ሊቀ ሊሂቃን።
ከዚህ በላይ እኒህ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ጠ/ ሚር አብይን እጅግ አቅርበው እና አስጠግተው ጠ/ ሚኒስተራችን መሪያችን ነው እያሉ ነው የሚጠሩትም። መቼም ዶር አብይ አህመድ በበዛ ሁኔታ ዕድለኛ ናቸው።

እኔ ልዑል ዶር አስፋው ወሰን አስራተ ካሳ ጹሑፌን ከገኙት በጣም  በእርግጠኝነት የምነግራቸው ዛሬ በውጭ በሚገኘው የኔቱ ህውከት፤ እዛ ባለው ትብትብ ሴራ፤ በግራ በቀኝ በሚረጨው መርዝ እና ደባ፤ በባዶ ካዝና፤ በተናቆረ፤ በተበተነ የሃሳብ ክፍልፋይ ሆነው ነው ሁኔታው ነው ይህን ሁሉ የከወኑት።

ሁሉም ነገር ስክነት ከኖረው፤ ከተረጋጋ ግን ከጠበቅነው በላይ የበለጠ ውጤታማ እና ስኬታማ ዘመን ወደ ፊታችን እንዳለ ዛሬ ሳይሆን እኔ ቀድሜ ስጽፍ ነው የባጀሁት።
ኢትዮጵያዊ ማርቲን ሉተር ናቸው ዶር አብይ አህመድ - ለእኔ ገና ብሄራዊ ቀን የሚያስወስን ቁምነገር በዚህ ታላቅ ኢትዮጵያዊ መንፈስ ውስጥ እንዳለ ዕምነቴ ሙሉ ነው። ቀረህ የምለው ምንም ነገር የለም እና። የመንፈስ የሰው የተፈጥሮ የእኛዊነት ሙሴ ስለሆኑ። ዕድልም አለ። የሄዱበት ሁሉ ስኬት ነው … ለምለምም ነው። ከ ውስጥ ስለሆነ ሰዉ ከውስጡ ለማስቀመጥ ይፈቅዳቸዋል። አንደባታቸው እጅግ ልዩ ቃና እና አቅራቢ ነው።    
  • ·       ስለ ርቱነት ልዑሉ የሰጡት አስተያዬት።

መንገዱ አዲስ እና ባልተጠበቀ ፍጥነት እጥፍ ድሎችን ያሰመዘገበ፤ ከልብ እና ከውስጥ ሊደመጥ የሚገባው፤ የንግግርን ጥበብ የሰው መንፈስን በመለወጥ እረገድ መሬት ላይ የታዬበት፤ ንግግር የሰውን ልባዊነት በመንፈስ ድልድይነት የመዘርጋት አቅሙ የታዬበት፤ የንደበት ቁምነገርነት የተመዘነበት፤ ፍቅር የአፍ መፍቻ ቋንቋ የሆነበት፤ ለአፍሪካ ለራሷ አዲስ የምህንድስና ጥበብ ነው ይላሉ የታሪክ ሳይንቲስቱ ዶር ልዑል አስፋው ወሰን አስራተ ካሳ።
  • ·       የሰላም ዓለም አቀፍ ሽልማት እጮኛነት በሚመለከት።

መቼም ክቡርነታቸው ለጋዜጠኛ ያላቸው ክብር እና የሰጡት ዕውቅና ከድንቅ በላይ ሲሆን፤ በዚህ ዙሪያ ለተጠዬቁት ጥያቄ ሲመልሱይቅር ይበለኙ እና የቀደመው የአሜረካ ፕሬዚዳንት / ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ምን ሰርተው ነው ለዛ ሽልማት የበቁት? በማለት ይጠይቁ እና የጠ/ ሚር አብይ አህመድን ቅናዊ፤ ፍቅራዊ፤ ትህትናዊ 100 ቀን ጉዞ ጋር በማነጸጻር ይልቃል፤ ይገባቸዋልም“ ባይም ናቸው። ይህን ሲናገሩት በሙሉ ልብነት እና በእርግጠኝነት በፍጹም ጨዋነት እና ቅንነትም ነው።

ክብሩነታቸው …  ኤርትራው ጉዳይ ሳይጨመር አገር ውስጥ ብቻ ያደረጉት ከበቂ በላይ ነው የሚሉት። ተያይዞ ለተነሳላቸው የፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ ሽልማታዊ ሂደትን አስመልከቶም፤ ለሰላሙ የሰጡት ቅናዊ ምላሽም አድንቀው እንደ አገር ኤርትራ ዛሬ ራሷን የቻለች አገር ስለሆነች በኤርትራውያን ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ሊቀርብ የሚገባው ስለመሆኑ ጥቆማ ሰጥተዋል።

እጅግ ቅናዊ፤ ክህሎታዊ፤ ሰዋዊ፤ እኛዊ፤ ተፈጥሯዊ የሆን ዕይታቸውን ነው እኒህ ብልህ ጥበብ ያጋሩን። በዚህ ውስጥ እጅግ የላቀ ያስተዋለ የመሪነት ክህሎትም እኔ አይቻለሁኝ። ወገንን በፍቅር የማዬት ሰውኛ ጠረን አድምጫለሁኝ፤ ለዚህም ሙረሲን አንደ ምሳሌ ያነሱት፤ ትግራይን እንደ ምሳሌ ያነሱት ነገር ከልብ የሚገባ አንጀት አርስ ትንተና ነው። 

ይህ የተመስገን ዘመን እንዲህ በዬዕለቱ የምሥራችን እዬቀለበን፤ የኢትዮጵውያን ቅኖችን ወደ አንድ ማዕዶት እያመጣ፤ ልንሰማቸው የሚገቡ የመልካምነት ዓውደ ምህረቶች እዬሰፉ፤ አዋኪ ሃሳቦች እዬጠበቡ እና ጥግ እያጡ እንደሚመጡ ተስፋ አለኝ።

በሰው የተከወነ ነው ለማለት በማያሰቸለው 100 ቀን የቀን ከሌት ትጋት በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር ሰላምን፤ ፍቅርን ለማስፋፋት የተደረገው ጥረት እና የተገኘው ውጤት ታሪክን፤ ትውፊትን፤ ትሩፋትን ዕሴትን አበልጽጓል።
የአብዛኛውን ቅን ኢትዮጵውያን መንፈስ በመስማማት፤ በማስታራቅ፤ በማቀራረብ መንፈሳዊ ሃዲድ አቆራኝቷል። ቀደም ባለው ጊዜ የኢትዮጵያ ጉዳይ የጥቂቶች የነበረው፤ ዛሬ በመላ ዓለም ያሉት ኢትዮጵውያን ጨምሮ የአገራቸው ጉዳይ ሙሉ፤ ንቁ ብርቱ ተሳታፊ አድርጓቸዋል።

አብዛኛው ቅኑ ዜጋ መንግሥት አለን፤ መሪ አለን፤ ሙሴ አለን አሰኝቷል። የዕዬለቱን ዜና እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በጥድፊያ ይከታተለል፤ ሃሳቡን ይሰጣል፤ ሙሉ ተሳትፎ ያደርጋል። በሚገባም የእኔ ብሎ ይከታተለል። ውጪ የሚኖሩት ስለመሪያቸው አብረው ለሚሠሩት ሁሉ ያሰተዋውቃሉ፤ አንገታችን የማንደፋበት መሪ ሰጠን ብለውም ልዑል እንግዚአብሄርን ያመሰግናሉ። ተመስገን።
  • መከወኛ

ልዑል ዶር አስፋው ወሰን አስራተ ካሳ ዛሬ የሰጡት ቃለ ምልልስ እጅግ ታሪካዊ ነው። መንፈሳቸው ከኢትዮጵያዊነት ጋር በጽኑ የተሳሰረው የታሪክ ሙሁር እና የውርሰ ኢትዮጵያ አመክንዮ እጬጌ ዛሬ ከአውስትራልያው ራዲዮ ከSBS ዝግጅት ጋር ባደረጉት ቀለምልስ ዘለግ አድርገው ትናንትን - ዛሬን - ነገን - ከነገ ወዲያን ቃኝተውታል። ትውልዳዊ ድርሻችንም በሚጋባ ገልጠዋል።

የአንደበት ብቃት ለመሪነት ክህሎት ምን ያህል አስፈላጊና ተፈላጊ ስለመሆኖ በተደሞ አመሳጥረውልናል። እሳቸውም እኮ ባለርቱ አንደበት ናቸው። እጅግ ማራኪ እና ሳቢ አቀራርብ ነው ያላቸው። የጥናት እና የምርምርም ሰው ናቸው።

ኢትዮጵያ ባላት የህሊና ጥሪት ሙሉ ለሙሉ መጠቀም የምትችለበት ዘመን ነውና ትውልዱን ወደ በጎ - ደግነት - መልካምነት - ራስን ወደማወቅ በሚያመጡ ጉዳዮች ላይ ከእንደዚህ ዓይነት የዕውቀት፤ የልምድ፤ የተመክሮ፤ ክህሎት ጠገብ፤ ዲታ አቅም በእጅ እያሉን መዋለ መንፈሳቸውን ተሻምቶ ጥቅም ላይ እንዲውል የማማቻችት ተግባር የአዲሱ የአራቱ አዲስ ኪዳን ባለቤቶች እርምጃ፤ የጠ/ ሚር አብይ አህመድ ካቢኔ ሰፊ መስክ ሊሆን ይገባል። አብሶ በዚህ መልክ ሁኔታዎችን በልዩ አክብሮት እና ውስጥነት በቅንነት ለሚቀበሉ ሊሂቃን የአያያዝ ልዩ ጥበብ እና ልዩ ስልት፤ በልዩ ሁኔታ ምቹ ነገሮች ሁሉ ሊደራጅ ይገባል እላለሁኝ እኔ እንደ ሥርጉተ ሥላሴ።

ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።

የኔዎቹ ቅኖቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።



አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።