ልጥፎች

ከጁን 15, 2019 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ለግራጫማ ሰብዕና ልዋጭ የተሰጠችው አላዛሯ ኢትዮጵያ። {የወግ ገበታ 15.06.2019}

ምስል

ለግራጫማው ጃዋራዊው ሰብዕና ልዋጭ የተሰጠችው አላዛሯ ኢትዮጵያ።

ምስል
ግራጫማ ሰብዕና። „ የደከሙት ን   እጆች   አበርቱ፤   የላሉትን ም   ጉልበቶች   አጽኑ። “ ትንቢተ   ኢሳያስ   ምዕራፍ   ፴፭   ቁጥር   ፫ ከሥርጉተ © ሥላሴ Sergute©Selassie 15.06.2019 ከእመ   ዝምታ   ሲዊዘርላንድ። ·        ጠብታ። ወዶቹ ቅኖቹ ቅኔዎቹ የአገሬ ልጆች እንዴት ናችሁ? ደህና ናችሁ ወይ? ዛሬ ግራጫማ ሰብዕናን አስመልከቶ ጥቂት ነገር ባነሳሳ ትፈቅዳላችሁን የኔታዎቼ? … ከበታችነት ደዌ ጋርም ይህን መሰል ሰብዕና ተዳማሪ ነውና። አሉታዊው ዴሞግራፊ የነፍሱም ክር በዚህ ዘሃ የተሸመነ ነውና። ·        ሲቃ። እንደምታውቁት አዱኛዎቼ፣ የአገሬ ልጆች የተውኔት ተፈጥሮ በሁለት ዘርፍ ይዳኛል። እኔ እህታችሁ ግን ሦስተኛም አለበት ብዬ እሞግታለሁኝ። ይህን በጸጋዬ ድህረ ገጽ በ2009 ላይ ጽፌበት ነበር። ዓለምም ጨለማና ብርሃን በሚል በሁለት ጎራ ትለያለች ከጸሐይ አፈጣጠር ተልዕኮ አንፃር። ከቀንና ሌሊት አፈጣጠር ሥነ-አመክንዮ በመነሳት። በመኖር ሂደትም ደስታና ሃዘን ተብሎ እንዲሁ በሁለት ዘርፍ ይመደባል። እኔ ግን ሦስተኛም አለ ባይ ነኝ … ሊነጋጋ ሲል፤ ሊጨላልም ሲል ያለው ቅይጥ ግራጫማ ቀለም፤ ግራጫማ ሁነት በሦስተኛ ዘርፍ መመደብ አለበት ብዬ እሞግታለሁኝ።   ለዕለቱ የተውኔት ሁለት አንገፋ ፒላሮች እንመልከት። ትራጀዲ እና ኮሜዲ አጫዋች አዝናኝ አሰቂኝ በአንድ ማህበር ሁለተኛው ደግሞ አሳዛኝ አስለቃሽ፤ ሆድ የሚያስብስ በሌላ ወገ...

አቶ ያሬድ ኃይለማርያምን እና መሰሎቻቸውን የሚሰማ መንግሥት ከወዴት አለ?! {ከጸሐፊና ተርጓሚ አቶ መስፍን ማሞ}

 ንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጡልኝ።  አቶ ያሬድ ኃ ይለማርያምን እና መሰሎቻቸውን የሚሰማ መንግሥት ከወዴት አለ ?!   “ እኔ በስውር በተሰራሁ ጊዜ  አካ ሌም በምድር ታች   በተሠራ ጊዜ አጥንቶቼ ከአንተ አልተሠወሩም። “ መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፻፴፰ ቁጥር ፲፭ መስፍን ማሞ ተሰማ {ጸሐፊና ተርጓሚ} ሠላም ለናንተ ይሁን! በኢትዮጵያ ሥነ - መንግሥትና ሥነ - ህዝብ መስተጋብርና ኃ ላፊነት፣ ህጋዊነትና ተጠያቂነት ላይ የአቶ ያሬድ ሀይለማርያም ምልከታና ምክረ ሀሳብ ሁሌም ያስደምመኛል። ለአብነት ጁን 13/2019 ' ፖለቲከኞቻችን ጠዋት ጥምጥም ከሰዓት ኩፊ ' በሚል ርዕስ በፌስ ቡክ ገፃቸው ያሰፈሩት ጥልቅና ውስጠትን ጠያቂ የሆነ የወቅቱን ፖለቲካዊ ዱካ የቃኙበት ፅሁፍ አንዱ ነው። የኢትዮጵያ መሪዎች ወይም የመንግሥት ኃ ላፊ ፖለቲከኞች ግን እንዲህ ያለ ቅን መንፈስና ቅን ሰብዕና ከሀገራዊ ራዕይ ጋር ያጣመሩ ዜጎችን አያስጠጉም። አያነጋግሩም። አያዳምጡም። እነርሱ - የሀገረ መሪዎቹ - በዙሪያቸውና በመንግሥታቸው   መዋቅራት   ሁሉ   ( አልፎ አልፎ አንዳንድ ሁለ ገብ ቅቡልነት ያላቸውን ለገፅታ መሳመሪያና ማድመቂያ ካልሆነ በስተቀር ) በአብዛኛው   የሚያሰባስቡትና   በሚመሩት   መንግሥት መዋቅራት ኃ ላፊነት የሚሰጡት በዕድሜያቸውና በዘመናቸው ካሳለፉት ፖለቲካዊ ኩነት ያልተሞረዱ፣ እንዳረጀ እባብ የውጪ ቆዳቸውን እንጂ ውስጣቸውን   ያልቀየሩ ካ...